Monday, April 8, 2013

ፖለቲከኞቻችን ሲመደቡ


ከአንድ ጋዜጠኛ ወዳጄ ጋር ሻይ ቡና ቢጤ እየቀማመስን በነበረበት ሰዓት በድንገት ራሳችንን የፖለቲካ ወግ ጥረቃ ጎላ ውስጥ ጥደን አገኘነው፡፡ያው ኑሮአችንም፣ውሎአችንም ፖለቲካ ነውና ማውራታችን፣ መቦጨቃችን እንተወውም ብንል የሚተው አይደለም፡፡
ከወዳጄ ጋር የጀመርነው ፍተላ እንደአጋጣሚ የአገር ቤት ተቃዋሚ ፖለቲከኞቻችንን የሚነካካ ነበር፡፡በተለያዩ ምድቦች ሽንሽነን ቃኝተኛቸዋል፡፡የቀረ ምድብ ካለ እርስዎ ሊያክሉበት ይችላሉ፡፡
የመጀመሪያዎቹ፡- ሆዳሞቹ ናቸው፡፡
እዚህ ምድብ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲን እንደቢዝነስ አይተውት የተጠጉትን ስብስቦ የያዘ ነው፡፡ መነሻቸውም፣ግባቸውም ቢዝነስ(ጥቅም) ብቻ ነው፡፡ብዙውን ጊዜ የራሴ የሚሉት ቢሮ ወይም አድራሻ የላቸውም፡፡ውስጣቸው ሲፈተሸም የሚገኙት አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ናቸው፡፡ግን ቢዝነሳሞች ናቸውና መንገዱን ያውቁበታል፡፡ለምሳሌ በአገር አቀፍ ምርጫ በቀረቡ ዕጩዎችና ሴት ዕጩዎች ብዛት የፋይናንስ ድጎማ እንደሚሰጥ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በሚገርም ሁኔታ የተሻለ አደረጃጀት አለን ከሚሉት በላይ ዕጩዎችን በየመንደሩ እየዞሩ እንደሸቀጥ ገዝተው ምርጫ ቦርድ ወስደው ያስመዘግባሉ፡፡

ገዥውን ፓርቲ ለማስደሰት እጣንና ከርቤ እያጤሱ ይዘው የሚቆሙ ዓይነቶች ናቸው፡፡እንደ ዋንጫ ከወደአፋቸው ሰፋ ያሉ ናቸው፡፡ምርጫው ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ እየሄደ መሆኑን በኋላም በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው፣በሕዝብ ስም እየማሉና እየተገዘቱ ሲናገሩ ውስጣቸውን የማያውቅ የዋህን በሚገባ ይሸውዳሉ፡፡

ሁለተኛዎቹ፡-
በአመዛኑ የሃብታም ጡረተኞች፣ የትርፍ ሰዓት ፖለቲከኞችና ጥቂት ምሁራን መሰባሰቢያ ናቸው፡፡ሰዎቹ አንዳንዴ ፖለቲካውን እንደጊዜ ማሳለፊያ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ከገዥው ፓርቲ ጋር ያላቸው ግንኙነት በከባድ ጥንቃቄ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ብዙዎቹ ተቃዋሚዎች ቢሆኑም ዋጋ የሚያስከፍል ነገር ውስጥ ላለመግባት ይጠነቀቃሉ፤እንዲህ ዓይነት ነገር ከመጣም ቶሎ መውጪያቸውን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ 
ሥልጣን የሙጢኝ የሚሉ ዓይነት በመሆናቸው ብዙም ወጣት ተከታዮችን ሲያፈሩና ሥልጣን ሲያጋሩ አይታዩም፡፡የእነዚህኛዎቹ የዘወትር መፈክርእጅህን ባህር ውስጥ ክተት፤ ብታገኝ ዓሳ ይዘህ ትወጣለህ ባታገኝ ታጥበህ ትወጣለህእንደሚባለው ጥቅማቸውን ያሰላ ጨዋታን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ 
ሦስተኛዎቹ፡-
እውነተኛ አገራዊ ስሜትና ቁጭት ይዘው በሰላማዊ ትግል፣በምርጫ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለው ትግል የጀመሩ ናቸው፡፡ብዙዎቹ ዕድሜያቸው በወጣትና በጎልማሳዎቹ ክልል ቢገኝም ጥቂት በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችንም አካተዋል፡፡አንጻራዊ በሆነ መልኩ የእኔ የሚሏቸው አባላት ያሏቸው ናቸው፡፡ግልጽ ርዕዮት ዓለምና አቅጣጫ ያላቸው ሲሆኑ አንጻራዊ በሆነ መልክ የህዝብ ድጋፍም ያላቸው ናቸው፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment