Wednesday, August 26, 2015

የህውሃት አሽከር የሆነው ብአዴን

የህውሃት አሽከር የሆነው ብአዴን አሽከር ደመቀ መኮነን አማራው ተገፍቷል ተፈናቅሏል ይህን ህገ ወጥ ተግባር ደግሞ ብአዴን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የመንግስት ድርጅቶች ሃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው ብሎ መናዘዝ መጀመር ከምን የመነጨ ይሆን? ይህ ነገር ውጫዊ ተፅእኖው ምን ያህል እንደበረታባቸው ማሳያና የተገፋውን የተገደለውን የተባረረውን አማራ አለንልህ ችግርህን የምንፈታልህ እኛው እና እኛው ብቻ ነን ሌሎች የሚሉህን አትስማ ብሎ የከሰረ ፖለቲካ የመስራት የታሰበች ቧልት መሆኗን 100%( ቅርጫ ቦርድ ይህ የእኛ ነው ለምን ተጠቀምህ እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ) አውቀናል ነቅተናል። 

ሆዳሙ ደመቀ ሆይ ያኔ በ1999/2000 ዓ/ም ላይ የመተማን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በጊዜው የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም የህዝብ ነው ህዝብ አውቆት ነው መሆን ያለበት ብሎ የተወውን አንተ ፈርመህ ዛሬ የተቀመጥህበትን ወንበር የተሸለምህበትን አማራ አለሁልህ የምትልበትን ድፍረት ከየት ተበደርህ?
አማራ አምርሯል ልቡም ከእናንተ ጋር እንዳልሆነ አስነግጠን እንነግርሃለን ቀናትን የሚጠብቅ አቢዮት ብቻ ነው የቀረው፤ክብሩን፣ማንነቱን ያስመልሳል ህልውናውንም ያስጠብቃል በወሮ በላ ልጆቹ የጠፉ ሃብት ንብረቶቹንም በደሙ ያስመልሳል። ትላንት እነ አቦይ ፀሃየ የጠፋው አማራ መልሶ እንዲያንሰራራ አንፈልግም ብለው በድፍረት የሞቱን ድግስ ሲያውጁ የት ነበርህ? ድሮውንም ብአዴን አማራውን አይወክልም አማራ የአሽከርነት አባዜ የለበትም ኩሩ እና ታሪካው ህዝብ ነው ወደ ነበረበት የታሪክ ምህዋሩ በቅርብ ይመለሳል።

ሞት የአሽከሩ ብአዴንና ለአሽከሮች

No comments:

Post a Comment