Wednesday, April 3, 2013

አሁን አሁን ኢትዮጵያን እራሷን እያፈርኳት መጥቻለሁ::

 በቤኒሻንጉልና ጉሙዝ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተፈናቀሉ በትውልድ አማራ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ሲነሳ ሰዎች ለጉዳዪ የተለያዩ አመለካከት ሲያጽባቁ ይታያል:: የመጀመሪያው ይህ የአማራ ጉዳይ ነው ስለ ጉዳዩ መጨነቅ በራሱ ዘረኝነት ነው የሚል አስተሳሰብ አለ:: በአንዲት አገር ውስጥ ያለ መንግስት በዜጎቹ ላይ በሚደረስው እንግልት መፍትሄ እንደ መስጠት የችግሩ አካል በሆበነት ሁኔታ በጣም ትንሹ የመኖር መብትን ሲጣስ እያዩ ሰብዓዊነት ይቀድማል ወይስ ዘረኝነት ? ይህን የሚሉ ሰዎች እራሳቸው ዘረኝነት የሚቃወሙ ቢመስሉም "ዘረኝነት" የሚል ካባ ሌላውን በማሸማቀ ልዩነትን ይፍጥራሉ::

ሌላው ደግሞ ይሄ አዲስ ነገር አይደለም በተለያዩ የአገሪቱ ክፎሎች ውስጥ የተከናወነ በሌላው ብሔር ላይም የደረሰ ነው ጉዳዩ አሁን ያልተጀመረ እንደሆነና በቃላሉ ሊፈታ የማይችል መሆኑን ደጋግመው ይገልጻሉ:: በዚህ ደግሞ ምንም እንደማይደንቃቸው እንድያውም ይህ ታሪክ ዘግቦ እንደሚያሰቀምጠው ይገልጻሉ:: በርግጥ አንድ ብሔር ተኮር ጥቃት ሲደረስ አይተናል:: ትናንት በጋምቤላም በመሬት ምክኒያት ለዚያውም በገዛ ክልላቸው ስፈናቀሉ አይተናል:: ነገሩን ከመሰረቱ መረዳት ጥሩ ሆኖ ሳለ ወደፊት በሌላ አካባቢ እንደማይፈጸም ምንም ማረጋገጫ የለንም::


ጉዳዩን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የሰባዊ መብት ረገጣ አያይዘን ልንረዳው እንችላለን :: ከመሬት ንጥቂያ ጋር አያይዘንም ልንረዳው እንችላለን እንዲሁም ከፍ አድርገን የችግሩ ሁሉ መንስዔ የገዢው ፓርቲ በምከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ውስጥ ተጣምሮ ያለ የብሔር ፖለቲካ ያስከተለው እንደሆነና እየተከናወነ ያለው አሁን ያልጀመረ ሆን ተብሎ የሚደረግ እንድሆነም ልንረዳ እንችላለን::ይህ ከተባለ ደግሞ ለነገሩ እውቀት ስላለን ችግሩን የመቃዎም ብሎም መፍትሄ የመፈልግ ሃላፊትን አለመወጣት እራሱ ችግሩን እያባባሰው እንደሚሄድ እሙን ነው:: ሌላው ደግሞ የችግሩ ሰለባዎች ከአንድ ብሔር ተወላጅ በመሆናቸው ምክኒያት ከሚደርስባቸው ጥቃት አስከፊው የእለት ከእለት ኖሯቸው መቃወሱ ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸውን የሚያኖሩበት ቦታ የሚመግቧቸው ማጣት ነው:: በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለን አንድን ገበሬ አሁን እየተፈጸመባቹህ ያለው አዲስ ነገር አይደለም በሌላ ቦታ በሌላ ብሔር ላይ የተፈጸመ ነው ብሎ መንገር ለችግሩ መፍትሄ አይሆነውም::

አሁን ለተጋረጠባቸው ችግር ወቅታዊ መፍትሄ መሆን የሚችለው

 (ሀ) የኢኮኖሚ ድጋፍ ማድረግ
 (ለ) የጤና ረዳታ የሚደረግበት ሁኔታዎች ማመቻቸት
 (ሐ) ከጎናቸውም በመቆም ድምጻቸውን ማሰማት (ማሰተጋባት).. ሌላም ሌላም

ለዘለቄታው ደግሞ ይህ አካሄድ በኢትዮጵያዊያን መካከል ሰፊ ቅራኔን የሚጫር ሊሆን ስለሚችል እንደ ስላማዊ አገርና እንደ ህዝብ የመቀጠል እየተፈጸመ ያለውን በአግባቡ ልዩነትን በማጥፋት መቃዎም ያስፈልጋል:: ይህንን ለማድረግ ደግሞ ሰመጥር ጀግና መሆን አያስፈልግም ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው::

ኢትዮጵያን የዕለት ዕለት ጀግና ይስጣት

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment