Thursday, April 4, 2013

ስለ እስክንድር እውነት እናውራ።

 ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር ወዳድ ኢትዮጵያ እስክንድርን  የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው በመሆኑ፣ ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት አያዳግትም።እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ለም ውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው።
ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የእስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው። የነ ርእዮት ለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።
ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።
እጅግ ልብ የሚነካ በደል ነው፡፡ እንባ ያቆረዘዙ አይኖቼፅሁፉን ሀሳቤን ጀምሬ እንዳልጨርስ አግደውኝ  የነበሩ በደሎች ብዙ ነበር እስቲ ይሁና ብለን መተው ግን የለብንም፡፡ ብሶት እንባን አስቁሞ እልህ ያመጣል መሰልከለቅሶ ወደ እልህ ተሸጋገርኩ፡፡ ግለሰቦች ላይ የሚፈፀምን ግፍሃሰትም ቢሆን ለህዝብ ጥቅም ነው ብለን ፖለቲካዊ ሽፋን እንስጠው፤ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ ምን ሽፋን እንሰጠዋለን ጎበዝ? ከባድ ነገር ነው፡፡ የግፍ መጨረሸው ህዝብ ላይ የሚፈፀም ነው፡፡ በህዝብ ላይ የሚፈፀምን ግፍ ለመታገል ምክንያት አያስፈልግም እና ይህን መንግስት እንወዳለን የምትሉ ሁሉ………የመቻል ግድቡ ፈርሶ ጎርፉ ሁላችንም ከማጥለቅለቁ በፊት ተው በሉት!!!
 ኢትዮጵያን በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment