ሀመሮች; "የጠገበም የተራበም ልክ አይፈርዱም" ቢሉም ;እንደ ረሃብ ግን የኅሊና ሚዛንን የሚሰባብር የለም:: ሠው ሲርበው ከአምላኩ ይጋጫል:: ከራሱ ይጣላል:: ከገኘሁ ሁሉም! በ 77 አንድዋ ወንድሟ ሞቶ ሲያረዷት: እንዲህ አለች አሉ... "ወንድም ሞተሽ ብለው ለምን ይጠሩኛል; እራቴ ጎመን ነው ከብት ይበላብኛል!" what a year it was?an
overwhelming! ሌላኛው ደግሞ እንዲህ አለ... "እባክህ አምላኬ አዝመራውን ባርከው; ሆዴ ሊቀደድ ነው እየራበኝ ሳከው" woow what an imense roar?! ጊዜውን የሚያሳይ ከዚህም ጫን ያለው ደግሞ..."አህያ መጣች ተጭና ምስር; እናትየዋ ሞታለች ከስር; ልጁ ይጠባል የጡቷን ደም ስር" ....ብሎ ዘግናኙን የጊዜውን እውነት ስሎልን አልፏል::
ሲርብህ የፀጋዬ "ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል? ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል? መዝሙርህ ይሆናል:: ረሃብ መጥፎ ነው:: "የበላችው ያቅራታል ከላይ ከላይ ያጎርሷታል" እንደተባለላት ልጅ ከሆነም ጥጋብ መጥፎም ነው:: ግን ከርሃብ ይሻላል::ቢያንስ ረሃብን እንጂ 'ጥጋብን አጠፋለሁ' ብሎ የሚናገር መንግስት የለም:: ብዙዎቹ እያስራቡ በሆዱ ቢገዙትም ቅሉ! እጅግ አትጥገቡ;እጅግ የተራቡትን ትረሳላችሁና! እጅግ አትራቡ;ሁሉን ትረሳላችሁና! የራበው ሕዝብ መሪዎቹን ሊበላ ይችላል; እጅግ የራበው ሕዝብ ግን መሪዎቹ ያሉበት የሚያደርስ አቅም የለውም:: መሃል መንገድ ላይ ይቀራል:: እናም ለራህባችሁ ጊዜ አትስጡ:: የምትበሉት ብታጡ ያስራቧቹህ ጥጋበኞች አሉና!! 'ባገኝ በልቼ ባጣ ተደፍቼ' አይሰራም እዚ......!
No comments:
Post a Comment