Wednesday, April 24, 2013

ፖለቲካ ሲሸሽ በሙከራ


አንድ ቀን አባት ልጁ ት/ቤት ሄዶ ሳለ  አንድ ሙከራ (Experiment) ለማድረግ ይወስናል፡፡ የአፍሪካ ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት በህዝባቸው ላይ እንደሚያደርጉት ዓይነት ሙከራ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ ልጁ ላይ አንዳችም የጐንዮሽ ጉዳት (Side effect) የማያስከትል ነው - ኤክስፐርመንቱ፡፡ የአፍሪካ መንግስታትና ፖለቲከኞች ሙከራ እኮ ህዝብን የሚፈጅ ሁሉ ሊሆን ይችላል (እነሱ ምን ቸገራቸው!) በአፍሪካና በተቀሩት የሦስተኛው ዓለም (የድሃው ዓለም ቢባል ይሻላል!) አገራትን የእርስ በርስ ጦርነት፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የነፃነት አፈና ወዘተ... መንስኤያቸውን በቅጡ ብትመረምሩት ሁሉም የድንገተኛ ሙከራ (Experiment) ውጤት እንደሆኑ ትደርሱበታላችሁ፡፡ ይሄኛው ግን የፖለቲከኞች ሳይሆን የአንድ ልጁን የሚወድ አባት (ህዝቡን የሚወድ ፖለቲከኛ ግን ከየት እናምጣ?) ትንሽዬ ኤክስፐርመንት ናት፡፡
 
አባት ለሙከራ ሥራው የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች ይዞ በቀጥታ ያመራው ወደ ልጁ የመኝታ ክፍል ነበር፡፡ ቁሳቁሶቹንም በልጁ የማጥኚያ ጠረጴዛ ላይ ደረደረ፡፡ መሃፍ ቅዱስ፣ ከብር የተሰራ ዶላርና አንድ ጠርሙስ ውስኪ ነበሩ - የሙከራ ቁሳቁሶቹ፡፡ 
ከዚያም አባትየው ከራሱ ጋር እንዲህ እያለ ያወራ ጀመር፡፡ ..ከእነዚህ ሦስት ነገሮች የትኛውን እንደሚያነሳ ከበሩ ኋላ ተደብቄ አያለሁ፡፡ መሃፍ ቅዱሱን ካነሳ ፀደቅኩ! እንደኔ ሰባኪ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ዶላሩን ካነሳም ነጋዴ ይሆናል - ይሄም ለክፉ አይሰጥም፡፡ ነገር ግን የውስኪ ጠርሙሱን ብድግ ካደረገ የመጨረሻ ቅሌት ነው - ለማንም ለምንም የማይረባ ሰካራም ይሆንልኛል! አደራህን ፈጣሪ... ከዚህ ሰውረኝ.. ብሎ የልጁን ከተማሪ ቤት መመለስ በትእግስት ይጠባበቅ ጀመር፡፡ የልጁን ኮቴና ፉጨት የሰማው አባት በር ኋላ ተሸጉጦ ነገሮችን በጥሞና ይከታተል ገባ፡፡ ልጅ እንደተለመደው ወደ ክፍሉ በመግባት ደብተሩን አልጋው ላይ ወርውሮ ሊወጣ ሲል ጠረጴዛው ላይ የተቀመጡት ነገሮች የዓይኑን ትኩረት ሳቡት፡፡ በጉጉት ተሞልቶ ወደ ጠረጴዛው ተጠጋ፡፡ በመጀመሪያ መሃፍ ቅዱሱን አነሳና ብብቱ ሥር ሸጐጠው፡፡ በመቀጠል ዶላሩን ኪሱ ውስጥ ጨመረ፡፡ በመጨረሻ ውስኪውን ከፈተና በደንብ ተጐነጨለት፡፡ 
አባትየውም ..እግዚአብሔር ይጠብቀው... ልጄ ፖለቲከኛ ነው የሚሆነው!.. ሲል ለራሱ አንሾካሾከ፡፡ 
ይታያችሁ... አባት የልጁን ፖለቲከኛ መሆን እንደመዓት የቆጠረው የዲሞክራሲ እናት ናት በምትባለዋ አሜሪካ ውስጥ ነው፡፡ መአተኛ በሆነችው በአህጉረ አፍሪካ ቢሆንስ?
በአፍሪካማ... ፖለቲካ እሳት ነው - ..እፉ.. ብለን ለህፃናት የምንነግራቸው ክፉ እሳት፡፡ ነገር ላልገባቸው አዋቂዎችም ..አደገኛ ስለሆነ ይጠንቀቁ!.. ብለን ቅድመ ማስጠንቀቂያ የምንሰጥበት አደገኛ ጉዳይ ነው - የአፍሪካ ፖለቲካ!! 
አሜሪካኖች ግን ስለፖለቲካ እንዲህ ይላሉ ..ፖለቲካ መጥፎ ሙያ አይደለም፡፡ ከተሳካልህ በብዙ ሽልማቶች ትንበሸበሻለህ፡፡ ካልተሳካልህና ቅሌት ከተከናነብክ ደግሞ መሃፍ መፃፍ ማንም አይከለክልህም..... ወቸ gùD! እዚህ አፍሪካ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካ ካልተሳካልህና ሥልጣን ካልተቆናጠጥክ መሃፍ መፃፍ አይደለም ትንፋሽ የምትወስድበት ጊዜ እንኳ የሚሰጥህ አታገኝም... ወይ ከአገር ትሰደዳለህ አሊያም አንከብክበው ወስደው ከርቸሌ ያጉሩሃል፡፡ ወዳጆቼ... የአፍሪካ ፖለቲካ የሚመኙት ሳይሆን የሚሸሹት ነው - እንደ ኤሌክትሪክ፡፡ (ፖለቲካና ኤሌክትሪክን በሩቁ ነው የተባለው እዚሁ አፍሪካ በተለይ ኢትዮጵያ  ውስጥ አይመስላችሁም?)
ከሰብኣዊ 

No comments:

Post a Comment