ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል። ፍትሕ የናፈቃት ዓለም። በየጥጋጥጉ ዲስኩር ብቻ ተለጥፎ ይነበባል!‹‹በመፈክር ውስጥ የተሸጎጡ በርካታ ውሸቶች አሉ፤››“ነጻ ስለመሆን የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ሰው በሰውነቱ የሚከበርበትአገር እስከምንመሰርት ድረስ እንታገላለን። የብሶታችንና የትግላችን መነሻለናንተ ለኔ አዲስ ትግል አይደለም” መብታችን ይከበር ነው የምንለው፣ ነፃነት ያስፈልገናል፣ማንም እንዳሻው ተነስቶ ህወሃትን አምልኩ እንዲለን አንፈቅድም! ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ እየተሻኮትን ለወያኔ እድሜ የምንጨምርለት? ፖለቲከኞቹሰ ብንሆን የምንታገለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ካልን ልዩነታችንን አጥበን አንድ ላይ ማበር ያልቻነው ለምንድን ነው?
ህዝቡ አንድ በሆነበት ሰዓት በፖለቲካው ድርጅቶች ርዕዮተዓለም መከፋፈል ምክንያት ህዝቡን ከጨቋኝ ስርዓት መታደግ ያልተቻለበት ግዜ
ላይ መሆናችንን አስተውለናል ካላስተዋልን እናስተወል እንጂ! ዛሬ በዚህ ወሳኝ ትግል ምዕራፍ በሆንበት ወቅት ላይ ሆነን አንድነታችን
ካልታየ ነገ ደግሞ እንደፈራነው ስንታገል የነበርነው ድርጅት እራስ በራሳችን መሻኮት ልንጀምር ነው ማለት ነው አረ ጠንቀቅ እንበል!!
ለፖለቲካ ድርጅቶች እውነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ቆመናል ካልን አንድ የሚያረገን፣
የምናብርበት ግዜ አሁን ነው። ከዚህ የከፋ የጭቆናና የአፈና ዘመን አታሳዩን! ለህዝባችን በአንድ ላይ እንቁም !ዛሬ ህውሃት በወንዝ
ላይ የወደቀ ዛፍ በሆነበት ግዜ እኛ የወንዙን ውሀ መልቀቅ ሲገባን የሀሳብ ልዩነት ገደለን። የነፃነት ጉዞ መጨረሻው ያማረና ጣፋጭ
ነች። ድል ነፃነት ለናፈቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ከዘካሪያስ አሳዬ
No comments:
Post a Comment