Sunday, April 7, 2013

ኢትዮጵያ ወደአደገኛ አቅጣጫ እያመራች ነው (ጥብቅ መረጃ)


በከፍያለው ገብረመድኅን

ሀቁን እንነጋገር ከተባለ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት አገር አይደለችም። ይህ ማለት ግን ለጥቂቶች መንግስተ ሰማይ አልሆነችም ማለት አይደለም። ፍሬ ነገሩ ግን ሥልጣን ላይ ካሉት ስዎች ጋር በማበር የምዕራብ መንግሥታትና ኩባንያዎቻቸው፡ ጥቅሞቻቸውን ለማራመድና፡ አሁን ያለውን ስቴተስኮ እንዳለ ለማቆየት የፈልጉትን ያህል ቢደስኩሩም፤ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባይተዋሮችና በብዙ መልኩ ሕይወታቸው በአረብ አገሮች በግርድና ላይ ካሉ ወገኖቻችን ጋር ያለው ልዩነት መጠነ ጠባብ እየሆነ መምጣቱን መሸፈን አልቻሉም። በሌላ አባባል፤ የስው ልጅ ውሎውና በቀኑ መጨረሻ ላይ በስላም ወደጎጆውና ቤተስቡ መመለሰሱ ዋስትና በሌለው ሁኔታ ውስጥ፤ ባልታሰበ ቀንና ስዓት ዜጎች ንብረታችውን በመንግሥት እንዳይነጠቁ የሚሰጉበት፤ ከሁሉም የከፋ ደግሞ ወደእሥር ቤት እንዳይወረወሩ፤ ልጆቻቸው ከሀግራችው አስፈሪ ሁኔታ በሥውር ለመሸሸ በሚያደርጉት ከሀገር የመሰደድ ሁኒታ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የሚሰጉበትበአጭሩ ሕዝቡ አንገቱን ደፍቶ ለመኖር የተገደደበት ወቅት የነጻነትና የሰላም ጊዜ ነው ብለው የሚያስቡ ግለስቦች ከራሳቸው ምቾት ባሻገር ማየት የተሳናቸው ብቻ ናችው።
በየትኛውም ትርጓሜ፤ ይህ ሁኒታ በአንድ በኩል ከባርነትና በሥጋት ከተወጠረ ሕይወት በሌላ በኩል ደግሞ ከስላማዊና ነጻነት ጋር ሲወዳደር፤ በጉልህ የሚታየው የኢትዮጵያውያን ሕልውና ከፍርሀትና ሰቀቀን ነጻ እንዳልሆነ ነው።
Freedom House ይህንን ሁኔታ ቀደም ብሎ በመገንዘቡ፤ ላለፉት ዓመታት በተለይም 1998 – 2012 ባሉት ጊዜያት በስብአዊ መብቶች አክባበር ረገድ ኢትዮጵያ እንዴት እንዳሽቆለቆች በተከታታይ ዓመታዊ ረፖርቶቹ ሲያቀርብ ከርሟል። ለምሳሌ 1998 የወጣው ሪፖርት የፖለቲካና ሲቪል መብቶችን አይያዝ በተመለከተ እንዲህ ሲል ዝግቦ ነበር:- “Ethiopia’s civil liberties rating changed from 5 to 4 due to improvements in civil society and greater economic freedom.”
በዚያን ጊዜ የታየው መሻሻል የኢትዮጵያ የስብአዊ መብቶች ይዞታ በመጭው ዓመታት ይበልጥ ይሻሻል የሚል አመለካከት ፈጥሮ ነበር። ይሁንና በሚቀጥለው ዓመት የወጣው 1999 .. ሪፖርት እንደበፊቱ ተስፋ የቋጠረ አልሆነም። ጭብጡም እንዲህ ይላል:- “Ethiopia’s political rights and civil liberties ratings changed from 4 to 5 due to limitations on opposition political parties and civic organizations to undertake activities and disseminate information.”
Freedom House የአንድን ሀገር የስብአዊ መብቶች ይዞታ የሚለካው በሶስት መሥፈርቶች ነው። እነዚሀም () የዜጎች ነጻነት መከበር () የዜጎች ሲቪል መብቶች መረጋገጥ እና () የዜጎች ፖለቲካዊ መብቶች መከበር ናቸው። በእነዚሀ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ አንድም ጊዜ የዜጎች ነጻነት ሙሉ ለሙሉ የተከበረባት አገር ተብላ ተሰይማ አታውቅም። 12 ዓመታት “Partly Free” ስትባል ከርማ 2011 ጀምሮ ጭልጥ ብላ ወደ “Not Free” ተሸጋግራ፤ አሁንም በዚያ ጎራ ትገኛለች።
ወደዚያ ከገፋፏት ድርጊቶች መካከል በሁለቱ መለኪያዎች፤ ማለትም በዜጎች የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች አከባበር ያሳየቻቸው እንቅስቃሴዎች እጅግ ዝቅተኛ ከመሆን አልፎ ወደ መጥፎ በመሸጋገራቸው ነው። ለምሳሌ፤ 2011 ወደ “Not Free” ተብላ ከተሰየመች በኋላ፤ በዜጎች የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች መከበር ያገኘችው ነጥብ በእያንዳንዳቸው ስድስት ከስድስት ነው። 1999 .. ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለቱም እነዚህ መለኪያዎች 5/6 5/6 ስታገኝ ከርማ:2011 በኋላ፤ ማለትም በገሀድም መለስ ብቸኛ መሪ ሆኖ ከወጣና የኢትዮጵያን ልማታዊ መንግሥት ካውጀ በኋላ ከላይ እንደተጠቀሰው ሀገሪቱ ሙሉ ነጻነት የሌለባት ተብላ ተፈርጃለች። 2005 .. የመንግሥት ኅይሎች በአደባባይ ሰለማዊ ሠልፈኞች የረሽኑበት ሁኔታ እንኳ በከለር ኮድ (አምበር) ማስጠንቀቂያና ጠንካራ የቃላትና የፖለቲካ ውግዘት ነበር የታለፈው። ለአንድ አገር ክፍተኛው የፖለቲካ ውድቀት፤ የመጨረሻውንስድስት ክስድስት ማግኘት ነው።
Freedom House ለመጀመሪያ ጊዜ የመስብስብና የመደራጀት ነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ በገህድ አደጋ ላይ መውደቁንያጋለጠው 2003 .. ሲሆን: ያን ጊዜም እንዲህ በማለት የዘገበው:- “Ethiopia received a downward trend arrow due to the government’s response to civil unrest that has included heightened restrictions on freedom of assembly and organization.”
የድርጅቱ ይህ አመለካከት በምንም መልኩ አልተዛነፈም። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያርፉ: Freedom House በማግሥቱ የላከው የኅዘን መግለጫ ብዙ ቁም ነገር የያዘና ሀግሪቱ የወደቅችበትን አስከፊ የፍርህትና የነጻነት መጥፋት በሚገባ የሚያመላክት መሆኑን ከመሆኑም ባሻገር እጅግ በሚገርም ሁኔታ የወደፊቱን የሀገሪቱን ችግር በመጠኑም ቢሆን የዳሰሰ ነበር።
“While showing authoritarian tendencies from the beginning of his rule, Meles’s government initially adhered to a range of democratic standards. As the years passed, his leadership style became increasingly iron-fisted. Ethiopia’s designation in Freedom House’s Freedom in the World report declined from Partly Free to Not Free for events in 2010, as the government grew more hostile toward political opponents, media critics, and civil society activists. The country was also designated Not Free in parallel reports on press freedom and internet freedom. Freedom in the World registered a further decline for Ethiopia the following year, citing the misuse of antiterrorism laws to punish opposition activists and journalists. Given Ethiopia’s tragic and bloody political history—first under Emperor Haile Selassie, then under Mengistu—Meles’s refusal to institute governance norms based on democracy and human rights principles is an important and thoroughly unhappy part of his legacy.”
ከላይ የኃዘን መገለጫ ውስጥ ይተጠቀስው ሪፖርት (Freedom in the World 2011) እንዲህ ሲል ነበር የኢትዮጵያን የነጻነት ሁኔታ የመዘገበው:-
“Ethiopia’s political rights rating declined from 5 to 6, its civil liberties rating from 5 to 6, and its status from Partly Free to Not Free due to national elections that were thoroughly tainted by intimidation of opposition supporters and candidates as well as a clampdown on independent media and nongovernmental organizations.”
2010 በተፈጸሙት ገሃዳዊ የምርጫ ማጭበርበር፤ የመንግሥት ኅይልን መጠቀም፤ የሕዝብ መገናኛ አውትሮቹን በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በማፈኑ አገር ለማስተዳደር ብቃት እንደሌለው መለኪያ ተደርጓል።
ሀገር ተቆረሰች፡ መለስና ሕውሃት እንዲያውም ብርታት አገኙ። አበሻ ወድግል ጥቅሙ አደላ። ሽፍታ መንግሥት ሲሆን፤ ዘራፊ ኅይሉን የመንግሥት የጦር ኃይል ያድርግና፤ የሽፍትነት ባህሪው ስለማይለቀው ሕገመንግስታዊ ድጋፍ አግኝቶ የሀገር ምዝበራም ሕጋዊነት ያገኛል። ዘመናዊ ሽፍቶች ስለሆኑ፤ ሁሉን ያሞኙ መስሏችው (የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ) EFFORT አቋቋመው። የሀገርን ሀብት በሼር ተከፋፍሉት። ጄኔራሎቹ ዛሬ የሐር አንሶላ ኮስኮሰን እያሉ፡ በትዕዛዝ የተስሩ አንሶላዎች ክሆንግ ኮንግ ያስመጣሉ። በየስድስት ስዓት ርቀት ውስጥ በስም የመከላክያ ሚኒስቴር ህብት የሆኑ ሆቴሎች እንዲሠሩ ወይንም እንዲገዙ ወስነው ለእነዚህ ዘምናዊ መሣፍንት መዝናኛ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
መለስና ሕወሃት ሥልጣን ከያዙበት ቀን ጀምሮ የፈለጉትን በአደባባይ ረሽኑ፡ ቀሪውን እሥር ቤት በዘር በዕድሜ እለዩ ትውልድ አኮላሹ። ሌሎቹ ብሄረስቦች እነርሱ የሚያዳርጉትን ሁለት ዕጥፍ አድርገው ዘረፉ፤ ሕዝቡን ረገጡ። የኢትዮጵያ ውርደት መጠኑን የሚገንዘብ የተሻለ ትውልድ ካልመጣ በስተቅር የጥፋት ውሃ እያንዳንዱ ዜጋ እያቀና ነው። ዛሬ በገሃድ አገር እየተመዘበረች ነው። ብዙው አገር ለቆ ተሰደደ፤ ሀገሪቱም፡ ነጻ ሆና ያልኖረች ይመስልብላ የጀመረችው ገንባታም 20 ዓመታት መከራ በሁላ ከባሕር ዳር እንደስማነው፤ ድንብር ግትር እየሆነ ነው።
መታውቅ ያለበት፤ ሕወሃት እጅግ በሚያስከፋ መንገድ የስው ልጆችን መብቶትችና ነጻነቶች መግፈፍን የጥንካሬውና ሥልጣንን መቆናጥጫው መሣሪያው ስላደረገው፤ ከሌሎች ጥፋቶችና ክፋቶች ይቆጠባል ብሎ ማስብ የዋህነት ነው። እንዲያውም፤ ኢትዮጵያን የማዋረዱን ሥራ ገና አላጠናቀቀም። በመስጊዶችና በኔተክርስቲያኖች የሚፈጸመው ባዕድ ደባ ይህንኑ አመላካች ነው። ችግሩ ቀጣዩ የጥፋት ተግባር የሚካሄደው በአዕምሮም ሆን ኅሊና ምንም ዐይነት ብቃት በሌላቸው ስንኩሎች በመሆኑ፡ ጥፋቱ ከእዚህ በታች እንደተመለከተው የክፋና የተፋጠነ ይሆናል።
ዘር የማጽዳት ፕሮግራም በምድረ ኢትዮጵያ (Ethnic Cleansing)?
በተለይም በተደጋጋሚ በማን አለብኝነት ሲካሄድ የነበረው ሕዝቡን የመክፋፈል ፖለቲካ ወደ የዘር ማጽዳት ዘመቻ (Ethnic Cleansing) ከተለወጠ ስንበት ብሏል። ሕወሃት የመጀመሪያ ረድፍ ጠላቶቹ አድርጎ የሚያያችውን ኦርሞችንና አማሮችን በገሀድና በስውር መንገድ እየጠራረገ፡ አገሪቱን በብቸኛነት የሚገዛበትንና የሚይስገብርበትን ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግን ክምን ጊዜውም በላይ በማፋፋም ላይ ነው።
በመሆኑም፡ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ቤተ ክርስቲያንና መስጊዶች ተደፈሩ። ዛሬም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። ይህ በፈጣሪ የሚሳብበው የስሞተኛ/የሽሽት ጸሎት፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የዛሬ 45/46 ዓመታት ገደማ ሲሉት የነበረውን ያስታውሰኛል – “የሀገራችን ሕዝብ ከዚህ የባስ አታምጣ ይላል። መደብ ላይ ከመተኛት (ጎጆ-አጥነት ባልታወቀበት ገጠር) አሹቅ ከመብላትና ውሃ ከመጠጣት በታች (ድርቅና ርሀብ እምብዛም ሥር ባልሰደዱበት ዘመናት) ወዴት ወደከፋ በታች ይወረዳል?”
እኔም ሳስበው፡ ፈጣሪ ፖለቲከኛና ባለመሆኑና ለሥልጣኑ ሥጋት ስለሌለበት ይህ የእርሱ አስተሳሰብ ወይንም አመለካከት ይሆናል ብዬ አላምንም፡፡ አንድ ሁለት እይለ የኢትዮያን ብሄረስቦች ክቤታቸውና ንበረታችው ሲመንግል፤ ከቤት፡ ከቤተስብ፡ ከንበረትና ከሃይማኖት እገዳ ውጭ ምንድንው ከዚሀ የባስ የሚሆነው?
አማራው ከኢትዮጵያ መሥራቾች መካከል እንዳልነበረ ሁሉ፡ ዛሬ ሥልጣን የተላበሱ ስዎች (ቡድኖች) አማራውን በተቀነባበረ መልኩ፡ ከደቡብ እስክ ደበብ ምሥራቅ፡ ክመሀል ሀገር ሁሉ በማፈናቀል አገር አልባ ይመስል፡ ብዙ ወንጀል እየፈጸሙበት ነው። ፍርህት የዋጣቸው ዜጎች ጥርሳቸውን መንከሳችውና አንጀታችው ማረሩ ግን አልቀረም። ፍርሀት ስለዋጣችው፡ ማለትም የሆድ አደሩንና የስላዩን ብዝት ስለሚያውቁ፡ በባዕድ የጭቆና አገዛዝ እንደተያዘ ሕዝብ ሁሉ፡ ይህንን ቀን በጸሎት ለማለፍ ጥረት ስያደርጉ ይታያል። ይህ የኢትዮጵያ ጥፋት” “ነው።
አንድ የቀድሞ የሕወሃት ባልሥልጣን የአማራና የኦርቶዶክስ ቢተክርስቲያን ግንኝነትን መምታት ለድርጅታችው ዓላማ መሳካት ዐይነተኛ መሣሪያ መሆኑን በገሃድ መናግራችው፡ የዘር ማጽዳቱ ዘመቻ ምን ያህል በዕቅድ የተያዘ መሆኑን አመላካች ነው።
መለስ ከደቡብ ሰለተባረሩ አማሮች ተጠይቆ ፓርላማ ውስጥ ሲመልስ፡ የነበረውን የማድበስበስ ጥረት፡ የስሜቱን መርካትናገና እናሳያችኋለንየሚለውን ስሜቱን አልሸፈነውም። ለሕወሃት ይህ በፕሮግራም የተያዝ ጉዳይ በመሆኑ፡ የኦሮሞ ሊሂቃንን ገደሎና አዋርዶ ካኮላሽ በኋላ፡ የኦሮሞን ወጣቶች እሥር ቤት አጉሮ ወደአማራው መሸጋገሩ፡ ከሆድ አድሮች በስተቀር፡ ሕዝቡን በአላምን ባይነት ሳያደነዝዘው አልቀረም። ከዚህ ጥቃት እኔ ተርፋለሁ ብሎ የሚያስብ ዚጋ ሁሉ ተራውን ጠባቂ መሆኑን የሚያመላክት ነው።
የሕወሃት ዓላማ አገሪቱን ለዘለቄታው ረግጦ መግዛት በመሆኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፡ እስከዛሬ የፈጻማቸው ወንጀሎች በቂ ባለመሆናቸው ፕሮግራሙ እርሱ በፈለገው ፍጥነት አልተካሄዱም ብሎ የሚያምን ድርጅት ይመስላል። እስካሁን የሚድረገው ጩኸት ሕውሃት ብቻውን የሚያድርገው እይስመስለው በመሆኑ በርሱ ስም ይህንን ደባ የሚፈጽሙትን በውኩልነት ተጠያቂ ማድረግ ይስፈልጋል!
የሕዝብ የነጻነት ርሃብና የገዥው ቡድን የኤኮኖሚ ጥቅሞች እየፈጠሯቸው ያሉት ግጭቶች
የሕዝብ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ከባለሥልጣኖች (ከተወሰነ ቡድን) ጥቅምና ፍላጎትች ጋር ተጻርራሪ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት: አገዛ፡ዙ ሕግ በበላይነቱ ለዜጎች አስተማማኝ ጠለላ ስለማይሰጣቸው ብዙኅን ኢትዮጵያውያን በዕለታዊ ኑሮአቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ለሚቃጣ አደጋ ሲጋለጡ ይታያሉ። ከእርሻ መፈናቀል፡ የቤቶች በባለሥልጣኖች ወይንም የተወሰነ ቡድን ትዕዛዝ እንዲፈርሱ መደረግና የግለስቦች መንገድ ላይ መወርውር በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል። ይህ አንድ ጊዜ የተፈጸመ ስህተት ሳይሆን፤ ሆን ተብሎ በተደጋጋሚ ተግባራዊ የተደረገ፤ የተወስደውም መሬት በጥቅም ግንኙነት እየተለወጠ፡ ዜጎች አቤቱታ ስሚ እንኳ ያጡበት ሁኔታ ነው። ይህ ሁኔታ የዜጎችን በአገራቸው በነጻነትና ሙሉ መብቶቻቸው ተክብሮላቸ መኖራቸውን እስከአሁን አላሳየም።
ሀግሪቱ በሕግ መተዳደር እስካልቻለች ድርስ፤ ፍርድ ቤቶች የባሰሥልጣኖች ፍላጎትና ጥቅሞች ማስከበሪያ መሆናቸው ገሀድ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ: ግልጽም ሆነ ሥውር ፖሊሶች እንዲሁም የመከላከያ ኅይሉ የሀገርነና የዜጎችን ደኅንነት ጠባቂ ባልሆኑብት ሁኔታ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረቶች ለፖለቲከኞች ጥቅም፡ እንዲሁም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ማስፋፊያዎች የትርፍ ማካበቻ በሆኑበት አስፈሪ ጊዜ አግራችንና ሕዝባችን ነጻ ናቸው ብሎ መናገር አንድም ሀስተኛነት አለያም ጥርቅም ያል ደደብነት ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙው ሥልጣን በእጃቸው ያለ ግለስቦችና ዋናው ቡድን፡ ከእነርሱ በላይ ለሀገር አሳቢ እንደሌለ፡ ከእነርሱ በላይ የሀገርን ጥቅም አዋቂ እንድሌለ አድርገው ሲናገሩና ለማሳመን ሲሞክሩ ይደመጣሉ። ይህ እውነት ቢሆን ምንም ባልከፋ ነበር። ነገር ግን ጠቃሚ ብለው የሚሠሩት፡ የራሳቸውንና የአጋሮቻቸውን ጥቅም ሲያራምድ: አግሪቱ ስትመዘበር ይሳያል። በአንጻሩም በእነርሱ ድርጊት ብዙ ዜጎች ሲጎዱ፡ ደራሽ አጥ የሆኑበት ሁኔታዎች እየተበራከቱ ናችው።
ሆኖም ገዥው ቡድን እንዴት አድርጎ የመንግሥትንና የሕዝብን ንብረት በንቀትና ድፍርት በገሃድ ሲመዝብር የታያል። ለምሳሌ፡ በየቦታው የራሳቸውን ሰዎች የሚመድቡበት ምክንያት ለግል ድርጅታችው (EFFORT) ግንዘብ የሚያስተላልፉበት መንገድ መሆኑ በግልጽ የታያል።
በዜና ማስራጫዎች ይዘገባል
ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። በመክላከያ ሚኒስቴር ሥር ያለው የበርታበርትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በእንግሊዝኛው ስሙ Metal and Engineering Corporation (MetEC) ባለፈው ዓመት መጋቢት ላይ የያዩን የፈርቲላይዘር ፋብሪካ ግንባታ ሥራ ለተቋራጮች እንድሚሰጥ ያስታውቃል። ወዲያው ብር 792 ሚሊዮን ኮንትራቱ ለአምባዬ ኮንስትራክሽን መሰጠቱ አሁን ደግም የሕወሃት መስፍን ኢንጂነሪንግ ምክትል ሥራ አስኪያጅ / ተስፋሁን በዛብህ በቅርቡ እንደገለጹት የፈርቲላይዘር ፋብሪካዎችን ኮንትራት ሥራ ድርጅታችው ለማግኘት ዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመክላከያው ብረታብረት ፋብሪካዎች ወጭና ገቢ ላይ ገንዘብ ሚኒስቲርም ሆን መንግሥታዊ ኦዲተሮች ድምጽ የላቸውም። ይህ ጉዳይ አቶ ግርማ ሠይፉን አሳስቧችው 2004 በጀት በሚጽድቅበት ወቅት ለመለስ ጥያቄ አቅርበው ነበር። በውቅቱ የተጣቸው መልስ የተሽፋነፈ ነገር እንደሌለና፡ ወጭና ገቢውን ማየት የሚፈልግ ዜጋ ጥያቄ አቅርቦ መመልከት ይችላል የሚል ቀልድ ነብር። ሥጋት ግን ዛሬ አግጦ የሀግሪቱ ንብረት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አማካይነትና ኮንትራት ስጭነት ግነዘብ ለጥቂት ዘመነኞች መዝናኛ ወደ EFFORT በግልጽ እየፈሰሰ ነው። እይንዳንዱ አባልም ወደውጭ የሚያሽሸሸው ገዝብም ቀላል አይደለም።
ይግረማችሁ ብሎ ብረታ ብረትና እንጂነሪንግ ባለፈው ሐምሌ ወር በብር 140 ሚሊዮን በብርጋዴር ጄኔራል ኪንፈ ዳኝው አማካይንት 72-ክፍሎች ያሉትን ሆቴል (Rivera Hotel) ለመግዛት በቅቷል። ለምንድነው መክላከያ ይህ ሆቴስ ያስፈለገው ተብለው ሲጠየቁ፡ ለወራት የሚቆዩትን እንግዶቻችንን ለማስተናገድ ነው የሚል መልስ መስጠታቸውን አዲስ ፎርቹን ስሙ እንድይጠቀስ ያልፈለገን ባለሥልጥን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። 80 ሚሊዮን ብር ከተገዛው ሆቴል Imperial Hotel ቀጥሎ፡ ይህ ሁለተኛው መሆኑ ነው።
ይህ የብረታ ብርትና እንጂኔሪንግ ኮሮፖሬሽን 2010 ሲቋቋም፡ 12,500 ሠራተኞች ያሉት ድርጅትና ተጠሪትነቱም ለመክላከያ ሚኒስቴር ሲሆን፡ ውናው ዓላማው የአገሪቱን ልማት ለማፋጥን እንዲቻል እስክ 2014/15 የሚቆየውን የአምስት ዓመት ፕላን በኢንዱስትሪና ኢንጊነዕሪንግ የማያስፈልገውን የመፈብርክና የመሐንዲስነት ሥራዎችን ማከናወን ነበር።
አሁን እንደሚታየው ክሆነ ግን፤ ለሕወሃት ድርጅቶች ዐይነተኛ የገንዝብ ማስተላለፊያ ሆኖአል። የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የማይፈልዟችውን መኪናዎች እንዲገዙ እየተደረገ፤ ከበጀት የሚዘረፈው ገንዝብገቢው ጄኔራሎቹን ክማበልጸግና ክማዝናናት አልፎ፡ በሥራ ተቋራጭነት ስም ከእነርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው የበሄረስባችው ገንቢዎችም በጓሮ በር የሚያገኙዋቸው በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሕንጻ፡ የመንገድ ሥራ ተቁራጮችም አላል ተጠቃሚ እየሆኑ፡ ሙያና ብቃት ያላቸው በዝቅተኛ ዋጋ ተወዳዳሪ ሥራ ሊሠሩ የሚችሉ ባልሙያተኞችክገዥውዘር ባለመሆናቸው የሚቀጡ መኖራችውን ማስታውስ ይገባል።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን የሀገር ጥፋት መዋጋት ይገባዋል። ከላይ እንደጠማይገባ ተግባር ነው። ዛሬ ይህንን ለማድረግ ከምንጊዜውም በበለጠ ተክኖሎጂ የፈጠራቸው አመቺ ሁኔታዎች ስላሉ፤ እንዚህን ተክኖሎጂዎች በመጠቀም፡ ሁኒታውን የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም እንዲያውቀው ማድረግ ይቻላል። ተገቢም ነው።
እነዶ/ ደብረጽዮን ይህንን በር ለመዝጋት ብዙ ሞክረው፡ ስንትና ስንት ሀብት ለአፈናው አፈስስው አልተሳካላቸውም።

No comments:

Post a Comment