Wednesday, September 9, 2015

የአገራችን እውነተኛ ባለቤቶች ለመሆን ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን

የአገራችን እውነተኛ ባለቤቶች ለመሆን ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን፣ በስደት በምንኖርበት አገር ሁሉ ከሚደርስብን ጥቃት ራሳችንን ለመከላከል እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል ይኖርብናል። በደቡብ አፍሪካ የሚታየው አስቀያሚ ሁኔታ በሌሎች አገሮችም ሊከሰት እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል። በተለይ የኢኮኖሚ ቀውስ በሚያጋጥምበት ወቅት ስደተኞች ሁሌም ኢላማ መሆናቸው አይቀርም። በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያን ለህልውናቸው ሲሉ በየአካባቢያቸው እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሟገት ጠንካራ ማህበራትን መመስረት አለባቸው።
በምናየው ነገር ሁሌ መበሳጨት ትርጉም የለውም፣ የተግባር ሰዎች ልንሆን ይገባል። ሳውድ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ስታባርር በውጭ የታየው ጊዚያዊ አንድነት መልሶ ከስሟል። ያንን ሃይል አሰባስቦ የሚይዝ የሲቪክ ድርጅት አለመፈጠሩ ያንገበግባል ። እኛ ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ድርጅት ለመፍጠር ለምን እንደሚሳነን አላውቅም። ጥቃቱም የሚበረታው በእኛ ላይ ነው። ካልተደራጀን ደግሞ ጥቃቱን መከላከል አንችልም። የመጨረሻ ዋስትናችን አገራችን ብትሆንም ለሁሉም የሚሆን አገር እስክትመሰረት ባለንበት ቦታ ሁሉ ተደራጅተን እንታገል።

No comments:

Post a Comment