Thursday, February 26, 2015

የኤፈርት ባለቤት ማን ይሁን??

ምን አልባትም ከምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ኤፈርት ሳይሆን አይቀርም:: ማስተካከያ አለን ባዮች አስተያየት መስጫው ጋር ጠብቁኝ:: አዲሱ የትግራይ ብሄርተኝነት እንደየትኛውም ብሄር ተኮር ብሄርተኝነት የዘውጉን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ በየትኛውም አይነት ሃገራዊ ኪሳራ ላይ ቢሆን ይደራደራል.......በአብሮነት ውስጥ ያሉትን መተሳሰሪያ ገመዶችን ቢገዘግዝ እንኩዋን ጠባብ የብሄርተኝነት ባህሪው ያንን እንዲያደርግ አይፈቅድለትም:: አንዱ በኦሮሞ ፈርስት አመንክዮ ላይ ያንጫጫን ይኅው ለብሄር ጥቅም የሚኬድበት መንገድ ሌሎችን አደጋ ላይ የማያስቀምጥ ለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ አለመቻሉ ነበር....(ይህ ማለት በሃገራዊነት ላይ ስላለው ስለማንቆጣጠረው የማንነትና ስሜት ቅድሚያ ሳይሆን ይህንን የኦሮሞ ቅድሚያነትን ለማረጋገጥ የሚኬድበት መንገድ ትግበራ(practicality) አነጋጋሪ የሚሆንበት አገባብ ስለሚኖር ነው...ቅድሚያ ለኔ የሚለው የዳርዌንያንን አስተምህሮ ስናስተውል) ::

በአዲሱ ትግራይ ብሄርተኝነት ውስጥ የኤፈርት የባለቤትነት ክርክር ከትግራይ ተሻግሮ የማይሄድበት አንዱ መገለጫ ይኅው የትግራይ ፈርስት አመለካከት ነው:: በህውሃትና በትግራይ ብሄርተኝነት መካከል ያለው አንዱ ልዩነት የኤፈርት ሃብት አያያዝና ተጠቃሚነት ነው:: ለመሆኑ ኤፈርት የኢትዮጽያ ህዝብ ሃብት ላለመሆን ምን ምክኒያት አለ?
ምንም እንኩዋን ኤፈርት ግዙፍ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ቢሆንም ኢትዮጽያና ኢትዮጽያውያን እምቅ አቅም ሊፈጥረው የሚችለውን አይነት ሃገራዊ ኢኮኖሚ ስናስብ ኤፈርት እዚህ ግባ የሚባል አይሆን ይሆናል:: ነገር ግን በህግ አግባብና አመንክዮ ኤፈርት የኢትዮጽያ ህዝብ ነው የሚል ወይንም በዚያ ደረጃ አንስቶ ህውሃትን የሞገተ የትግራይ ብሄርተኝነት አልተስተዋለም
ትግራይን መልሶ ለማቋቋም እና በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለማልማት በፈረንጅ 1995 በ2.7 ቢሊየን ብር ግምት ይንቀሳቀስ የነበረው ድርጅት ዛሬ ላይ በግምት 30 ቢሊየን ዶላር አካባቢ በበርካታ የአገልግሎትና ንግድ ስራ ውስጥ ይገኛል ::

No comments:

Post a Comment