Tuesday, April 9, 2013

ዛሬ አይደለም የጀመረው !

ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ እስከዛሬ አንስቶ ወያኔ በአማራው ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና መከራ በቀላሉ ተነግሮ አያልቅም በአሁኑ ጊዜ አማራው የሚደርስለት አጥቶ በወያኔ የዘረኝነት ቀንበር እየተጨቆነ እየተመዘበረ ይገኛል ወያኔም ዘር ማጥፋቱን በሰፊው አጠናክሮ ቀጥሎበታል መጥቀስ ካስፈለገም ወያኔ ከበርሃ አንስቶ የአማራን ህዝብ ሰርጎ በመግባት ደርግ ናቸው የሚል አመለካከት ስለአለው በጎንደር፣ ዳባት፤በበለሳ በደብረታቦር፣በአርማጭሆ በጋይንት፣ በወሎ ላሊበላ፣ በቆቦ፣ በሰቆጣ በአጠቃላይ በአሁኑ አማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው ቦታ በርካታ የአማራ ህዝብ ተገላል እስከ አሁን ጊዜ በትግራይ እስር ቤቶች ታስረው ይገኛሉ አብዛኛወቹ የት እንደደረሱ አይታወቁም፣ትግራይ ውስጥ ደንቆሮ ዋሻ እስር ቤት የሚገኙ የአማራ እረኞች አሁንም አሉ፤፤
ወያኔ ስልጣን ከያዘ ወዲህ ጸረ አማራነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ለምሳሌ መጥቀስ ካስፈለገ፣

1ኛ.ስልጣን በያዘ ማግስት አማራን ከሌሎች ብሄር በሄረሰብ ነጥሎ አማራ ባልሆኑ ከሌሎች ብሄረሰብ የተውጣጡ አካላትን የብሄሩ ተወካይ አደረገ፣፣
2ኛ.በአማራ ክልል ብጥብጥ በማስነሳት አማራን መግደል ማሰር ምሳሌ በ1985ዓ.ም በጎንደር እየሱስ በሀይማኖት ሰበብ ንጹሃንን በመትረጊስ ጨፍጭፋል በርካታወች ሙተዋል በርካታወች አካለ ጎደሎ ሁነዋል በርካታወች እስከ አሁና ሰአት እስር ቤት ይገኛሉ፣በበደኖ በአርባጉጉ በጅማ ተጨፍጭፈዋል
3ኛ.ሰፋፊ የእርሻ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ የተቃወሙትን ገላል አስራል ከሀገር እንዲሰደዱ አድርጋአል፣ጎንደር ባታ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው ታስረዋል ይገኛሉ፤የጎጃም ገበሬ ከእርስቱ ተፈናቅሎ ልጅና ሚስቱን ጥሎ እየተሰደደ ይገኛል፤፤
4ኛ.በፓስተር ታምራት ላይኔ ትዕዛዝ በሱማሌ ክልል የሚገኙ አማራወች ተዘርፈዋል ተገለዋል ምሳሌ በጎዴ ከተማ መጀመርያ በሰርግ ቤት ቦንብ ተወረወረባቸው ከዚያም በሀዘን ቤት አሁንም ቦንብ ተወረወረባቸው ብዙ አማራወች ለሞት ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል በጎዴ የነበሩት እንዲፈናቀሉ ተደረገ ይህ ትዕዛዝ የወያኔ ነው
5ኛ.ወያኔ ስልጣን እንደያዘ ከወሎ ከአልዋ ምላሽ ብሎ ሰፊና ለም መሬት ወስዳል ከጎንደር ሙሉ ወልቃይት ጠገዴን ከፊል የአርማችሆን መሬት ወደትግራይ ወስዳል ይህአልበቃው ብሎ የዋልድባን ገዳም በልማት ስም እያረሰው ይገኛል የጎንደር አድባራት ተዘርፈው ወደትግራይ ተወስደዋል፤፤
6ኛ.ከአብደራፊ አንስቶ እስከ ቢኒሻንጉል አዋሳኝ ሰፋፊ የአማራን መሬት ለሱዳን ሰጥታል የተሰጠው መሬት ከአብደራፊ፤ ኮረደም ኮርሁመር፤ስናር፤ደለሎ፤ኮርጅሀሙስ፤መተማ፤መርትራድ፤ቱመት፤ሽንፋ፤ነብስገብያ ታላቁን ፓርክ የአላጥሽ ይዞታ በአጠቃላይ አጼ ቴወድሮስ የተወለዱበን ለሱዳን ሰጥቶብናል፤፤
ይሁንና ከሱዳን የተፈናቀሉ ትግረኛ ተናጋሪ በመተማ፤በኮኪት፤በኩመር በቱመት ፤በአብደራፊ፤በአርማችሆ አስፍሮ አማራን ከቦታቸው አፈናቅሎ ይገኛል ይህ አልበቃ ብሎ በአማራ የጠረፍ ከተሞች ከመቶ 95ፐርሰንት ነጋዴወች የህወሃት ዘር ያላቸው ናቸው
7ኛ.አሁንም ከወሎና ከጎንደር ቆርሶ የወሰደው አልበቃ ብሎት ሰፋፊ መሬት ለእርሻ ወስዳል ምሳሌ የአዜብመስፍን ወንድም 3000ሄክታር መሬት ሽንፋ አለው ታች አርማችሆ 4000ሄክታር አለው እነስዩም መስፍን ከቤተሰባቸው ጋር በገለጎ 10000ሄክታር መሬት በላይ ይዘው ይገኛሉ የአርማጭሆን ገበሬ አፈናቅለው የትግራይ ገበሬ አስፍረዋል የህዝቡን እሮሮ ለሚያፍኑ 200ሄክታር መሬት ወያኔ ሰጥቶአቸዋል 
ደለሎ ከሱዳን የተረፈው በትግሬወች ተይዘዋል ኪሮስ ላንባ 4000 ሄክታር ገብረስላሴ 2500ሄክታር የአርማችሆ ገበሬ ከቦታው እንዳይደርስ ተደርጋል፤የአማራ ገበሬ በስደት ወደሱዳን እንዲጋዝ ተደርጋል በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እንዲታሰሩ እንዲገደሉ እንዲዘረፉ እየተደረገ ይገኛሉ በዚህም ተዕዛዝ በገላባት፤በኩኒና፤ በዶካ፤በገዳሪፍ፤በከሰላ፤በመደኔ፤በባሶንዳ፤በካርቱም፤በእምዱርማን፤በፖርትሱዳን፤እስርቤቶች ውስጥ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ እስረኛ ይገኛሉ ከግማሽበላይ አማራ ናቸው፤በዚህም ሱዳን ገበሬ ቢገል ተጠያቂው የገበሬው ቤተሰብ ነው፤ምሳሌ በ1999 ዓ፣ምደለሎ ላይ የሱዳን ወታደሮች 10ገበሬወችን ገለው በሰሊጥ አገዳ አቃጥለዋቸዋል በ2001 ዓ.ምበቱመት አካባቢ 9 አማራወች የፊጥኝ ታስረው ተገለዋል ቤተሰቦቻቸው እሬሳ ቢጠይቁ እንካን ወያኔ ለምን ነው የጠየቃችሁ ብሎ ቤተሰባቸውን አስራል በ2000 ዓ.ም ነብስ ገቢያ ከተባለው ቦታ 28 ኢትዮጵያኖችን አግተው ካርቱም ወስደው ሱዳኖች ቢያስሩ ወያኔ ደን ሲጨፈጭፉ የተገኙ ብሎ በካርቱም ፍርድ ቤት ከአንድ አመት እስከ ሁለት አመት እንዲታሰሩ አድርጋል
8ኛ.ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ከአርሲ፤ከሀረር፤ከአፋር፤ከባሌከጅማ፤ ከወለጋ፤ከጎዴ፤ከደቡብ፤በአጠቃላይ ከአራቱ ማዕዘናት አማራ በግፍ አፈናቅላል አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል ከሰሞኑ እንካን ከቢኒሻጉል ተፈናቅለው ሲወጡ 59ሰወች ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ አልፋል ይህንዘግናኝና የዘርመጥፋት እየሰሙ ዕያዩ ዝም ያሉ አማራ በወገኑስቃይ የሚደስት ካሉ ከመጠየቅ አያመልጡም ስለዚህ ሁሉም ዛሬ ነገ ሳይል ለወገናችን እንድረስ እላለሁ ስራየ ማቄ ጨርቄ የሚባልበት ጊዜ አይደለም ትውልድ የማዳን ጊዜው አሁን ነው ዝም ካልነ ወያኔ ግፉን አጠናክሮ ይቀጥላል
9ኛ.ወያኔ በአማራ ክልል ሸዋሮቢት፤ደብረታቦር፤ወልደያ ፤ጭልጋ ፤ደሴ፤ባህርዳር፤አዲስዘመን፤በኢትዮጵያ አሉ የተባሉትን እስር ቤት ለእኛው ማሰሪያ አስገብቶልነል፤ ነገሩ ወያኔ አማራውን በቁሙ ካሰረው 22 አመት አለፈው የአማራ ህዝብ ከወያኔ ቤት ያለው ጀግንነት ከእኛ ቤት የለም እንዴ ከነሱቤት ያለው ወኔ ከእኛ ቤትየለም እንዴ ጀግንነቱም ወኔውም አቅሙ ከእነሱ የሚበልጥ ነው ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳንል መነሳት አለብን ፤በዚህ አጋጣሚ አማራ ሁነህ ከወያኔ ጉያ የተደበቅህ ከአሁኑ ወደ ወገንህ ተመለስ ያለበለዚያ ሆድህ አታሎህ በወገንህ የምትዘምት ከሆነ ልጅ ያለህ በልጅህ እናት ያለህ በእናትህ በአጠቃላይ ለቤተሰብህ ጦስህ እንዳይደርስ ተጠንቀቅ ፤
በአጠቃላይ የወያኔ በአማራው ላይ የሚያሳየው ግፍ በቃህ ልንለው ከሆነ እኛው አማራወች ነን፤ የተኛህ ተነስ ጊዜው አሁን ነው ሆድክን ወደህ ህዝብህን ለወያኔ አጋልጠህ የሰጠህ ተጸጸትና ወያኔን ተፋለም ወያኔ ስልቱ ሆድአደር አማራን በማደራጀት አማራውን የሚበቀል እናም ከወያኔ ጋር ሁነህ ህዝብህን የበደልክ አሁንም አልረፈደብህም ተነስ የወገንህ ሰቆቃ ይብቃህ እንበለው ወያኔ በኢትዮጵያ ያደረሰው
ተዘርዝሮ አያልቅም ስለዚህ የወያኔን ሴራ በቃህ የምንልበት ጊዜ አሁን ነው፤ወገኔ ዛሬ ምን እበላለሁ ብለህ ወያኔን ሙጥኝ ብለህ ነጻነትህን አሳልፈህ አትስጥ ነጻነትካለ ሁሉም አለ ነጻነት ከለለህ የጋማ ከብት ነህ ወያኔም ግቡና አላማው ይህ ነው መቶበመቶ ግብ መቶለታል የአማራ ህዝብ ወያኔን ከሚታገል ጋር ሁኖ መታገል አለበት፤
ለኢትዮጵያ ሀገሬ ለወገኔ ብለን እንነሳ ጦሩም ሆነ ፖሊስ ሀይሉ የወያኔን ሴራ ተገንዝቦ ከህዝብ ጋር መሆን ጊዜው አሁን ነው ዛሬ በሰራዊቱ የትግሬ የበላይነት አለ ሁሉም ይህንያውቃል ስለዚህ የወያኔ አሽከር ከመሆን ወገንህን አድን ዛሬውን አድርገው አትጠራጠር ታሪክ ስራ ወገንህ ይበልጠሓል የወያኔ ዘረኝነት በሰራዊቱ የከፋ ነው እራስህን አታታል ለወያኔ ከመሞት ለወገንህ ሙት ዛሬ ወያኔ በ1987 የቀነሳቸውን ታጋዮች ጠርቶ ዳርፉር ፤አብየ፤እየላከ በሰላም ማስከበር እየላከ ደህና ገንዘብ እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል አንተ ግን ሱማሊያ ገብተህ በጥይት አረር ትቆላለህ ወገንህን እንድትገል እየተደረገ ነው ስለዚህ በያዝከው በህዝብ ንብረት ወያኔን አስወግድ ጊዜው አሁን ነው ወገንህ እየተፈናቀለ እየተዘረፈ እየተገደለ እየታሰረ እየተሰደደ አንተ ወያኔን የምታገለግለው ከሆነ የወገንህ ስቃይ ይቀጥላል ወያኔም አጠናክሮ ይቀጥላል ስለዚህ ሳታመነታ የህዝብህን የሀገርክን ውድቀት ታደግ ድል ለሀገሬ ነጻነት ለህዝቤ እመኛለሁ፤ከአሁን በኃላ ወያኔን እጅን አጣጥፎ ማየት በአለም ላይ ታይቶ የማያውቅ በደል እንደሚያደርስ ነው ስለዚህ ወያኔን በቃህ ብለን የምንታገለው ጊዜው አሁን ነው ፤፤
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር፤፤

No comments:

Post a Comment