Monday, April 29, 2013

ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ስለምትሆንበት ሁኔታ በተለይም የህግ አገልግሎት ዘርፉ ጋር በተያያዘ ወይይት ተካሂዶ ነበር።


በውውይይቱ ላይ ከሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከህግ ትምህርት የተመረቁና በህግ ሙያው ላይ ብዙ አመት የሰሩ ጠበቆች ተገኝተው ነበር። ከእነሱ መካከል አንድ አንጋፋና ታዋቂ ጠበቃ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሲሰጡ:-
እናነተ አያቀረባችሁት ያለው ነገር መሬት ያልወረደ ነገር ነዉ። የዉጭ ሀገር ተቛም ወይም ግለሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ መቶ ስለሚሰራበት ሁኔታ እና ምን አይነተ ገደብ(restrictions) መጣል እንዳለበት ነው ሁሉም ጠበቃ ተበታትኖ የየራሱን እሚሰራበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው ።ሁሉም ጠበቃ በአንድ ተቛም ስር (legal firm) እሚሰራበት ሁኔታ አልተመቻቸም፣ፍርድ ቤት ስንሄድ በእውቀት ያልዳበሩ እና ያልበሰሉ ዳኞችን ነዉ እምናገኘው ዳኛ ከተሆነ በኋላ ጠበቃ እሚኮንባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ትመስለኛለች። አንድ የህግ ባለሞያ ጠበቃ ሆኖ በቂ አውቀት ከያዘ በህዋላ ፣ከሰከነና ከበሰለ በኋላ ፣ከመንግስት ተፅእኖ ቀርቶ ከራሱ ተፅእኖ ተላቆ መሆን አለበት።
እዚህ ሀገር የተገላቢጦሽ ነዉ በዘሁኑ ወቅት እኔም ሆነ እማውቃችው ጓደኞቼ የፍቤት ጉዳይ ብዙም አንይዝም ።የፍትህ ስርአቱ በመበላሸቱ ምክነያት እየተበሳጨን ለበሽታ ተዳርገናልበማለት በብዙ ምሬት እና ቅጭት ተናገሩ። ሌሎች ጠበቆችም ተመሳሳይ ሀሳብ ሰንዝረዋል ።ከላይ የተፈውን የተናገሩት ጠበቃ ሌላም ልብ የሚነካ ንግግር ተናግረዋል።
እኔ ሀገሬን በጣም ነዉ እምወደው የወጣትነት ዘመኔን እጅግ እምወዳችዉ ጓደኞቼን ገብሬአለሁ። እንድምፈልገው መጠን ሀገሬን ማገልገል አልቻልኩም ህግ 
ሲወጣ እንደማህበር ያለንን አስተያየት አያማክሩንም። ባይገባቸው ነው እንጂ እምንጠቅማቸዉ እኛ ነበርን ።የእነሱ ሰዎች የሚነግሯቸዉ እነሱ መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነው። እነዚህ ችግሮች ሳይቀረፉ ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ሆነች አልሆነች ለእኔ ትርጉም የለውም
አኝሁ ጠበቃ በስተመጨረሻ ላይ የልዩነት ሀሳብ አለኝ ሲሉ ሰብሳቢው ደሞ አይ ሰአት ስለሌለ በዚሁ እንዝጋው አሉ። ጠበቃው መልሰውእዚህ እንዃን እንድንናገር ይፈቀድልንበማለት ሲመልሱ ሁላቸንም ሳቅን። ሳቃችን ትክክል ለመሆነናቸው ማረጋገጫ አስመሰለብን።
ሌላው እኔም እምስማማበት ሀሳብ እንዲህ በተዘበራረቀ የፍትህ ስርአት ያለባት ሀገር የዳበረ የፍትህ ስርአት ካላቸው ሀገሮች መተው ለመስራት የሚሞክሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የተወሳሰቡ ችግሮች ሊገጥማቸው እንደሚችል መገመት አያዳግትም።በሌላ በኩል ካንር የህግ ባለሞያ እንደተሰነዘረው የአለም ንግድ ድርጅት ዋነኛ መርህ በርህን ክፈትልኝ በሬን እከፍትልሃለዉ ነው።ኢትዮጵያ እምትልከዉ ነገር የቱን ያህል ሰፊ ሆኖ ነው በረዋን የምትከፍትው የሚለው ነገር በራሱ አከራካሬ ነው።

ከህግ አገልግሎት ውጭ የተነሳዉ ኢትዮጵያ አባል ለመሆን ቴሌ ኮምንኬሽን የባንክ ስራን ወደ ግል ማዞር የሚለው ነው። ኢትዮጵያ ባንኮችን ወደ ግል ሙሉ በሙሉ ለማዞር በተወሰነ ደረጃ ብትስማማም የቴሌኮም ስራን ወደ ግል ማዞር ላይ ግን ሊዋጥላት አልቻለም። ለነገሩ እንዴት ሊዋጥላቸው ይችላል ቴሌኮም ስራዉን እረሰቶ ስልክ እያስመጡ መሸጥ አና ሲም ካርደ መቸብቸብ ዋነኛ ስራዉ አደርጎታል። ስልክ በተደወለ ቁጥርይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም አምትለዋን ሴትዮ ቀይሮመስመር እያስተካከልን ነውና እባኮን ትንሽ ይታገሱንበሚል መቀየር እንዃን መቀየር ተስኖታል።
በዚህም ተባለ በዚያም ኢትዮጵያ ሀገሬ ያለም ንግድ ድርግት አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበች 10 አመት አልፏታል። ቴሌኩምና ሌሎች በመንግስት የተያዙ ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር አሁን ባሉት በመንግስት ባለስልጣናት ገገማነት ምናልባት ሀምሳ አመት ሊፈጅ ይችላል ።ግን 2014 ኢትዮጵያ ያለም ንግድ ድርጅት አባል ትሆናለች እያሉ ይፎግሩናል።

No comments:

Post a Comment