Sunday, April 14, 2013

ኢዴፓ የመንግስት አሟቂ ቤተ ተሃድሶ ጀምረዋል!



ከመንግስት ጎራ በመሰለፍ በ11ኛው ሰዓት ላይ ተቃዋሚዎች ላይ ክደት በመፈፀም የሚታወቁት  አቶ ልደቱ በ1997 የምርጫ ሰሞን አቶ ልደቱ አያሌው የሰሩት ድራማ በየትኛውም ኢትዮጵያዊ ልብ ተቀርጾ ስለመቅረቱ እማኝ መቁጠር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡የቅንጅቱን ውህደት እውን ለማድረግ ይረዳ የነበረውን የኢዴፓ ስምምነት ለመግለጽ ይጠበቅ የነበረውን ማህተም ይዘው የተሰወሩት አቶ ልደቱ በመጨረሻ ብዙ የትግል አጋሮቻቸውን አጥተው ‹‹ሶስተኛ አማራጭ››ይዘው መቅረባቸውም አይዘነጋም፡፡ሶስተኛው አማራጭ ለልደቱ ተከታዮች ጭምር ግልጽ ባይሆንም 2002 ምርጫ ለመሳተፍ ባደረጉት ሽር ጉድ ሳይሳካላቸው አልፋል።  2005 የአካባቢ ምርጫ መሳተፍ ወሳኝ ስለ መሆኑ በመወትወት አለን ለማለት ሞክረዋል፡፡የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን በመፈረም የፓርቲዎች ምክር ቤት አባል መሆን የቻሉት ኢዴፓዎች በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ቢያንስ ውሳኔው ሙሼን እንደማያካትት እርግጠኛ አድርጎኝ ነበር፡፡አሁን ጥርጣሬዬን የሚያጠራ መረጃ እጄ ገብቷል፡፡ፓርቲውን ከታማኝ ተቃዋሚነት ለመዋጀት የተነሱ ጥቂት የማይሰኙ ወጣቶች ባደረጉት ውስጣዊ ትግል ፓርቲው ከምርጫው ራሱን እንዲያገል ሆኗል፡፡ኢዴፓ ቢያንስ 1 ዕጩ መወከል ይገባዋል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ከምርጫው መገለል የለበትም የሚለውን ሀሳብ ያመጣው ሙሼ መሆኑን እነዚሁ የኢዴፓን መታደስ የሚናፍቁ ታጋዮች ይናገራሉ፡፡በቀጣይ ጠንካራና ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እስከ ውህደት የሚደርስ ስምምነት ለመፈጸም ተዘጋጅተናል የሚሉት እነዚሁ ታጋዮች እነ ሙሼ ይህን የማይፈቅዱ ቢሆኑ እንኳ በኢዴፓ ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም ይላሉ ፡፡ግን ግን ኢዴፓ ቤት ተሃድሶ ገብ ምንም የሚታይ ለውጥ መፍጠር ሳይችል ቀርቷል፡፡ከምርጫው በኋላ ኢዴፓ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቆይቶ በመጨረሻው መጨረሻ ፕሬዘዳንቱ አቶ ሙሼ ሸሙ በአዲስ አድማስና በተወሰኑ ጋዜጦች ላይ ሀሳባቸውን ይሰጡ ይሆን?የሆነው ይሁን ህዝብን የሚጠቅም ስራ መስራት የህዝብ አይን መሆን ነው።ያለበለዚያ በህዝብ መተፋት አይቀርም !!!!!  

No comments:

Post a Comment