Sunday, March 20, 2016

"ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል"አሉ

"ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል"አሉ አበው።በውሸት አለም ውስጥ እውነትንም በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ መሞከር ለማያውቅ ትውልድ"ውሸት ይሆን?" የሚል ጥርጣሬ ሊያስነሳ ይችላል።ብዙ ልጆች "ወልቃይት አማራ ነው!"እያሉ ሲፅፉ አያለሁ።እኔ ደግሞ ይህን አባባል ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን"እየሱስ ጌታ ነው"የማለትን ያህል ዘግይቶ መመስከር ይመስለኛል።ለቀባሪ ማርዳት አይነት የተደጋገመ አባባል በሉት ከፈለጋችሁ።የወልቃይት ማንነት አያጠራጥርም እኮ።የማያውቅ አለ እንዴ?እኔ የምስማማው "የወልቃይቶች መብትና ነፃነት ይከበር!" በሚለው ነው።ለወልቃይት እኔም ያገባኛል ባይ ነኝ።
እንቅልፍ የሚነሳን ብሶት እስከሆነ ድረስ ለኛ አጀንዳችን ወልቃይት ብቻ ሳይሆን ጠገዴ፣ራያ አላማጣ እና አዘቦ፣ኡመራ፣መተከልናከፍ ሲል አክሱም ናቸው።ለርሀቡ የተሰጠው ምላሽስ ብትሉ።እርጎ የሚቀዳውና ቅቤ አናቱ ላይ የሚለጥፈው የሰቆጣ ህዝብ በድርቅ ምክንያት የሚበላውና ሚጠጣው ውሀ ሲያጣ እና ከቀየው ሲሰደድ ምን ተባለ?ወደ ዛሬው ጉዳይ ልምጣና ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ማንነታቸውን የተነጠቁ ወረዳዎችና ዞኖች ነፃ መሆን አለባቸው።አለዚያ በብሄርተኝነት ተነሳስተን እንዳንጠፋፋ እፈራለሁ።መሬቶቻችን የኛ ብቻ ናቸው!!!

No comments:

Post a Comment