Sunday, April 21, 2013

እናስተውል!ያወጣችሁት ቃል ጠላታችሁ ሆኖ መልሶ እንዲወጋችሁ አትሞክሩ።


ከመቼ ጀምሮ ነው ሌባ ሲሰርቅ ሌባ አትበሉት የተባለው? በዳይ ሲበድል ግድየለም ይበድል የተባለው? ወያኔ/ህአዴ በትክክል ይሄንን ግፍ የሞላውን አገዛዙን በህዝቡ ላይ 21 ዓመት በላይ ሲፈፅም ቆይቶዋል። ታድያ እቺ አፍሪካዊ ሽልማት አያስፍልጋትምን? እኛስ ለሃገራችን የምቆረቆረው ድምፃችንን ማሰማት የለብንምን? በዚህም ሆነ በሌላ መንገድ ለሃገሩና ለህዝቡ ድምፁን የሚያሰማ ኢትዮጵያዊ ሳይ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል። ህአዴ/ወያኔን በጥቅም፣ ባለማወቅና በመታለል የሚደግፉት ኢትዮጵያዊያኖች ዞር ዞር ብላችሁ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ብታዩ ጥሩ ነው። ሁለት ድንጋይ ደርድሮ ፎቅ ሰራሁ፣ መሰረት የሌለው አስፓልት አንጥፎ ሃገር አስድጊያለሁ ሚለውን መንግስት ከመደገፍ ይልቅ ለሃገራቸውና ለነጻነታቸው ሲሉ ደማቸውን ያጡና በእስር የሚሰቃዩትን ውድ ኢትዮጵያዊያኖችን ብትደግፉ ያዋጣችኋል። ያወጣችሁት ቃል ጠላታችሁ ሆኖ መልሶ እንዲወጋችሁ አትሞክሩ። ፍቅር፡አንድነትና ሰላም ለኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
Ethiopian people is UNITY ,  TPLF is Nothing!

No comments:

Post a Comment