Tuesday, April 9, 2013

የራስ እያረረ የሰዉ ታማስላለች እንደሚባለዉ

የሟች ጠ/ሚ ገዢያችንን ስም ላለማንስት ምዬ ነበር ግን ምን ላርግ እሳቸዉን እረፍት የነሳዉ እኔ ሳልሆን ራእያቸዉን አራማጅ ነን የሚሉ አካላት ናቸዉ,.. እነሆ የሱማሊያ ሕዝብ ለሟች ሀዉልት ሰሩ ሲባል ነገሩ ለተወሰነ ደቂቃዎች ኮማ ዉስጥ ከተተኝ,,, "አዎ ኮ'ማ... C'O'M'A"..... ከኮማዉ እንደምንም ብዬ ከነቃሁ በኋላ ለማረጋገጥ የፈለኩት የኛ ሱማሊያ ወይስ የሞቃዲሾዎቹ የሚለዉን መሆኑን ነበር,.. መቼም እሳቸዉ በየሀገራት ሰራዊት እየላኩ ፀጥታ ማስከበር አመላቸዉ አልነበር ?? {የራስ እያረረ የሰዉ ታማስላለች እንደሚባለዉ} የሱማሊያ ጉዳይ ደግሞ ክፉኛ እንቅልፍ ነስቷቸዉ የነበረ ጉዳይ መሆኑ ግልፅ ነዉ,, ከአንዴም ሁለቴ ሶስቴ በፓርላማ ተቃዋሚዎች ምን አገባን ሲሉት ጆሮ ዳባ ብሎ ባጀት በጅቶ ሰራዊት ልኮ ስንት ኢትዮጵያኖች ሬሳቸዉ በአደባባይ በሞቃዲሾ ከተማ በየሚዲያዎች ማየት የተለመደ ሆነ,.. ግን የሆነ ይሁን ሀዉልቱን የሰሩት ወንድሞቼ የጂጂጋዎቹ መሆኑን ሳዉቅ ለ3 ደቂቃ ከ45 ሰኮንድ የለማባራት ሳቅኩ (ሊበሏት ያሰቧትን ቆቅ ጅግራ ነሽ ይሏታል ወይም ዶሮን ሲያታልሏት በ...... ጣሏት አሉ) ቆይ እኔ የምለዉ የሱማሌ ህዝብ ለመለስ ሀዉልት ሰራ ሲባል ለጆሮ አይቀፍም ??

እስቲ በመለስ ዘመን የሱማሌ ህዝብ ምን ጥቅም እንዳገኘ እንየዉ ....በየአመቱ ታላላቅ ድርጅቶች እንደ WFP, WHO, Oxfam እና UNICEF ስለ ድርቅ እና ረሀብ ሲዘግቡ ኢትዮጵያን ሳያነሱ አያልፉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ደግሞ ኦጋዴን ክልል ሁሌ የዚህ ሰለባ መሆኑ ግልፅ ነዉ,.. (ታዲያ የክልሉ ህዝብ ከልጆቻቸዉ ጉሮሮ ነጥቀዉ ነዉ የሰሩት ማለት ነዉ),.. ሌላዉ ኦጋዴን ክልል ከኢትዮጵያ ክልሎች ሁሉ ግጭት ሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈናቀል የሴቶች መደፈር እና ብጥብጥ የሰፈነበት ቀጠና ነዉ ፤ በዚህም ምክኒያት የክልሉ ህዝብ በየቀኑ የኦብነግ (ONLF) ንቅናቄ ግንባርን መቀላቀል ከእለት እለት እየጨመረ መጥቷል (በዚህ መሀል የክልሉ ህዝብ ለሳቸዉ ሀዉልት ሰሩ ሲባል አይገርምም ?? ) እስቲ ይሁን ብለን እንቀበለዉ እንጂ የማይታመን መሆኑ ግልፅ ነዉ።
ግን አሁን አሁን ነገሮችን ቁጭ ብዬ ሳየዉ ከመግረም አልፈዉ በግድ ያስቁኛል ፤ ነገሩ እንዲህ ነዉ " ለሰብአዊ መብት የቆሙ እና የሚሞግቱ ሙሁራን እንዲሁም ወጣቶች ሁሌ የመንግስትን ድክመቶች እና ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለያየ መልክ ሲነቅፉ አያለሁ " በዚህ አጋጣሚ ለነዚህ ወጣቶች ያለኝን ከፍ ያለ አክብሮት እየገለፅኩ በአእምሮዬ የሚወራጩ ሀሳብ ቢጤ ላካፍላችሁ,...
ቀልደኛዉ እና የዋሁ መንድስታችን ወያኔ ኢህአዴግ ዋና ድክመቱ ከስህተት እና ከታሪክ የማይማር ድርጅት መሆኑ ነዉ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!!!!

No comments:

Post a Comment