Tuesday, August 11, 2015

ላለፉት 12 ዓመታት “ደብል ዲጂት” ያደገው ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በምትጠቃበት የድርቅ መጠን እንደ ኬንያና ታንዛኒያ የመሣሰሉት ጎረቤት ሀገራትም እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። ሆኖም ከተጠቀሱት ሀገሮች በከፋ ሁኔታ ድርቁ(የአየር ንብረት መዛባቱ)- ረሀብና የከፋ እልቂት የሚያስከትለው እኛ ሀገር ነው።የዚህም ምክንያቱ ከአጠቃላይ ህዝባችን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ገበሬ ኢኮኖሚያዊ አቅሙ በቋፍ ላይ የሚገኝ በመኾኑ ነው።ይህ ምንም ምርምር አያስፈልገውም።
ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከኦባማ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢትዮጵይ ላለፉት 12 ዓመታት በተከታታይ “ደብል ዲጂት” የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧን የደሰኮሩት። እርሳቸው ይህን በሚሉበት ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ በክፍሎች እጅግ በርካታ ሰዎች በረሀብ ምክንያት ቀያቸውን ጥለው እየተፈናቀሉ፣ ጥቂት የማይባሉ የቤት እንሥሳትም በየሜዳው እየረገፉ ነበር። “ኢ. ፒ.አር.ዲ ኤፍ” ም ይበለው “አይ. ኤም. ኤፍ”፤ የቁጥር ጨዋታ ሜዳው ላይ ያለውን እውነታ አይሸፍንም።
ለነገሩ የድርቁ ሁኔታ እየተጋለጠ በመጣበት በአሁኑ ወቅትም ሹመኞቻችን መግለጫ ቢሰጡ “ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ ዓለምን እየመራን ነው” ማለታቸው አይቀርም። ለነሱ ዕድገት ማለት በምስሉ ላይ የምታዩት አስፋልት ነው። ከአስፋልቱ ዳርና ዳር እየረገፉ ያሉት ህይወቶች(የገበሬው ሀብቶች) በዕድገት ስሌታቸው አይካተቱም።
“…ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ፣
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? “
በዓሉ ግርማ

No comments:

Post a Comment