Thursday, February 19, 2015

“ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” የዶ/ር ነገደ ጎበዜ አዲስ መጽሐፍ

negede book

“. . . ይህንን የትግሉን ህዝባዊ ገፅታ ችላ ብለን እነዚህን ሚሊዮኖች የሚያካትት ህዝባዊ የትግል ማእበል ለመቀስቀስ፣ መቀስቀስ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለን የጋራ ስትራቴጂ አውጥተን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር “በእኛና በእነሱ” መሃከል negede bookበተወሰነ የትግል ክፈፍ ከብረት ድስትና ከሸክላ ድስት ፍልሚያ፤ ሸክላ በአሸናፊነት ይወጣል በሚል የአጉል ህልም ዓለም ውስጥ ነን ማለት ይሆናል፡፡” ዶ/ር ነገደ ጎበዜ
በምርጫ 97 ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማቸው ውስጥ ተቃዋሚዎችን ለመወንጀል እየተንጨረጨሩ ያነሱት ስም ነገደ ጎበዜ የሚለውን ነበር። ያ ስም እንደገና ተመልሶ መጥቷል። አሁንም ከመጽሐፍ ጋር ነው የመጣው። ዶ/ር ነገደ ጎበዜ “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” የሚል አዲስ መጽሐፍ ይዘው መጥተዋል።

ቀደም ሲል “ሕገ መንግሥት ምርጫና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ (ከትላንት ወዲያ እስከ ነገ)” የሚል አነጋጋሪ መጽሐፍ ያሳተሙትና የመኢሶን ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት ዶ/ር ነገደ ጎበዜ በዚህኛው መጽሐፋቸው ብዙ የደከሙ መሆናቸው ያስታውቃል። አሁን ያለንበትን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ለመመልከት እስከዛሬ ከነበረው መመሳሰልና መለያየቱን መርምረዋል። በጊዜ ሂደት ውስጥ አሁንም ያልተውናቸው ያልተማርንባቸው ዛሬም ትናንትም የምንደጋግማቸው ቋሚ ስህተቶቻችን ምን እንደሆኑ አይተው ለማሳየት ሞክረዋል።
(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

No comments:

Post a Comment