Sunday, April 7, 2013

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ ተቋረጠበት


3 ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለንአለ
እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገንየንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ  ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል።
ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ለተወሰኑ ሳምንታት ሲያሳትም ቆይቷል።
መጽሄቷ በተመሳሳይ መንገድ እንድትዘጋ ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገና ልእልና ጋዜጣን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ስራውን ለመስራት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጅ 100 ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛው ጋዜጣ  ከመንግስት በተላለፈው ጫና እንዳይታተም በድጋሜ ታግዶበታል
ተመስገን በራሱ ስም ፈቃድ አውጥቶ መስራት ከተከለከለ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ስለሚኖረው አማራጭ ሲጠየቅ፣ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዋ ትግል አማራጮች በመጠቀም አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለንብሎአል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ከፍተኛ ወከባ ሲደርስበት እንደነበር  ይታወሳል።  ተመስገን፣ 106 ያላነሱ ክሶችም እንዳሉበት ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment