Wednesday, August 26, 2015

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ የምግብ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተረጂዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት የተጨማሪ የ230 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል ።
ለምግብ እጥረት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መካከል 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በተያዘው አመት አስቸኳይ የምግብ እርዳታን እንደሚፈልጉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። በሀገሪቱ የተከሰተው የዝናብ እጥረት አደጋ ከተተነበየው የከፋ ነው ያሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ሀላፊዎች በምግብ እጥረቱ የሚጎዱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ይፋ አድርጓል ።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅርት የእርዳታ ማስተባበሪያ ተወካይ የሆኑት ዴቪድ ዴል-ኮንቴ በተለያዩ ክልሎች የተከሰተውን የድርቅ አደጋ እስከ ሚያዚያ ወር 2008 አ.ም ቀጣይ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ። በአፋር ክልል በርካታ እንስሦችን የገደለው የድርቅ አደጋ በአማራ ከልል በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ተመሳሳይ ጉዳት ማድረስ መጀመሩን ነዋሪዎች ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል።
በበልግ ወቅት ያጋጠመው የዘናብ እጥረት በመደበኛው በክረምት ወቅትም በመደገሙ ምክኒያት ችግሩ የከፋ ሊሆን መቻሉን በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ድርጅት ተውካይ የሆኑት ጆን አይሌፍ ለሮይተርስ አስረድተዋል። የተለያዩ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች በበኩላቸው በኢትዮጵያ ያጋጠመው ድርቅ በሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የቅርብ ከትትል እንደሚፈልግ በማሳሰብ ላይ ናቸው።
ምንጭ፤- ኢሳት
ኢሳት የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ ነው!
ኢሳትን ይደግፉ!!

No comments:

Post a Comment