Tuesday, August 4, 2015

የአፍራሾች ዋይ ዋይታ (ደነባ ጉልላት)

ደነባ ጉልላት
ስንሰማ የነበረው ወያኔን በትጥቅ ትግል የሚፋለም ጠፋ ነበር ። ስንሰማ የነበረው የሕዝባዊ ሀይሉ መሪ ዶክተር ብርሃኑ በግንባር አልተገኙም የሚለውን ነበር ። ሁለቱም ቅሬታ ሲወገድ ግን ዋይ ዋይታና ኡ ኡታ የሚያሰሙ ከየስርቻው ብቅ አሉ ።
ከማንም በፊት ወደ ሻዕቢያ ሂዶ የነበረው ኤልያስ ክፍሌ የዚሁ ፊታውራሪ ሆኖ ብቅ አለ ። ወዳጅ ሲለው የነብረውን ሻዕቢያን ጠላት ብሎ ሰይሞ ተጀመረ የተባለውን የትጥቅ ፍልሚያ ሀሰት ሲል ኮነነ ። ሕዝባዊ ሀይሉን ቁጥር ከ ፲ ወደ መቶ ቢያደርሰውም የትም አልተንቀሳቀስም ብሎ አስተባበለ ።ይኽው ግለሰብ ግን የዴምህት ሀይል በኤርትራ ፵ ሺ ደርሷል ይለናል ። ለዚህ ያህል የማይንቀሳቀስ ጦር ምን ያህል ወጪ ይጠይቃልን አላሰበበትም ።ኢሳያስም የሌላ ህገር ዜጎች ያሉበት ይህን ያህል ጦር ማስተናገድስ ለደህንነቱ ይበጀዋልምን ገዶት ለኤልያስ!የኢትዮጵያ ረቪው የኢንተሊጀንስ ክፍል ባገኘው መረጃ መሰረት እያለ ውሸት መጠረቅ ልምዱ ነው ። ኤርትራና ሻዕቢያ ጠላት ከሆኑን ኢሳያስን የዓመቱ የኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ያለ ኤልያስ ሊወገዝ የሚገባው ይሆናል ። ኾለኔል ፍጹም ያን ሁሉ ወጣት ከረሸነ ለምን ይህንን ለማጋለጥ ዓመታት ፈጀበት ብንል መልሱ ራሱ ጠቋሚ ነው ።ኤልያስ ክፍሌ ለመሆኑ አለሁ አለሁ ማለት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ የማንን አጀንዳ ነው በስራ ላይ እያዋለ ያለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ዋናው ተል እኮእ ግን አርበኛ ሀይሉን/ታጋዮችን መበጥበጠ መሆኑን ታሪኩ ይመስክራል ።

ሌላው ዋይ ዋይታ አሰሚ አቶ መልኬ ሲሆኑ ወደ ኤርትራ የዘለቁት በዚያ ዋሾና ተራ ሌባ አብርሃም ያዬህ ተወስደው ነውና ያጋጠማቸው መጥፎ ተመክሮ ካለ ቅሬታቸው ቢገባንም ስለ አርበኞች ግንባር ያላቸው ዕውቀት ግን ጊዜ ያለፈበት መሆኑ የሚታይ ነው ። ደምስ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ እሱም ቢሆን አርበኞች ግንባርን ደጋፊ መስሎ በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ የዘለቀ ነው ።ለምን መሄድ እንዳቆመ ኮለኔል ፍጹምን መጠይቅ አንገደድም እናውቀዋለን ምክንያቱንና ነው ። እስካዛሬ ድምጹን አጥፍቶ ተደብቆ ከርሞ አሁን በግንቦት ፯ና አርበኞች ግንባር ላይ ምን አስነሳው በሻዕቢያም ሆነ በአርበኞች ግንባር መሪዎች ግፍ ተፈጸመ ካለስ ለምን እስካሁን ዝምታን መረጠ ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ግልጽ ያደርጋል የእሱን አፍራሽ ተልእኮ ።
ከድረ ገጾች ደግሞ ያ የለመደበትን ኢትዮፓትርዮት የተባለውን የትምክሀት ገጽ ወደ ጎን ስንተው የኢትዮሚዲያው አብርሃም በላይና የዘሃበሻም አዘጋጅ ና ጋዜጠኛ በሉን ባዩን አበበ በለውን አጅበው በጸረ ሻዕቢያ ሰበብ ሕዝባዊ ሀይሉ ላይ ተነስተዋል ። ወያኔን የሚያስደስት ጸረ ሕዝባዊ ሀይልና ጸረ ዶክተር ብርሃኑ ዘመቻ በግልጽም በረቀቀ መንገድም እያካሄዱ መሆናቸውን ሀገር ወዳዶች ያጋለጡት ጉዳይ ነው ።ከኢትዮፓትርዮት እየለቀሙ ጸረ ሕዝባዊ ሀይል ጽሁፎችን የሚለጥፉት አሲምባ አዘጋጆች ደግም ጸረ ግንቦት አቅዋማቸውን ማሰማት ከጀመሩ ውሎ አድሯል ። የፓል ቶኩ እንደራሴ (ተስፉ ፡ስድስት“) አዲስ አቅዋም አልያዘምጸረ ግንቦትነቱ የታወቀ ነውን ። የዚህ አፍራሽ ስብስብ ማዕክል ግልጽ ሆኖ ባይመጣም ወይም አንድ ሆኖ ላይገኝ ቢችልም ስራቸው ግን የተጀመረውን ትግል በርታ በርቱ በማለት ፈንታ ማፋለስ ሆኖ ይገኛል ።ከዚህስ ማን ይጠቀማል ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ። ተጠቃሚው ወያኔ መሆኑ ግልጽ ነው ። መፍረክረክ ሲጀምር አይዞህ ባዮች ስለሆኑለት ባይወዳቸውም ሊያመስግናቸው ይችላል ። አንዳንዶቹም በቀጥታ ከእሱ ጋር ንክኪ የላቸውም ማለት አንችልም ። እነ አበብ በለው ወያኔ ወያኔ መሽተት ከጀመሩ ዓመታት አልፈዋል ።
ትጥቅ ትግሉ ተጀምሯል ። ያለውን አደጋ አይተው ሸብረክ ሳይሉ መሪዎቹ ወደ አስመራ አቅንተዋል ። ትግሉን በቦታው ሆነን እንመራለንም ብለዋል ። አንመለስም እስከ ድል ድረስ ብለዋል የሚለውን ግን ካፋቸው ስላልሰማሁ ማረጋጋጥ አልችልም ። ብለዋል ባዮቹ አንዳንዶቹ ምን ሞቲቭ እንዳላቸውም የሚሳት አይደለም ። ሕዝባዊ ሀይል የጀመረውን ትግል በርታ ግፋበት ሊባል ይገባዋል ። ዶክተር ብርሃኑ ውድቀታችንን ትሰማላችሁ፤ ስንነሳም ትሰማላችሁ እንዳሉት ሁሉ በዚህ መንፈስ የትግሉን ሂደት መጠበቅ መልካም ይሆናል ። ድጋፍ እየሰጠናቸው መሆኑ አስፈላጊ ነው ። ከዚህ ቀደም በጄኔራል ሃይሌ መለስ፤ በኢአግ፤ወዘተ የተደረጉ የትጥቅ ትግል ሙከራዎችን በበቂ ባንደግፋቸውም ውድቀታቸውን አልተመኘንም ። የረዱም ጥቂቶች አልነበሩም ። የሕዝባዊ ጥሪ እንደሚወገዘው በነዚህ አፍራሾች ያልተደረገ ከሆነ በአጭር ጊዜ መታወቁ አይቀርም ።እየተካሄደ ካለም (እኔ ነው ብዬ አምናለሁደግሞ አፍራሾቹ ያፍራሉ ። እነ ኤልያስ፤አብርሃም፤ዘ ሀበሻ፤አበበ በለውና መሰሎቻቸው ላይም ማዕቀብ ያስፈልጋል ።
አፍራሾች ይፈርሳሉ !!
ድል ለሕዝብ !!

No comments:

Post a Comment