Wednesday, April 24, 2013

ውሸትም ለዛ አለው ! በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሩብ ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዙ( ኢቲቪ) አቤት አቤት ውሸት !


በኖርዌይ አገር በሚገኙ ኢትዮጵያዊን ስደተኞች ተዋርዳ የተባረረችው የወያኔ ዲፕሎማት ጀሌ በስዊዲን ወይዘሮ መብራት በየነ::በኖርዌይ ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶባት የተባረረች ሲሆን በኢቲቪ የውሸት ማስተባበያ ሰጠች ።
በኖርዌይ ሊደረግ የነበረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ  ድምፃቸውን ያሰሙበት ነበር።በኖርዌይ አገር በሚገኙ ኢትዮጵያዊን ስደተኞች ተዋርዳ የተባረረችው የወያኔ ዲፕሎማት ጀሌ በስዊዲን ወይዘሮ መብራት በየነ ህ አልበቃ ብሏቸው የውሸት ወሬ በኢቲቪ ለህዝባችን እያስተላልፉ ይገኛል። እውነቱን ግን በቪዲዮ ምስል ያለውን ፊልም ይመልከቱ ! የኢቲቪ ማስተባበያ ጽሁፍም አያይዘነዋል ያንቡት!

በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል 75 ሺ የኖርዌይ ክሮነር/ሩብ ሚሊዮን ብር/  ቦንድ መግዛታቸውን በስቶክሆልም የኢፌዲሪ ቆ/ጀ/ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
ፅህፈት ቤቱ እንደገለፀው በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያ በተለያየ ሽፋን የተሰባሰቡ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ሃይሎች ያቀነባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ ሳይገድባቸው ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ በመግዛት ለአገራቸው ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አመስክረዋል ብሏል፡፡

http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/586-በኖርዌይ-ስታቫንገር-የሚኖሩ-ኢትዮጵያውያን-75-ሺ-የኖርዌይ-ክሮነር-ቦንድ-ገዙ

No comments:

Post a Comment