Wednesday, August 26, 2015

በሓወልቲ ሰማእታት ለምትገኘው ኣቶ Daniel Berhane

፩) ኣብዛኞቹ የቀበሌና ወረዳ ተወካዮች፣ የሴቶችና የገበሬዎች ማህበራት ተወካዮች፣ ማንበብና መፃፍም እንደማይችሉ ማረጋገጥ ከፈለግክ የተሰጣቸው ማስተወሻ በእጃቸው መኖሩና ኣለመኖሩ ለማየት ሞክር
፪) ኣቶ ኣባይ ወልዱ የኮሚቴው ኣባል መሆን ኣይጠበቅባቸውም። በሳቸው ስር ወይም ኔትወርክ ያሉ ሌሎች ኣባላት የኮሚቴው ኣባል ሁነው ኣስፈፅመዋል።
ይህም የሃገራዊ ምርጫ ልምድ መቅሰም ትችላለህ። እንደ የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ቅስቀሳና ፍላጎት ቢሆንማ ማንም ኣባይ ወልዱ በስልጣን እንዲቆይ ኣይፈልግም ነበር።

፫) የስብሰባው ተሳታፊዎች ኣቀማመጥ በመጡበት ወረዳና ዞን እንዲሆን የተደረገበት ዋና ምክንያት ምን ይመስልሃል...? የነትወርክ ሃላፊዎች በግሩፕ ስብሰባና ከስብሰባው በሗላ ዋና ስራቸው እያንዳንዱ የኣባይ ወልዱ ደጋፊና ተቃዋሚ ለይቶ ማሳወቅ ብቻ ነው። የምልመላው ሂደት ታማኞች ተለይተው ስለመጡ የማሳመን ስራ ኣስቀድሞ የተሰራ ነው።
የህወሓት ኣባላት የምስጢር ምርጫ ልምድ ባለቤት ናቸው ያልከው የቅርብ ግዜ ማለትም የ11ኛው ጉባኤ ልምድ በኔትወርክ ስራ እንደተሰራ ላስታውስህ እፈልጋለው።
፬) የግለ ሰዎች የቁንጅና ውድድር ሳይሆን በሁለት የህወሓት ኣንጃዎች የስልጣን ሽኩቻ፣ የስልጣን ሽምያ ጥሎ ማለፍ መሆኑ ግልፅ ነው። ከጉባኤ በሗላ መሰረታዊ የመዋቅር ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚያስብና የሚጠብቅ ሰው መኖሩ እጠራጠራለው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO....!

No comments:

Post a Comment