ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ሊደርግ የነበረው የቦንድ ሽያጭ
በተቃዋሚዎች ብርቱ ጥረት እንዳይሳካ ተደረገ። ኖርዌይ ኦስሎ በተቃውሞ ተቀውጣ ውላ ነበር። ለቁጥጥር በሚያስቸግር ሁናቴ ተቃውሞ
ሲደረግ ውሏል።የወያኔ ጀሌዎች በመጀመሪያ ስብሰባውን የጠሩበት አዳራሽ በኖርዌይ አጠራር Schweigaards galleri በተባለ ቦታ በኖርወይ ሰዓት
አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በ15 ሰዓት ወይንም በ3 ሰዓት ላይ ለደጋፊዎቻቸው በስልክ በSMS አድርገው እንደነበርና በዛም ደጋፊዎቻቸው
በተጠሩበት ቦታ አካባቢ ብዙ ተቃዋሚዎች አካባቢው ላይ እንደነበሩ በሰላዮቻቸው ስለተነገራቸው ቦታውን ለመቀየር የተገደዱ ሲሆን ወያኔዎቹና
ጀሌዎቹ በስውር ለመቀየር ያሰቡት ቦታ በተቃዋሚዎቹ በኩል የተጠናከረ ስራ ሲሰሩ ስለነበር ያንንም ደርሰውበት ወደ ሁለተኛው የተከራዩበት
Scandinavia hotel ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በመያዝና ሊያዘጋጁት የነበረው ስብሰባ ተቃዋሚዎቹ እዛው ድረስ በመሄድ የቦንድ ሽያጭ በተቃውሞና በመፈክር ያስቆሙት ሲሆን አንዳንድ ተቃዋሚዎች ወደ
ሆቴሉ በመግባት ያለውን ሁናቴ ተናግረው ነበር በሆቴሉ ውስጥ ክ10 የማይበልጡ የወያኔ ደጋፊዎች እንደነበሩ ውስጥ የገቡትም እንዳይነጋገሩ
ስብሰባው እንዳይደረግ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱም የአይን ምስክር ሰተዋል።በተለይ ከሆቴሉ ፖሊስ አትገቡም የተባሉት ተቃዋሚዎች
በቁጥር ከፍተኛ ሲሆኑ በልህና በስሜት ሆነው ሲያሰሙት የነበረው የተቃውሞ ድምፅ ለፖሊስ ሁላ አስቸጋሪ እንደነበርና ፖሊስም ሁኔታውን
ለመቆጣጠር የፖሊስ ሀይል በከፍተኛ ሁናቴ እንዲጨመር በማድረግ በሁናቴው የነበረው ክስተት ሲናገሩ የነበሩት ተቃዋሚዎች ያስረዳሉ።በዚህም
ሁናቴ የተለያዩ የኖርዌይ ቲቪ እንዲሁም ጋዜጣ ስለ ተቃውሞ የዘገቡ ሲሆን ሁናታው ከባድ የሆነ ተቃውሞ እንደነበርም ገልፀዋል።
በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሰደር መብራት በየነና ጀሌዎቹ ለሁለተኛ
ጊዜ ትልቅ ተቃውሞ ደርሶባት ወደ መጣችበት ፖሊስ በድብቅ ከሆቴሉ አስወጥቷል።ይህ ተቃውሞ ለሁለተኛ ግዜ ሲሆን በመጀመሪያ በኖርዌይ
በስታባንገር በ20/4/2913 ከፍተኛ ተቃውሞ በአዳራሹ ውስጥ በማድረግ አምባሳደሯን እንዳባረሯት የሚታወቅ ሲሆን በሳምንቱ ደግሞ
በ28/4/2013 በድጋሚ ስብሰባው እንዳይደረግ በማድረግ ኢትዮጵያኖች ተቃዋሚዎች ከፍተኛ ሚና አድርገዋል።
በተቃውሞ ላይ የነበሩ ሰዎች ሲናገሩም ወያኔን 2ለ0 አሸነፍነው
ሲሉም ተደምጠዋል።በዚህም በማያያዝ ትግሉ በከፍተኛ ሁናቴም እንደሚቀጥል አስረድተዋል።ወያኔም ለአባይ ግድብ እያለ የሚያሰማው የፖለቲካ ጨዋታ እንዳልተሳካለትና ህዝቡም ለፖለቲካ ጨዋታም እንደሆነም
በደንብ አውቋል። ወያኔ ለአዳራሽ ክፍያም በሳምንት ውስጥ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የራሳቸው ሰው ተናግረዋል። የስታባንገሩን
ብሮግራም እንዳልተሳካላቸው በተለያዩ ድረገፅ ሁላ በቪድዮ ምስል በማስደገፍ የተላለፈ ሲሆን የወያኔ ቲቪ ግን ከግማሽ ሚሊዮን ብር
በላይ ሰበሰብን ብሎ የውሸት ኘሮባጋንዳ ሲያሰማ እንደነበረም ይታወቃል።
በተቃውሞ ላይ ሲነሱ የነበሩቱም መፈክሮች ብዙ ሲሆኑ ከብዙ በጥቂቱ
ላካፍላችሁ ገንዘብ ከመሰብሰብ በፊት ነፃነት ይቅደም!ድምፃችን ይሰማ!በግፍ
የታሰሩት የፖለቲካና ጋዜጠኞች ይፈቱ ! ወያኔ ሌባ! የሰብኣዊ መብቶች
ይከበሩ! ነፃነት እንፈልጋለን!የህዝቡ ድምፅ ይከበር!እኛ እስክንድር ነጋ ነን !እኛ ርዕዮት አለሙ ነን!እኛ አቡበክር ነን! በኢትዮጵያ
ውስጥ አባርታይድ ይቁም !እና የተለያዩ መፈክሮች ሲሰሙ ነበር።ይኽን ስብሰባ እንዳይካድ ለማድረግ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና
አባሎች፣ሲቢክ ማህበራት፣አክቲቪስቶችና፣አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሩቅም ከቅርብም የተገኙ ሲሆን በአንድ ላይ በመሆን
አንድነታቸውን አስመስክረዋል።
በመጨረሻም በአንድ ላይ በመሆን ኢትዮጵያዊያኖቹ ባስተላለፉትና
ባሰሙት ቃል ልለያቹ።
እኛ ኢትዮጵያውያን የፀረ ልማት ሀይሎች አይደለንም! የፀረ ልማት
ሀይል ወያኔ/ህውሃት ነው።
ከዘካሪያስ አሳዬ
No comments:
Post a Comment