Wednesday, August 26, 2015

አንተ የምትተኛ ንቃ!

አንባገነኖችን የበለጠ አንባገነን፡ ጨካኞችን የበለጠ ጨካኝ ያደረገውን አስተሳሰባቸውን ዛሬ በተቃውሞ መልክ ወደ ህዝብ እያወረዱ ይገኛሉ። ሆነ ብለው በታቀደና በተጠና መልኩ የተጠበቡበትን ከግብር እና ከእንጀራ አባቶቻቸው ከፋሽስቶች የተማሩትን የከፋፍለህ ግዛ እስትራቴጂ በመጠቀም በቅድሚያ የኢትዮጵያዊነት ተቀዳሚ አቅንቃኝ የነበሩትን አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን የመቆጣጠርና የማዳከም ስራ ጨረሱ፡፡ የኦሮሞን ህዝብ በአማራው ላይ በጠላትነት እንዲነሳና በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች መካከል የጠላትነት መንፈስን ለመፍጠር ሰሩ፡ በዚህም የፈለጉትን ያህል ፍሬ አፈሩ። ቀጥሎም ሙስሊሙን ከክርስትያኑ ለማጋጨት በሙስሊሞች ስም ብዙ ቤተ መቅደሶችን አቃጠሉ። ብዙ ክርስቲያኖችን ገደሉ።
በክርስትያኑ ትግስትና አስተዋይነት ሲከሽፍባችዉ በልማት ሰበብ ቤተ ክርስትያንን ይዞታ በመቆጣጠርና በማደህየት ስራ ተጠመዱ። በእቅድ ሀ ያልተሳካላቸውን በእቅድ ለ ቀጠሉበትና ሙስሊሙን በአሸባሪነት በመፈረጅ ክርስትያኑን ከጎናቸው በማሰለፍ ከህዝበ ሙስሊሙ ለማጋጨት ሞከሩ ይህም አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም አማራውን ከመላው ኢትዮጵያ በማፈናቀል፡ ሀብቱንና ንብረቱን በመዝረፍ፡ ሚስቱንና ልጁን በመድፈርና ዘር እንዳይተካ በማድረግ በአንድ በኩል ራሱን መከላከል እንዳይችል በማዳከምና በማደህየት በሌላ በኩል በምሬት ከሁሉም ክልሎች ጋር ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዲገባና እንዲዳከም ለማድርግ ሞከሩ። በአማራው ህዝብ በኩል ያደረሱት ጥቃት አማራውን የኢትዮጰያ ህዝብ በሚዘገንን ደረጃ ያጠቃ ቢሆንም የፈለጉትን የእርስ በእርስ ግጭትና የብሔራዊ አንድነት በማናጋት በተለያየ መንገድና ጥበብ ያሻሻሉአትን ክልል ይዞ የመገንጠል ህልም አልተሳካም። የመጨረሻው ግብ መጀመሪያ አድርገው የያዙትን ግዛት የማስፋፋት ዘመቻም አጠናክረው በመቀጠል ከዘጠኝ የማያንሱ የአማራ ክልል ወረዳዎች ወደፊት ሊገነቡዋት ወደሚከጅሉዋት የትግራይ ሪፐብሊክ አካተው ጨርሰዋል። ለዚህ ግብ ስኬት የመጨረሻ የማስፈጸሚያ እስትራቴጂ ደግሞ በአንድነት ፈርጀው ለ24 አመት ያዳከሙትን እና መብቱን ለማስከበር የተጠቃበትን የአማራነት ማንነት ይዞ የተነሳውን ሕዝብ ትግል በትግል ስልትና በዞን አወቃቀር ከፋፍሎ ማዳከምና ወደ እርስ በእርስ ግጭት በማስገባት እራሱን መከላከል እንዳይችል ማድረግ ነው።
አንተ የምትተኛ ንቃ! የአማራን ህዝብ የነጻነት፡ የእኩልነትና የፍትሀዊ አስተዳደር ጥያቄ ወደ መገንጠል የመግፋቱና የአማራ ጽንፈኝነት የመፍጠሩ እንቅስቃሴ የመገንጠል ጥያቄ ኖርማላይዜሽን እና የአማራውን አንድነት የመከፋፈል እንዲሁም አማራነትን በተቀበሉና አማራነትን የኢትዮጵያዊነት ስጋት አድርገው በሚወስዱ ሀይሎች መካከል መከፋፈልን የመፍጠር ሴራ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። በመሆኑም አማራን መገንጠል ወደሚል አስተሳሰብ ከወገን ትቆርቁዋሪነትና ካለማስተዋል የዘለቅን እንዲሁም በቅንነት መንፈስ ይህንን አባቶቻችንን የሰሩትን ድንበር የማፍረስ ጥረት ውስጥ የገባችሁ ወንድሞቸ ይህ አማራውን የመታደጊያ መንገድ ሳይሆን ውጤቱ የአማራውን ታሪካዊ ማንነት መናድ መሆኑን ተረድታችሁ ትክክለኛውን ትግል በትክክለኛው መንገድ እንድንታገል ከታላቅ አክብሮት ጋር ጥሪየን አቀርባለሁ። የአንድነት ሀይሎች ላይ በተድጋጋሚ የተስተዋለው በአማራው ህዝብ ላይ ካለማባራት የሚዘንበውን እስከዘር ማጥፋት የደረሰ ፍጹም ኢሰባዊ ተግባር በቸልታ የመመልከቱ ነገር ሀገርንና ወገንን እንደመክዳት የሚቆጠር መሆኑን ተረድተን ለወገናችን ልንደርስለት ይገባል። የሌላ ብሄር ተወላጆችም ከክልሉ ተወላጆች እኩል ሀላፊነት አለባችሁ። የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ከአዲሱ አበባ ማስተር ፕላን ክለሳ ጋር ተያይዞ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰውን እስከግድያ የደረሰ የሰባዊ መብት ጥቃት በምቃዎም በቀድሞዉ አንድነት ፓርቲ አስተባባሪነት የታየው ተሞክሮ በመርህነት ሊወሰድ የሚግባው መልካም ምሳሌ ነው።

አብረን ስንቆም እንበረታለን ስንበታተን እንረታለን! በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሁለገብ ጥቃት ባስቸኩዋይ ይቁም! ፍትህ ለኢትዮጵያ! የሰፊው ህዝብ ትግል ያሽንፋል!

No comments:

Post a Comment