Monday, April 15, 2013

የማመሳቀል አቅምን ማሳየት የፖለቲካ አሸናፊነትን ማሳየት አይደለም!

አጼ ኃይለሥላሴ በሰጡት ንጉሳዊ ብይን ያልተደሰተ ኢትዮጵያዊ ንጉሱ ፊት ቀርቦ ተቃውሞውን የማሰማት እድል ነበረው። እናም በንጉሱ ፊትጃንሆይ የሰጡት ፍርድ ፍርደ-ገምድል ነው። አቤት እላለሁበማለት ምሬቱን ይገልጻል። ንጉሱምከእኛ በላይ ማን አለና ነውለማን ነው አቤት የምትለው?” ብለው ይጠይቁታል።ሁሉን ለሚችል አምላክ እንጂ ለሌላ ለማን ይነገራልብሎ መለሰላቸው። ንጉሱም በሚታወቁበት ርጋታቸው ከፈገግታ ጋርእኛን ቀብቶ ያነገስን ማን ነው እና ነው ለእግዚያብሄር ይግባኝ የምትለውብለው መለሱለት ይባላል። ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ መጽሄት ሳነብ (ጦቢያ ላይ ይመስለኛል) ያገኘሁትን ነው ያካፈልኩት። ተደርጎ ይሆናል። ውጭያዊ ምክንያቶችን እንደተጠበቁ ሆነው የለውጥ ሃሳብን ከኢትዮጵያዊነት እና ከኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ጋር ማዋኽድ ስለተሳነው 1966 የፈነዳው ዓብዮት ዛሬም ድረስ ባይሳካም በወቅቱ የተወሰደው እሳት የለበስ እሳት የጎረሰ የፓለቲካ ርምጃ ጥሩ ነበር መጥፎ የሚለውን ብይን ለየራሳችን ትተን ለውጡ በማያሻማ ሁኔታ ትቶት የሄደውን  ትምህርት ግን ማስታወስ ያስፈልጋል።የህዝብ የቁጣ ሰይፍ ሲመዘዝ በነማን ላይ እንዳነጣጠረ የሚስተው ሰው ያለ አይመስለኝም።

ለውጡ ለስልጣን ወደመታገል ደረጃ ተሸጋግሮ ስልጣን በያዙ እና ስልጣን ባልያዙ ወገኖች(አሁን በግብጽ እንደምናየው ወይ እንደምንሰማው) መካከል ትግል ከመጀመሩ በፊት የለውጡ ዋነኛ ዒላማ የዘውዳዊው አስተዳደር ስለነበረ መጀመሪያም ሰይፍ የተመዘዘው በዘውዳዊው የመስተዳደር አካላት ነበር። የዛኔው የስልጣን መዋቅር እንዲህ እንዳሁኑ በጎሳ እና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ አንድ ወገን ያውም በቁጥር አናሳበአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አናት ላይ ቆሞ እንደፈለገ ከበሮ የሚመታበት ስርዓት ቢሆን ኖሮ ሊደርስ ይችል የነበረውን ጥፋት መገመት አይከብድም።  በለውጥ ሰሞን የሚደርስ ጥፋት ከአብዮት የአውሬነት ባህሪ ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን ለአብዮት የአውሬነት ባህሪ ትልቅ አስተዋጾ ከሚያደርገው ከወደቀው ስርዓት ጋርም የሚያያዝ ነው።
በአንድ የድህረ-ገጽ የመወያያ መድረክ ላይ ሃሳቡን በመልክ በመልኩ ሳያስተካክል እንደወረደ አፉን ባልፈታበት ቋንቋ የሚዘከዝክ አፍቃሪ ህወሓት አለ። ብዙ ጊዜ (እንዲያውም ሁሌም ማለት የሚቻል ይመስለኛል) የሚጽፋቸው ሃሳቦች (እምነቶች ሊባሉ ይችላሉ) ወለም ዘለም ሳይሉ፤ ሳይሹለከለኩ የህወሓትን የበላይነት አባዜ እና ስነ-ልቦና የሚያንጸባርቁ ናቸው።
ለግራዚያኒ ሀውልት መሰራት ምክንያት በአዲስ አበባ የተደረገው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ይስመለኛል( ዘነጋሁት ጉዳዮን) ይሄው የምላችሁ ሰው እግዚያብሄርም እኛ። ሰይጣንም እኛ።” በማለት ጻፈ። ከጸሃፊው ሁኔታ ህወሓት ትግራይ፤ትግራይ ህወሓት ነው። ልዩነት የለውም። ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኗን ቢያውቅም የሚያምን አይመስልም። ምናልባት ጠንከር ባለ ሁኔታ ይዞት ካልሆነ በስተቀር ይሄ ሃሳብ የሰውየው የግል  አመለካከት አይመስለኝም። ህወሓትኛ አስተሳሰብ ነው። እዚህ ላይ የተነሳበትም ምክንያት የቡድን አስተሳሰብ ስለመሰለኝ ነው።ጎሰኝነት የአስተሳሰብ ሚዛናቸውን ባንድ ጎን  ወደ ታች ስቦ መሬት ያላስነካባቸው ግለሰቦች ካሉአይመለከታቸውምና ቅር መሰኘት የለባቸውም።
እዝነ ህሊናቸውን ፈቅደውም ይሁን ሳይፈቅዱ ለጨፈኑ የህወሓት ሰይጣንነት ለማይታያቸው እና በማንኛውም የህይወት ገጽታ (በእምነት ጭምር) የህወሓትን መርዛማ የፖለቲካ እሳቤ እንደመለኮታዊ እውነት ወደላይ የሚሰቅሉትን ብዙዎቹን ነው የሚመለከተው፡:  እንዲህ አይነት ሰዎችመለስ ዜናዊ ሊቅ ነው። ወደር የሌለው ታጋይ ነው። ዓለምን የለወጠ ሃሳብ ባለቤት ነውብለው እዛ ላይ አያቆሙም። “እኛ[ህወሃት -ትግራይ]ሊቅ ነን። ታጋይ ነንበማለት ነገሩን ወደ ወል ባህሪ (ወደ ትግራይነት)ይወስዱታል። እዛም ላይ አይቆሙም! ሌላውን ወደ መናቅ ወደማጣጣልይሸጋገራሉ! አንዳንዶቹ ጸያፍ በሆነ መንገድ ይገልጹታል። ሌሎቹ ደሞ በብልጠት እየደባበቁ ያራምዱታል።
እግዚያብሔርም እኛ፤ ሰይጣንም እኛ በሚለው የቅዠት እምነት የፍጹማዊነቱ ደረጃ(የአድራጊ ፈጣሪነት ስሜቱ) የአጼ ኃይለሥላሴን ንጉሠነገስታዊ ባህሪ አስከንድቶ- ውድድሩን ከእግዚያብሔር ጋር ያደረገ ሃሳብ ነው።  ኃይለሥላሴ ከላይቸው እግዚያብሔር እንዳለ አምነው የስልጣናቸውን ህጋዊነት በእግዚያብሄር አድራጊ ፈጣሪነት ጠቅልለው የተሰጠ እንጂ ያልተቀማ እንደሆነ አምነዋል። የፖለካውም ተልዕኮ የተሰጠን የስልጣን ርስት ማስጠበቅ ነበር። በቃ ተብለው እስከወደቁበት ዘመንም እንደዛ አሳምነዋል። ከአውሮፓውያኑ ልዑላን እና ፍጹማዊ ነገስታቶች የተለየ አስተሳስብ አልነበረም።
ህወሓት ያንን አልፎታል። መሰረቱ በብዙ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የፈጠረው ራስእና የዓለም እይታ ነው:: ራሱን እንደ አምላክ ቆጥሮአል። ሌላውም ህወሓት እንደዛ ነው ብሎ እንዲያምን ይፈልጋል። ህወሓት ባደረሰው የስነ-ልቦና ዘረፋ ምክንያት(ለአማካሪዎቹ ምስጋና ይግባቸውና) የህወሓትን ዳረጎት የሚቀበሉም የማይቀበሉም የህወሓትን አምላክነት የተቀበሉ  ጥቂቶች አልጠፉም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ህወሓት ወታደራዊ የኃይል ሚዛን እንዳለው እያወቀ፤ የኢኮኖሚ ተቋማትን እንደተቆጣጠረ እና በፈጠረው የፖለቲካ ስርዓት ምክንያት ቅጥ ያጣ ሃብት እምዳጋበሰ ቢያውቅም ህወሓትን በንቀት እና በጥላቻ ከማየት ያለፈ(በህወሃት ምግባር ምክንያት )   አመለካከት እንደሌለው ህወሓት  ያውቀዋል። አንደኛውም የህወሓት ችግር ይሄ ይመስላል- እንደሰይጣን እንደሚታይ ያውቀዋል።   ማለት የተወጣጠረው የህወሓት ወታደራዊ ጡንቻ ሲዝል ነገሮችን በጉልበት እና በገንዘብ ማራመድ እንደማይችል ያውቀዋል። ያኔ የሚያድኑት የፍትህ ጥያቄዎች እንዳሉም ያውቃል።
 
ህወሓት በስልጣን ላይ ሆኖ ሃገር እያመሰ ባለበት ሁኔታ እንኳን  ወርቅ ነው እያለ ወደላይ የሚዘልበት የፖለቲካ ሃሳቡ ተሸንፎአል። ስዮም መስፍን 9ኛው የህወህት/ኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ኢህአዴግ  ”የውህደት ሃሳቡን ቸል ማለት እንደሌለበት ተናገረየተባለው ነገር (ሪፖርተር በዜናነት እንዳወጣውምናልባት በተወሰነ መልኩ ህወሓት የፓለቲካ አስተሳሰቡ የትም እንደማይደርስ መረዳቱን ያመላከተ ቢመስልም፤ ከታች እንዳማነሳው ሰሞኑን እንደ አዲስ የተወሰደው ዜጎችን የማመሳቀል ርምጃ የፖለቲካ ርዮተ-ዓለም ሽንፈቱን የመቀልበሻ ተጓዳኝ የፓለቲካ ርምጃ ሊሆንም ይችላል።
የህወሓት የስልጣን ህልውናው ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ እና በደህንነት ጉልበቱ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ህወሓት ያውቃል፤ እኛም እናውቃለን፤ሌላውም ያውቃል።  በሌላ በኩልም ይሄ በጉልበት ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ የፖለቲካ አሽናፊነትን እንደማይገዛ፤እንደማያዛልቀውም አሁንም ከህወሓት በላይ አሳምሮ ሊያውቅ የሚችል ወገን አይኖርም። ጭንቅ የሆነበትም ጉዳይ ይሄው ነው።  ስለሆነም ህወሓት የተያያዘው የፖለቲካ ስጋት ይደቅንብኛል ብሎ የሚያስበውን የፓለቲካ ሁኔታ ለመቀልበስ ሲል እንግሊዞቹ በታሪክ እንዳደረጉት አይነት የማይድን የሚያዳክም ግጭት በህዝቦች ዘንድ በእጅ አዙር እየተከለ መሄድ ነው።
እስከዛሬ ያስተዋልናቸውን ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ የበላይነት ያስጠብቁልኛል ብሎ የወሰዳቸውን የለየላቸው የፓለቲካ ርምጃዎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ርምጃ ተመስለው የተወሰዱ ፖለቲካዊ ርምጃዎችን ትተን (የስልጣን ክፍፍሉን፤ የኢኮኖሚ ዘረፋውን ሌላ ሌላውን ማለቴ ነው) በቅርቡ የወሰዳቸው የመሬት ሽያጮች የመሬት ንጥቂያዎች እና የማመሳቀል ርምጃዎች በዋነኛነት ያነጣጠሩት ህወሓት በሚፈራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ነው። ነገሩን በዝርዝር በጎሳ በጉሳ እያደረጉ ማስቀመጡ ምናልባት ህወሓት እንዲፈጠር ከፈለጋቸው ሁኔታዎች አንዱን እንዲሳካለት ማድረግ ሊሆን ስለሚችል አያስፈልግም። በወጥመድ ውስጥ እንደመግባት ሊሆን ይችላል። እምዲያውም ተቃዋሚውም ወገን ይሄንን ጉዳይ ጠንቅቆ በማወቅ የሚሰጠውን የተቃውሞ ምላሽ በተጠና ሁኔታ ማድረግ ያስፈልጋል። ሲሆን ሲሆን ህወሓት የፈለገውን አይነት አጀንዳ እየፈጠረ ተቃዋሚዉን የሚያስጮህበትን ሁኔታ በማስቀየር ተቃዋሚው ህወሓትን የሚያስጮህበትን እና አውሬነቱን አውጥቶ የሚጨርስበትን አካሄድ ማሰላሰል እና ማቀድ ያስፈልግ ነበር።

ማፈናቀል አዲስ ተሞክሮ አይደለም። ለሃያ አንድ አመታት ያህል ህዝቦች ከመፈናቀልም አልፈው እንደ ሰንጋ እንዲታረዱ የሆነበት ሁኔታም አለ- በህወሓት መሰሪ ፓለቲካ ምክንያት! ከአንደኛው የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሌላኛው ተዘዋውረው ራሳቸውን ለማሸነፍ እና ቤተሰባቸውን ለመመገብ የሞከሩትን ትተን ሳይንቀሳቀሱ እዚያው ተወልደው ካደጉበት መንደር እንዲፈናቀሉ ተደርገው አይናቸው እያየ(የእኛም ዓይን እያየ) መሬታቸው ለባዕዳን የተሽጠበት ሁኔታ አለ። እንዲህ ያለ ነገር በአፋር ወገኖቻችን ላይ ደርሷል። በጋምቤላ አካባቢ በአኙዋክ ወገኖቻችን ላይ ደርሷል። እንዲያውም የጋምቤላዎቹ ራሳቸውን ከእንዲህ አይነት ቅጥ ያጣ የማመሳቀል ርምጃ ለመከላከል ሳይወዱ በግድ ከህወሓት ጋር ህወሓት በሚገባው መንገድ እየተናነቁ ራሳቸውን ለመከላከል የሞከሩበት ሁኔታ እንዳለ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በገዳማውያን ጭምር (እነሱም ስጋት ሆነው ነው እንግዲህ!) ማፈናቀል ደርሷል። ህወሓት በገባው የፖለቲካ ስጋት የወሰደውን ርምጃ ሁሉ የጠቀለለው ልማትስም ነበር።
የሰሞኑን የማመሳቀል (በእጂ አዙር እንደሆነ ልብ ይሏል!)ተግባር ለየት የሚያደርገው አንደኛ ልማት የሚለው ዲስኩር ፕሮፓጋንዳ ላይ አለመዋሉ። ሁለተኛ በመጀመሪያ ሕወሓት አላመሳቀልኩም አይኔን ግምባር ያርገው ካለ በኋላ  መልሶ ደሞ ያመሳቀልኩትህገ-ወጥ”  ስለሆኑ ነው የሚል የሞኝ ክርክር ውስጥ ገባ። የህወሓት ደጋፊ የዜና አውታሮችም ያለ ምንም ሃፍረት ህገ-ወጥ ስለሆኑ ነው ለሚለው ሃሳብ ሰፊ ሽፋን ሰጡ። (በነገራችን ላይ ከሜዲያ ሸፋን ጋር በተያያዘ  ዚምባቡዌ እና ሌሎች መሰል ሃገራት  ኮሽ ሲል ሰፊ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጡት የምዕራባውያን -”ዓለማቀፍ” – የሜዲያ ተቋማት ኢትዮጵያ ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች በፖለቲካ ውሳኔ እንዲፈናቀሉ ሲደረግ እና ይህ ሁሉ መንገላታት ሲደርስ እንዳላዮ እንዳልሰሙ መሆናቸው እንዳይረሳ!)
የቀበሌ ወይ የወረዳ ባለስልጣናት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከከተሙበት ቦታ አፈናቅለው እየጫኑ ወደሌላ ቦታ የመላክ ፍላጎት ይኖራቸዋል ብየ አልገምትም። ከዚህ ድርጊት ጀርባ የህወሓት እጂ አንዳለበት ለማንም ሰው መገመት አይከብድም። በሁለት እና ሶስት ሳምንታት እድሜ ህወሓት ያፈናቀላቸውን ሰዎች መልሶ እንዲሰፍሩ አደረገ። የክልል ሶስት ባለስልጣናት ስለፈለጉ ተደረገ ብሎ ማሰብ ሞኝ መሆን ይመስለኛል።
እንዲመለሱ የተደረጉት ዜጎች የነበራቸውን ነገር እንደነበረ አያገኙትም። እንዳልነበረ ነው የሚያገኙት። በዚህ አንጻር ከሁሉም የበለጠ አሳሳቢው ጉዳይ በግፍ የተፈናቀሉት ዜጎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የነበራቸውን ሰላም እንዳልነበረ የሚሆንበት ሁኔታ መኖሩ ነው።  ምናልባት ስለሰፋሪዎቹ ህወሓት በእጂ አዙር ለአካባቢው ተወላጆች የሰጠው ምስል ሌላ አይነት ሊሆን ይችላል።እንደወራሪም አድርጎ ስሏቸው ሊሆን ይችላል።
ህወሓት እንዲህ የሚፈጥራቸው የፓለቲካ ሁነቶችፈጣሪነቱንእና የማመሳቀል አቅሙን እያሳየ ያለባቸው ሁኔታዎች እንዲመስሉ ለማድረግ ይፈልግ እንጂ በዋነኛነት ከስጋት እና ከጨለምተኝነት የሚመነጩ ሊሆኑ ይችላሉ። የማመሳቀል አቅምን ማሳየት የፓለቲካ አሽናፊነትን ማሳየት አይደለም! እንዲያውም እያመሳቀለ ያለውን የፓለቲካ ቡድን የተመሳቀለ ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።
የሆነ ሆኖ ህወሓት በአንድ በኩል ኢትዮጵያውያንን በገዛ ሃገራቸው እያንገላታ በሌላ በኩል ደግሞ የህወሓት ቱባ ናቸው የሚባሉት ሰዎች ኤርትራውያኖችን (ትላንትና በኃይል ንብረታቸውን ቀምቶ አረጋውያን ልጂ አዋቂ ሳይል በጉልበት እያጋዘ ወደ ኤርትራ እንዳላጋዛቸው) በኢትዮጵያውያ የማረጋጋት የማስፈር የማቀራረብ እና የማደላደል ስራ ይሰራል። የኤርትራ ተቃዋሚዎች በህወሓት/ ኢህአዴግ ግብዣ የህውሓት/ኢሃዴግን 9 ጉባዔ እስከመሳተፍ የደረሱበትንም ሁኔታ ማስታወስ ያስፈልጋል። ይህቺ የህወሓት ድርጊት የኢሳያስን  መንግስት ከመፍራት ይሁን ሌላ ነገር ከመፍራት ጊዜ ይፈታታል። ህወሓት የሃብት ክምችት ስላለው ምናልባት እሱም ራሱ አማላይ የፓለቲካ መደራደሪያ ሊሆን ይችላል ብሎ አስቦ ይሆናል።
የኤርትራን መንግስት በሚያደራጇቸው የኤርትራ ተቃዋሚዎች ቀይረው እየቀመሩ ያሉ የሚመስለውን የፓለቲካ ፕሮጀክት ያሳኩታል አያሳኩትም የሚለውን መተንበይ አይቻልም። ያለምንም ብዥታ መታየት ያለበት ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ፓሊሲ በቀጥታም በእጂ አዙርም እየተከተሉ በሌላ አንጻር ህወሓት ከኤርትራውያን ጋር የመቀራረብ ፓሊሲ ላይ የሚሰራበት ምክንያት በአትኩሮት ሊታይ ይገባል።  በህወሓት ስር ሆነውበብሄር ብሄረሰቦችፖለቲካ አገር አና ህዝብ እያደነቆሩ ያሉት ህወሓት የሚጋልባቸው የፓለቲካ ፈረሶቹም ጉዳዮ የገባቸው አይመስለም ወይንም ቢገባቸውም ጉዳያቸው አይደለም።

dbirku@gmail.com

No comments:

Post a Comment