Friday, April 26, 2013

ለኢህአዴግ የተፈቀደ ነገር ሁሉ ለተቃዋሚዎችም መፈቀድ አለበት የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡


የኢህአዴግ ካድሬዎች ምን ሊሉ እንደሚችሉ አይጠፋኝም ቢሉም ግድ የለኝም ስለለመድኩት፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ያወጡት መጽሐፍ እስከ 200 ብር ድረስ ሲሸጥ ትንፍሽ ሳይል  የኢህአዴግ አመራር ሲያወጡ… ተወደደ ምናምን ብሎ ይተቻል ሊሉኝ ይችላሉ፡፡ ይሄን ወቀሳ እቀበለዋለሁ፡፡ እውነት ነው፡፡ ምክንያት ግን አለኝ፡፡ወያኔ/ ኢህአዴግ ለድሀው የታገለ አሁንም የሚታገል የጭቁኖች ፓርቲ ነው ሲሉ ስለሰማሁ ነው ትችቴ ያየለው፡፡ በርግጥ አሁን  ወያኔ “ጭቁን ፓርቲ” አይደለም - ኢህአዴግ!!የዛሬው ኢህአዴግማ ድልቅቅ ያለ ሃብታም ሆኗል - ሞጃ! የገንዘብ ግን እንዳይመስላችሁ ገንዘቡን ተውት በሙስና ስለወነ የእኛ አይደለም እያሉ እየተሰሙ ነው ምነው ሲባሉ የሸቤ መንገዳችንን እያመቻቸን ነው ሲሉ ይደመጣሉ እዚ ላይ እውነት ብለዋል፡፡ የኢህአዴግ ሃብት ወይም ካፒታል ገንዘብ ሳይሆን ህዝብ ነው፡፡   የህዝብ ሃብታም ነው - ኢህአዴግ! እንዴ ብትሉ… 85 ሚ. ህዝብ እንዳሻው ይመራል (ግን አስፈቅዶ ነው ህዝቡን ብትሉኝ አይደለም በጉልበት) ከ97 ምርጫ ወዲህ “ናዳን ለመግታት ባደረገው አገራዊ ሩጫ” ከ7 ሚሊዮን በላይ አባላትን አፍርቷል ይባላል ያው በግዳጅ፡፡
(ገቢያቸውን ሲጠየቁ ሃብታችን ህዝብ ነው የሚሉ የአገሬ ድምፃውያን ትዝ አሉኝ)   በነገራችን ላይ “የሁለት ምርጫዎች ወግ” የምትለዋ ርዕስ በጣም ተመችታኛለች፡፡ (አቅም ጠፋ እንጂ ርዕሷ ብቻ 90 ብር አይበዛባትም!) እውነቴን ነው የምላችሁ … ርዕሷን የመረጣት ሌላ ተራ ፀሐፊ ቢሆን  የአድናቆት መዓት ባዥጐደጉድኩለት ነበር፡፡ አቶ በረከት ግን ገጣሚ (ቃል አቀባይም ናቸው!) በመሆናቸው ብዙም አልገረመኝም፡፡ ገጣሚዎች የቃላት (ቋንቋ) ሃብታም ናቸው ይባል የለ! (ገቢያቸውን ሲጠየቁ ሃብታችን ቋንቋ ነው እንዳይሉ ብቻ!) በዚህች አጋጣሚ የሼህ ሙሃመድ አላሙዲንና የኢህአዴግን ወዳጅነት የምትተርክ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ዕቅድ እንዳለኝና ርዕሷንም “የሁለት ወዳጃሞች ወግ” እንደምላት ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡ (ማመልከቻ መሰለብኝ አይደል? ይምሰላ!) በነገራችን ላይ የአቶ በረከት መጽሐፍ በሸራተን አዲስ የተመረቀ ምሽት ሼህ አልአሙዲ በይፋ “ኢህአዴግን እወደዋለሁ! አራት ነጥብ!” ሲሉ መናገራቸው አንጀቴን  አቃጥለውኛል በንዴት ግን ሳስበው አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንደሚባለው ሲሆነ አያስገርምም፡፡ እንዲህ የልቡን የሚናገር ሃቀኛ ባለሃብት ያስፈልገናል፡፡ ወዲያው ግን ሌላ ሃሳብ ብልጭ አለልኝ - “ተቃዋሚዎችን እወዳቸዋለሁ! አራት ነጥብ!” ብሎ በአደባባይ መናገር የማያሸማቅቀው ባለሃብትም መፍጠር አለብን የሚል፡፡ (በግድ እንፍጠር ግን አልወጣኝም - ካለ ማለቴ ነው!) አዎ … የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት የፃፉትን መጽሐፍ ሳይሸማቀቅ በግልጽ የሚያሳትም ባለሃብት ማየት አለብን - እንደ ጀሌ አልአሙዲ፡፡ ያኔ ነው ሚዛናዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አለን ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር የምንችለው፡፡ ለምን እንደሆነ አላውቅም… ለኢህአዴግ የተፈቀደ ነገር ሁሉ ለተቃዋሚዎችም መፈቀድ አለበት የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡ ይሄ እምነቴ ስህተት አይመስለኝም ! ወያኔ ይታረማል ብላችሁ ግን እንዳትጠብቁ፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment