Friday, April 26, 2013

የብሄር ብሄረሰብ ፓለቲካ፣ ለዘረኝነት ቅስቀሳ ይመቻል


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከሲዳማ ዞን ተነጥሎ ይዋቀራል በሚል ወሬ ሰበብ በከተማዋና በዙሪያዋ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ታስታውሳላችሁ - ከተማዋ የእገሌ ብሄር ነች፤ የእነእከሌ ነች በሚል። 
ከጠ/ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ለመፍጠር ወራት ፈጅቶበታል - የብሄር ተዋፅኦ ለመቀመር። ለነገሩ፤ ኢህአዴግ አንጋፋ መሪዎችን በአዳዲስ መተካት ሲጀምር ጎልቶ የተነሳው የመጀመሪያ ጥያቄ ከብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው - የእገሌ ብሄረሰብ ስልጣን አላገኘም፤ የእንቶኔ ተጎዳ በሚል። ለነገሩ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ወሬ በተነሳ ቁጥር፤ ወዲያውኑ ብቅ የሚለው ጉዳይ የዘርና የብሄር ብሄረሰብ ተወላጅነት ሆኗል - ከሙስና ጋር ተቆራኝቶ። በብሄር ብሄረሰብ ስም በመቧደን የሚፈጠር የስልጣን ሽኩቻና ግጭት አገሪቱን ሊያናውጥ የሚችል ሌላኛው የፖለቲካ አጀንዳ ነው። የግለሰብ የመደራጀት ነፃነትን የሚጥስ የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ፤ የግለሰብ ነፃነትን ለሚጥስ የዘረኝነት ቅስቀሳ ያጋልጣል።
ገናና መንግስትና የፖለቲካ አሸባሪነት ይመቻል

ሶስተኛው የፖለቲካ አጀንዳ የመንግስትን ስልጣን ሙሉ ለሙሉ ጠቅልሎ እድሜ ልክ እንደ ርስት የመቆጣጠር አባዜ ነው። ኢህአዴግ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሃያ አመታታ ያለ ተቀናቃኝ ስልጣንን በብቸኝነት ይዞ ለመቆየት ቆርጧል። ብዙ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ኢህአዴግን በማስወገድ ስልጣን ለመያዝ የሚመኙ ናቸው። የጠላትነትን መንፈስ ያሰፍናል - አሁን የምናየውን አይነት። ለምሳሌ 2002 . ወዲህ ኢህአዴግ በፌደራልና በክልል፤ በወረዳና በቀበሌ 99.5% በላይ በማሸነፍ ሙሉ ለሙሉ ስልጣን መቆጣጠሩ አገሪቱን ወደ አለመረጋጋት ይወስዳታል ብለው እንደሚያስቡ የአሜሪካ እና የአውሮፓ መንግስታት በተደጋጋሚ ገልፀዋል። 
የስልጣን ጉዳይ ውስጥ ከመግባት በእጅጉ የሚጠነቀቀው የአለም ባንክ ሳይቀር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ሪፖርት ውስጥ፤ ኢህአዴግ ከላይ እስከ ታች ስልጣኑን አስፋፍቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቦታ ማጣታቸውን መዳከማቸው፤ ውጥረትን አስከትሏል ሲል ፅፏል። የፓርቲዎች የምርጫ ፉክክር ሲጠፋ፤ ስልጣን ለመሻማት የፓርቲዎች መቆራቆስና መጋጨት ስለሚከተል፤ ትልቅ አጀንዳ መሆን ይገባዋል። ነገር ግን የፓርቲዎች ፉክክር ከዜጎች የመምረጥ መብት ውጭ ትርጉም የለውም ነገር ግን ዋናው ጥያቄ የፓርቲዎች ቦታ ማጣት ሳይሆን፤ ዜጎችን አማራጭ የማሳጣትና የመምረጥ መብታቸውን ያለማክበር ገዳይ ነው። አድራጊ ፈጣሪ ፈላጭ ቆራጭ ገናና መንግስት የመሆን ጉዳይ ነው ግለሰቦች የራሳቸውን ሕይወት በራሳቸው ምርጫ የመምረጥ ነፃነታቸውን እንዲያጡ የሚያደርግ ገናና መንግስት ሊፈጠር የሚችለው፤ የዜጎችን የሃሳብ ነፃነትና የመደራጀት ነፃነት በመርገጥ ነው። የፖለቲካ አሸባሪነትም ተመሳሳይ መንገድ የሚከተል ነው። በሌላ አነጋገር፤ ሶስቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች እርስ በርስ የተሳሰሩ የግለሰብ ነፃነት አጀንዳዎች ናቸው። ለማንኛውም የህዝብ መብት ይከበር !!! የአምባገነን መጨረሻው ሞት ነው !!
                ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment