Saturday, April 20, 2013

በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የተደረገው የአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል!!


በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የተደረገው የአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል!!
ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ጭቅጭቅ ነበር። ተቃዋሚዎች አይገቡም በማለት የተጀመረው መክፈቻ በኋላ ላይ ግን ፖሊስ ከመጣ በኋላ እንዲገቡ ተፈቀደ ። ስብሰባው በጥያቄ ተጀምሮ ነበር። ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውም እንዲ በማለት ጀመሩ፥
1 በመጀመሪያ እስከዛሬ እናንተ ከገባችሁ ጅምሮ ለገደላችሁት ሰዎች የህሊና ፀሎት ይደረግ በማለት ነበር የተጠየቀው በመቀጠል
2 እስከዛሬ እናንተ ያደረጋችሁትን የዘር ማጥፋት በአማራ፣ በኦሮሞ እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የተደረገው ነገር ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እየፈፀማችሁና እየገደላችሁ እዚህ መጣችሁ ገንዘብ መጠየቅ ለኛ ድፍረት ነው በማለት በስብሰባው አዳራሽ በጩወትና በመፈክር ተናወጠ የወያኔ የስዊዲን አገር ቆንፅላም እንዲሁም ጀሌዎቹም በመፍራት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች በማስረከብ ለቀው ወተዋል ! ።
ሌባ ነው ሌባ ወያኔ ሌባ በማለት የተጀመረው በመፈክር በጭወትና በዝማሪ አዳራሹ ተደበላልቋል!
ከገንዘብ በፊት ነፃነት ይቅደም!
ከገንዘብ በፊት ሰብኣዊነት ይቅደም!
ኢትዮጵያ አገራችን የደፈረሽ ይውደም! በማለት ተቃዋማቸውን ሲያሰሙ ነበር።

የወያኔ/ ህውሃትና ጀሌዎች በአለም ላይ የሚያደርጉት የአባይ ገቢ ማሰባሰብያ በየአለማቱ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል።
በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ሳይሳካ እንደውም ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት ያሳዩትን ጀግንነት ቀጥሎ በሌሎች አገርም በአሜሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ( ጅዳ) ፣በጀርመን ተቀጣጥሎ በቀጠለበት ሁናቴ በኖርዌይ
ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶበታል ።በኖርዌይ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል ። በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ይበልጣሉ።ታሪክ በውጪ ባሉ ኢትዮጵያዊያን እየተሰራ ይገኛል!
ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ተጠናክሯል ። የወያኔ የመገነጣጠል አላማ ስትራቴጂ የወደመበት ሆኗል።የሕዝቡም አንድነት የታየበት ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍም ሚያዚያ 18 2013 መካሄዱ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሆን በመዘመርና በመፍክር ብሶታቸውን አሰምተዋል።
ተቃዋሚዎቹ በአንድነት በመሆን ያሰሙት ቃል ነበር
(( ገና ይቀጥላል ሁላችንም ነፃ እስከምንወጣ ድረስ ))
ሞት ለአንባገነን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment