Saturday, November 24, 2012

ታሪክ ለመስራት ታሪክን ማጥፋት ተገቢ አይደለም !!


ይህ የባቡር መሥመር መሰራት የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት ማፍረስ ምን ይባላል ?
 ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም፡፡ <<በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ>>  አረለ የሚለው ተረቱ እውነት ነው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡  ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡ ታሪኳን ማፍረስ አንችልም !! ታሪክ ይፈርዳል !!
ይህ ታሪኳና ቅርሷ ደግሞ የህልውናዋም ምንጭና መሰንበቻም ጭምር ነው፡፡ ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ የለም!  እናም የሚመለከታቸው ሁሉ ወደ ርምጃ ከመግባታቸው በፊት ሦስት ጊዜ ሊያስቡ ይገባል፡፡ መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡ ግን አሁን በሐውልቶቹ አጠገብ የሚከናወነው ቁፋሮ ወደ መሠረታቸው እየሄደ ነው፡፡ እንደሚሰማውም የባቡሩ መሥመር በሐውልቶቹ ሥር የሚዘረጋ ነው፡፡ ታድያ የሐውልቶቹ ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?  ‹ለጊዜው ተነሥተው በኋላ ይመለሳሉ› የሚል መረጃም እየተሰማ ነው፡፡ ለጊዜውስ ተነሥተው የት ነው የሚሄዱት? በኋላስ በምን ሁኔታ ነው የሚመለሱት? ታሪካዊ ቦታቸውንስ ይለቃሉ?

እንዲያውም ሕዝቡ በመንገድ ምክንያት ቤት የፈረሰባቸው ሰዎች ኮንደሚንየም እንደሚሰጣቸው ሁሉ እነርሱም ከዚያ ቦታ ተነሥተው ኮንደሚንየም ሊሰጣቸው ይችላል እያለ መቀለድ ሁሉ ጀምሯል፡፡እውነት ነው ሕዝቡስ ቢሆን ከልምድ ነው እኮ ምን ይበል ,, ሕዝቡ ራሱ ነው ታሪኩን መጠበቅ ያለበት!
                                           ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
                                                                 ከዘካሪያስ



No comments:

Post a Comment