ስንቱ በረሀብ በሚረፈረፍበት፣ በመድሃኒት መግዣ እጦት ማቅቆ በሚሞትበት፣ በጧሪ ቀባሪ ማጣት ናውዞና ባክኖ በሚሞትበት፣ በሰቀቀን በሚሟሽሽበት፣ በውሃ እጦትና በውሃ ወለድ በሽታዎች በሚጠቃበት፣ (በሌላ ሌላው ትተነው እንኳን) በቁንፅል 'የፀረ ሽብር' ሰበብ በተናገርናት/በፃፍናት በያንዳንዷ ነገር ሰበብ፥ ስለ እድል ፈንታው ዋስትና በሌለው ሁኔታ ላይ... የነሱን ለቅሶና እንባ መታደግ አቅቶን ጆሮ
ዳባ ልበስ ያነው ስንቶቻችን ነን? ለቅሶ ማዳመቁ ከቅንጦትም ጋር ያያያዝነ ስንቶቻችን ነን?
ወያኔዎችና ጀሌዎቹ
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ
መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ
የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ
ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment