እኛ ለራሳችን ኑሮ ከቀን ቀን የብረት ዘነዘና ሆኖ እንደጉድ እየቀጠቀጠን እያደር እንዳረጀ የእንጨት ሙቀጫ እንሰነጣጠቃለን በዚህ ላይ ትንሹም ትልቁም ገንዘብ አምጡ፡፡ አዋጡ ይለናል፡፡ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል። ፍትሕ የናፈቃት ዓለም።
ለእንትና ክርስትና መዋጮ፡ ለእገሌ አባት ቀብር መዋጮ፡ ለእገሊት አገባች መዋጮ..የእድር መዋጮ፡ ፡ ፀድቶ ለማይፀዳ አካባቢ የአካባቢ ፅዳት መዋጮ፡ ከአጥር ቀለም ባለፈ አረንጉዋዴነትዋ እለት ለእለት ለሚያሽቆለቁለው ከተማችን አዲስ አበባ መዋጮ፡ ዛሬ ያስቀመጥነው 2000 ብር በንጋታው ሳንቲም ለሚሆነው ለአመታት የማናየው የጡረታ መዋጮ፡ የአባይ ግድብ መዋጮ…መዋጮ! እዚህ ላይ ተንቀቅ ማለት ነው! ቦንድ እያሉ መላወሻ አሳጡን! ፍትህ ! ፍትህ! እያለ ሰው ሲጨው ምነው ለፍትህ ቦንድ ቢኖረው ብዬ ተመኘው !
ሚጢጢው ገቢያችን እንኳን ዙሩን አክርሮብን ጥሎን ለሚበረው ኑሮዋችን ቀርቶ በወር ለምንገፈግፈው መዋጮ እንኳን አልበቃ እያለ ነው፡፡ ከዛሬ ገቢ ቀንሶ መስጠት ማዋጣት ሳይሆን መስዋእትነት መክፈል ነው፡፡ መስዋእትነት ብል የአሳማውና የዶሮዋ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
አቶ አሳማና እመት ዶሮ መንገድ ይገናኛሉ፡፡ ጥቂት ካወሩ በኃላ ዶሮዋ
“ስማ አንድ ግሩም ሃሳብ አለኝ፡፡ እኔና አንተ ለምን አንድ ምግብ ቤት በጋራ አንከፍትም?” ትለዋለች
አሳማም…” ምን የሚባል ምግብ ቤት ?”ይላል
“የአሳማ ስጋና እንቁላል ምግብ ቤት ብንለውስ?” ዶሮ ትመልሳለች፡፡ አሳማ ዝም ብሎ ሲያስብ
“ያው አንተም በስጋህ እኔም በእንቁላሌ ማለት ነው” ብላ ቀጠለች ዶሮ
አሳማም ትንሸ አሰብ አድርጎ
“ግዴለም ይቅርብኝ፡፡ ይህን ምግብ ቤት ማቅናት ላንቺ መዋጮ ነው፡፡ ለኔ ግን መስእዋትነት ይጠይቃል፡፡ “ብሎ መለሰላት አሉ፡፡
የኛም ማለቂያ አልባ መዋጮ ምስኪኖቹን ከእመት ዶሮ ይልቅ አሳማውን እያስመሰለን ነውና አንድ ቢባልስ!?
ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደእመት ዶሮ ያላችሁት ግን አጋግላችሁ ከመቀጠል ባትቆጠቡ አይጎዳም፡፡

ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment