Thursday, May 21, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ በ አማራ ክልል እንዳይንቀሳቀስ እየተደረገ ነው


semayawi-party
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በክልሉ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ሰንካላ ምክንያት የስርዓቱ ካድሬዎች ባሰማሯቸው በሆዳቸው ባደሩ የደህንነትና የፀጥታ አካላት እየታደኑ መታሰራቸውን አስረድተዋል፣

በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላቶች ከታሰሩባቸው ከተሞች መካከል ማንኩሳ፤ ደንበጫ፤ ፍኖተሰላም፤ ማቻከል፤ ሉማሜ፤ ሰከላና አዴት ከተባሉት አካባቢዎች ከሚያዝያ 24 /2007 ዓ/ም ጀምሮ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፀዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፍኖተሰላም ከተማ ቀበሌ 02 ህንፃ ተከራይተው ፅህፈት ቤት በመክፈት ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የድርጅታቸውን ዓላማ የሚገልፅ ፖስተር ለመለጠፍ ሲሉ በፖሊስ እየተደበደቡ መባረራቸውን የአይን እማኞች ዋቢ ያደረገው መረጃ ገልፀዋል፣

No comments:

Post a Comment