Thursday, April 11, 2013

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል


የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስር የአማራ ተወላጆችን ለመመለስ የክልላቸው ካቢኔ መወሰኑን በሚመለከት በአገር ቤት ለሚታተሙ ጋዜጦች እና ለኢሳት የሰጡት መግለጫ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ አነጋጋሪነቱን ቀጥሎአል፡የተፈጠረ ስህተት አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ ለማረም መንቀሳቀስ ተገቢ እርምጃ ነውበሚል ሒደቱን አንዳንድምሁራን ያደነቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞእርምጃው የጭንቅት ውጤት ነውበማለት አጣጥለውታል፡፡እነዚሁ ምሁራን ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገሩትበሕገወጥ መንገድ ሰፍረዋል፣ደን ጨፍጭፈዋልበሚል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ የአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ ተመርጠው እንዲባረሩ የሚደረግበት መንገድ ከአፓርታይድ የዘር መድልኦ ተለይቶ የማይታይና አደገኛ ጅምር መሆኑን ጠቁመው ይህን ሁኔታ የመንግስት አመራሮች ተረድተው ስህተቱን አምነው ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት ማሳየታቸው በበጎ መልኩ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡
በጅማ ዪኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው መንግስት የእሳት ማጥፋት ስራበማከናወን ችግሩን ከመሰረቱ መፍታት እንደማይችል ተናግረዋል፡፡ ዋናው ነገር ከላይ እስከታች ያለው አመራርየፌዴሬሽን አወቃቀር ጉዳይ አጣሞ በመረዳት አንድ ክልል በራሱ ተወላጆች ብቻ መያዝ አለበት የሚል የተሳሳተአመለካከት በሰረጸበት ሁኔታ ነገሩ ዓለም አቀፍ ቁጣ በማስከተሉ ብቻየተባረሩት ይመለሱማለት ችግሩን ከመሰረቱ የሚፈታ እርምጃ አይሆንም ብለዋል፡፡በአንድ በኩል ሰዎቹን ሕገወጥ ሰፋሪዎች ናቸው እየተባለ በሌላ በኩል ስህተት ተሰርቶአል ይመለሱ ማለት እርስበርሱ የተምታታና ጭንቀት የወለደው ምላሽ ይመስላል ሲሉአስረድተዋል፡፡ አይይዘውም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ከደቡብ ክልል፣ከሶማሌ ክልል አማሮች እየተመረጡ ተባረዋልያሉት ምሁሩ በነዚያ ጥፋቶች ምንም የማስተካከያ እርምጃ ሳይወሰድ ዛሬ ብድግ ተብሎ ስህተት መፈጸሙን በአደባባይመናገሩ ብቻውን ስህተቱን አያርመውም ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡በግሌ የቤንሻንጉሉ ፕሬዚዳንት መግለጫ አሳዝኖኛል ያሉት ምሁሩእንዲመለሱ ተፈቅዶአል፣ተወስኗል፣ከአማራ ክልልጋር ተስማምተናል፣ተፈራርመናል..”ሲሉ ምን ማለታቸው ነው፡፡የሰዎችን ተዘዋውሮ የመስራት መብት በኢትዮጵያሕገመንግስት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ጭምር ተቀባይነት ያገኘ ሆኖ ሳለ እነሱን ማንፈቃጅ ፣ማን ከልካይ እንዳደረጋቸው የሚያስገርም ነው፡፡ አንድ በአዲስአበባ የሚኖር ዜጋ ብድግ ብሎ በቤንሻንጉልለመኖር ቢወስን ቤንሻንጉሎች ከሰውየው ብሔር ክልል ጋር ተነጋግረው መስማማት አለባቸው እያሉንነውን?…ትልልቆቹ አመራሮች ነገሮችን በዚህ ደረጃ የሚገነዘቡ መሆናቸው በራሱ አስደንጋጭ ነው ብለዋል፡፡መንግስት ከደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ ባለፈው ዓመት በመጋቢት ወር የተባረሩትን የአማራ ተወላጆች በተመሳሳይ ሁኔታ ወደተፈናቀሉበት በመመለስ መልሶ የማቋቋም ተግባር መስራት ካልቻለና በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮቹ ስለፌዴራሊዝም ጽንሰ ኀሳብ ማስተማር እስካልቻለ ድረስ አሁንም በዘላቂነት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደማያምኑ የሕግ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስለተፈናቀሉት ሰዎች ምንም አለማለቱ እንዳስገረው ገልጿል።ይህ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ነው፤ ይህ ካልተዘገበ ሌላ ምን ሊዘገብ ነው?’ በማለት አክሏል።ወጣቱ ፖለቲከኛ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ በበኩሉ የሰዎቹ መመለስ ተገቢ ቢሆንም የደረሰው ቀውስ ግን በምንም ነገር የሚተካ አለመሆኑን ገልጿል።እንኳንስ ቤትን የሚያክል ነገር ቀርቶ አንድ ሰው ጓዳውንና ምኝታ ቤቱን ለመቀየር ቢነሳ ብዙ ችግሮች ይገጥሙታልበማለት የተናገረው ኢንጂነር ዘለቀ፣ ሰዎቹ ያጡት ነገር ብዙ በመሆኑ ቢመለሱም እንኳን የደረሰባቸውን ቀውስ በቀላሉ ለመተካት አይቻልም ብሎአል።የፌደራል መንግስቱን ከተጠያቂነት ለማዳን የሚደረገው ጥረት ተገቢ አለመሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ገለጹየቤንሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስር በአማራ ተወላጆች ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸሙት የወረዳ ባለስልጣናት ናቸው በማለት የክልሉን ባለስልጣናት እና የፌደራል መንግስቱን ከተጠያቂነት ለማዳን ያደረጉት ሙከራ በማስረጃ ላይ ያልተደገፈ ነው በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የህግ ባለሙያ ተናግረዋል።ባለሙያውበሚያዚያ ወር ውስጥ 2004 ዓም ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የሚፈናቀሉ ሰዎችን በተመለከተ በወቅቱ / ለነበሩት ለአቶ መለስ ዜናዊ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት፣ አቶ መለስ ዜናዊ የሰጡት መልስ የፌደራል መንግስት እጅ እንዳለበት የሚያመለክት ነው ብለዋል።የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ጉዳዩ የክልሉ ችግር ነው በማለት የሚሰጡት መልስ ተገቢ አይደለም የሚሉት ባላሙያው፣ ምናልባትም ዋናው ተጠያቂ የፌደራል መንግስቱ ሊሆን ይችላል ሲሉ አክለዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ቤንቺ ማጅ ዞን የተመለሱ የአማራ ተወላጆች ጫካ ውስጥ ወድቀናል ይላሉከቤንሻነጉል ጉሙዝ ከከማሺ ዞን ከያሶ ወረዳ ተፈናቅለው ፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩት የአማራ ተወላጆች ወደ መጡበት ቦታ እንዲመለሱ ቢደረጉም፣ መጠለያ እና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ነገሮች ባልተሟሉበት ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን በቦታው ደርሰው ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል።ተፈናቃዮቹ ህጻናቱም ሆኑ አዋቂዎች ምግብ ሳይመገቡ መዋላቸውን፣ ከአንድ ቀን በሁዋላ ዱቄት ተሰፍሮ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። የቀይ መስቀል ሰራተኞች አብረዋቸው እንደመጡ የሚገልጹት ተፈናቃዮች የተቅማጥ በሽታ በመከሰቱም ሀኪሞቹ ከአቅማችን በላይ ነው እያሉ መሆኑን ገልጸዋል።ተፋናቃዮች አንድም ባለስልጣን መጥቶ እንዳልጎበኛቸው ተናግረው የአማራ ክልል ባለስልጣናት መልሰው እንዲወስዷቸው ጥያቄ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።  አሁንም የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው የተናገሩ ሲሆን፣ የወረዳው ባለስልጣናት በቦታው ተገኝተው ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ስጋታቸውን እንደጨመረ ገልጸዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ክልል በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ የሚገኙ 2 በላይ አርሶአደሮች አንድም ባለስልጣን እንዳላናገራቸው ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ ከሶስት ቀናት በፊት ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ 7 አመራሮቻቸው ተይዘው 24 ሰአታት ከታሰሩ በሁዋላ በይቅርታ እንዲፈቱ መደረጋቸውን ታስረው የተፈቱ አንድ ተፈናቃይ ገልጸዋል።ተፈናቃዩየተዘረፍነው ንብረት ይመለስልን፣ ወደ ቀያችንም እንመለስበማለት በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸው፣ የወረዳው ባለስልጣናትም የቻግኒን ከተማ ህዝብ ጸጥታ ታደፈርሳላችሁ በሚል ሰልፉን እንዲበተን እንዳደረጉና መሪ ናቸው የተባሉትን ሰዎች አስረው እንደለቀቁዋቸው ገልጸዋል። ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ 500 በላይ ሰዎች እንታሰራለን በሚል ከከተማዋ መውጣታቸውን የገለጡት ተፈናቃዮ፣ በአሁኑ ጊዜ 1600 በላይ ሰዎች መፍትሄ አጥተው መቀመጣቸውን ገልጸዋል።ከከማሺ ዞን የተፈናቀሉት እንደተመለሱ ብንሰማም ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉት ግን አሁንም መልስ አልተሰጠንም በማለት ተፈናቃዩ ገልጸዋል።በሌላ በኩል ደግሞ በመተከል ዞን እንዲፈናቀሉ ሲደረጉ ድብደባ የተፈጸመባቸው አንድ የአማራ ተወላጅ፣ የደረሰባቸውን ጉዳት ዘርዝረው አቅርበዋል። ተፈናቃዩ እንዳሉት ድብደባው የደረሰባቸው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተጠይቀው አልወጣም የሚል መልስ ከሰጡ በሁዋላ ነው ።የክልሉ ፕሬዚዳንት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ካሳ እንደሚያገኙ ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment