Friday, April 19, 2013

በጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ለአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ በሚል የተዘጋጀውን ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ በማድረግ አኩሪ ታሪክ ፈፀሙ!!!a


በጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ለአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ በሚል የተዘጋጀውን ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ በማድረግ አኩሪ ታሪክ ፈፀሙ!!!

በሳኡዲ አረቢያ በጅዳ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች በጅዳ የኢትዬዪያ ቆንስላ ፅ/ቤት የአባይ ግድብ መሰረት የተጣለበት 2ኛ አመት ክብረ በአል በደማቅ ሁኔታ በማክበር ለአባይ ግድብ ኢትዬጲያውያኑ ቦንድ እንዲገዙ ለማድረግ ያዘጋጀውን ፕሮግራም አከሸፉ፡፡

ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞቹ በቆንስላው በተዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መዘጋጀቱን በመቃወም ልማት ከነፃነት ቡሃላ ነው በማለት በሃገር ቤት ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ ሳያቆም ሽራፊ ሳንቲም በልማት ስም እንደማለይለግሱ በተግባር ማሳየታቸው ተሰምቷል፡፡ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞቹ በቆንስላው የተዘጋጀው ፕሮግራም ከምሽቱ 2 ሰአት እንደሚጀምር ጥሪ ተደርጎ የነበረ ሲሆን የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ በመፍራት ያሰብነውን ፕሮግራም ለማካሄድ እንቅፋት አይሆኑብንም ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች በድብቅ መልዕክት በማስተላለፍ ከምሽቱ 1 ሰአት ላይ እንዲገኙ እና የተቀረው ሙስሊም ሰአቱን አክበሮ ሲመጣ አዳራሹ ስለሞላ ተመለሱ ለማስባል አቅደውት የነበረው ሴራ በሙስሊሙ አንድነት ሙሉ ለሙሉ ሊከሽፍ መቻሉ ተሰምቷል፡፡ከመግሪብ ሰላት በፊት ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞቹ ወደ ቆንስላው ፅ/ቤት ያመሩ ሲሆን የተወሰኑ ሙስሊሞች ከገቡ ቡኃላ የአዳራሹ እና የቆንስላው በር እንዲዘጋ በማድረግ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞቹ በበሩ ላይ እንዲቆሙ መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡

የቆንስላው ሃላፊ አቶ ዘነበ በሃገር ቤት ሙስሊሞች ላይ እደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ ሳይቆም ሽራፊ ሳንቲም አንሰጥም ለማለት ወደ ዝግጅቱ ቦታ ያመራውን ሙስሊም ህብረተሰብ ለሳኡዲ ፖሊሶች በማመልከት እንዲያዙ ለማድረግ ሲሞክር መታየቱ አብዛኛውን ኢትዬጲያዊ አሳዝኗል፡፡ሙስሊሞቹም ያለ አንዳች ማፈግፈግ በቦታቸው በመሆን ኮሚቴዎቻችን ይወክሉናል፣ከልማት በፊት መብታችን ይከበር የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ቦታውን በተቃውሞ እንዳደመቁት ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ቀደም ብለው ወደ ቆንስላው ፅ/ቤት ገብተው የነበሩትን ሙስሊሞች አቶ ዘነበ ለሳኡዲ ፈጥኖ ደራሽ ለሚባሉት ልዩ ሃይሎች በማመለከት አሸባሪዎች አጥር ገንጥለው ገብተውብናል እና እርዳታቹን እንሻለን በማለት በሙስሊሞቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አሳልፈው መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ላ ሆኖም ፖሊሶቹ ግቢውን ዞረው በመመልከት የተገነጠለ አጥር አለመኖሩን በመረዳታቸው እና እጅግ ስነ ስርአቱን የጠበቀ በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም ህብረተሰብ በበሩ ላይ ቆሞ በመመልከታቸው አሸባሪዎች ወረውናል መባሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን ተረድተው አንዳችም ነገር በሙስሊሞኡ ላይ ሳይደርስ መለቀቃቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በሰው ሀገር ሆነው ያውም ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት ሀገር ይህን መሰል ልዩ ተቃውሞ ማድረጋቸው የጅዳ ሙስሊሞችን ልዩ እንደሚያደርጋቸው ተገልፆል፡፡ለአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢየ ተብሎ የተጠራው ስብሰባ በሙስሊሙ አንድነት እና ጀግንነት ሙሉ ለሙሉ መሰረዙን ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ታግተው የነበሩት ሙስሊሞችም በሙስሊሙ አንድነት እንዲለቀቁ በመደረጉ የቆንስላው ፅ/ቤት በልዩ የተቃውሞ ተክቢራ መድመቁ ተሰምቷል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም በሃገር ቤት ሙስሊሞች ላይ መንግስት እየደረሰ ያለውን ግፍ እና ስቃይ እንዳንገሸገሻቸው በተግባር ገልፀዋል፡

፡የኢትዬጲያ መንግስት ያዘጋጀው ፕሮግራምም የታለመለትን ግብ ሳይመታ በከፍተኛ ውርደት ሳይሳካ መጠናቀቁን የጅዳ ሙስሊሞች አስታውቀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment