Friday, October 25, 2013

ዚምባቡዌ በሕገወጥ መንገድ ድንበሯን በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ ነበሩ ያለቻቸውን 38 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች፡፡

Government bans citizens from travelling abroad for work

 ኢሳት ዜና :-የኬንያው ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ሙታሬ በምትባለውና ከሞዛምቢክ ጋር ድንበርተኛ በሆነችው ከተማ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ በፖሊስ እንደተያዙ ማክሰኞ ማምሻውን ተዘግቧል፡፡
ተጠርጣሪ ስደተኞቹ በግምት ከ20 እስከ 30 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚምባቡዌ በሕገወጥ መተላለፊያ በኩል መግባታቸውን ያስታወቁት፣ በዚምባቡዌ ቤት ብሪጅ ዲስትሪክት የፖሊስ ኮማንደር ዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት ላውረንስ ቺኔንጎ ናቸው፡፡

ፖሊስ ምርመራውን እያካሄደ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኑም በሕገወጥ መንገድ ወደ ዚምባቡዌ በመግባታቸው ክስ እንደሚመሠረትባቸው ተናግረዋል፡፡

አንድ አውቶቡስ በመ ጋጨ ቱ ከ30 በላይ ሰዎች አለቁ

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሌ በራያ ቆቦ ወረዳ ከ40 በላይ መንገደኞች ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ በመገልበጡ ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶችም ቆስለዋል። መኪናው ከጭንቱ ልክ በላይ ሰዎችን ጭኖ መጓዙ ታውቋል።
በኢትዮጵያ የመኪና አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨ መ ረ መሄዱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል።

በቤይሩት የኢትዮጵያዊቷ ህይወት በመኪና አደጋ አለፈ

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በቤይሩት ኢትዮጵያዊቷ በመኪና አደጋ  ደርሶባት አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ባለመቻሏ ህይወቷ አለፈ።
ኢትዮጵያዊቷ አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ያልቻለችው- ቆንስላ ጽፈት ቤቱ ሀላፊነት አልወስድም በማለቱ እንደሆነ ተዘግቧል።
በዚህም ሳቢያ መዳን ስትችል የነበረችው ወጣት  ህክምና ባለማግኘቷ ለህልፍት መብቃቷ፤ ዜናውን በማህበራዊ መገናኛዎች የተከታተሉትን ሁሉ አሳዝኗል።
የቆንጽላ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች፤  ለግድብና ለተለያዩ ነገሮች እያሉ ኢትዮጵያውያኑ የሰው ፊት እያዩ ተንገላተውና ለፍተው ከሚያገኙት ገንዘብ  መዋጮ ከመሰብሰብ ውጪ በእንደዚህ ዓይነት የፈተና እና የችግር ጊዜያቸው ዘወር ብለው እንደማያዩዋቸው በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
በዚህም ሳቢያ ገንዘብ ተበድረው ልጆቻቸውን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚልኩ ኢትዮጵያውያን ወላጆች፤  እንደገና የልጆቻቸውን አስከሬን  በብድር ገንዘብ የሚያስመጡበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ይታወቃል።

ትልቁ የዲን መማሪያ ማዕከል ታሸገ::

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኘው ትልቁ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት ቤት በመንግስት ትእዛዝ እንዲታሸግ ተደርጓል፡፡
በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከ600 በላይ ተማሪዎች የእስልምና ሀይማኖት አስተምሮዎችን ይማሩበት ነበር።
መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማትን እያሸገ ነው። መንግስት  ድርጅቶቹ የአክራሪነት መፈልፈያ ሆኗል በማለት ይከራከራል።
የመንግስትን እርምጃ የሚቃወሙ ሙስሊሞች በበኩላቸው መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈልና ለማጋጨት እርምጃ እየወሰደ ነው በማለት ክስ ያሰማሉ።

ለብርሀንና ሰላም ማተሚ ያ ቤት አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ መሾሙ ሰራተኛው ን ድንጋጤ ላይ ጥሎታል

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ብርሀንና ሰላምን ለ20 አመታት የመሩት የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉወርቅ ገብረህይወት  ጡረታ ወጥተው በእርሳቸው ምትክ የህወሀት አባሉ አቶ ተካ አባዲ ዛሬ ስራስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።
የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ ሆነው የቆዩት አቶ ተካ፣ ከሰራተኛው ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ በመግባትና በአስተዳደራቸው ብልሹነት ይታወቃሉ።
ዛሬ ከሰአት ሹመቱ ይፋ ሲሆን የብርሀንና ሰላም ሰራተኞች እና ሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች በድንጋጤ መዋጣቸው ተሰምቷል። ወ/ሮ ሙሉወርቅ ምንም እንኳ የኢህአዴግ ደጋፊ ቢሆኑም፣ ከሰራተኛው ጋር ተግባብተው በመስራት የተመሰገኑ ነበሩ።
በአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው አቶ ተካ፣ ህገወጥ በሆነ መንገድ መሾማቸውንም ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል።
የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ያቋቋመው የሰራተኛ አዋጅ 377 ስራ አስኪያጆች የሚሾመው የስራ አመራር ቦርድ መሆኑን፣ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ አቅም ያለው ሰው ተወዳድሮ የሚገባበት ቢሆንም፣ ማስታወቂያ ሳይወጣ፣ በኢህአዴግ ቀጥተኛ ትእዛዝ እንዲሾሙ ተድርጓል።
የስራ አመራር ቦርዱ ለልማት አጄንሲው ማስታወቂያ እንዲወጣ ደብዳቤ ቢልክም፣ በመንግስት ተጽእኖ ስር የሚገኘው ኤጀንሲ በቀጥታ አቶ ተካ እንዲሾሙ አድርጓል።
ፍትህ፣ ፍኖተ ነጻነትና ሌሎች መንግስትን ይቃወማሉ የሚባሉ ጋዜጦች በብርሀንና ሰላም መሪዎች እንዳይታተሙ  መደረጉ ይታወቃል። አዲሱ ስራ አስኪያጅም ይህንኑ የመንግስት አፈና ፖሊሲ አስቀጥላሉ ተብሎ ከፍተኛ እምነት ተጥሎባቸዋል።

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ እና የፕራይቬታይዜሺን ኤጀንሲ በፖለቲካ ጫና ስራውን በአግባቡ እየተወጣሁ አይደለም አለ፡፡

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣  በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው ኦሞራቴ እርሻ ልማት በመንግስት አመራሮች ጫና በብዙ ሚሊየን ብር ኪሳራ ወደ ግል ተዛውሯል፡፡
በባለሃብቶች እጅ ባሉ ባለስልጣኖች ምክር የሚመነዘሩት የባለሃብቶች እና የባለስልጣናት ትስስር ለሰፊው የህዝብ ጥቅም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ኪስ የሚያደልቡ አሰራሮች መጠቀሚያ እንደሆነ ነው ያመለከቱት ፡፡
ካሁን በፊትም ፤ የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ ወደ ግል የተዛወረበት መንገድ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ነበር ፡፡
የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት በሊዝ ተሺጦ ያለ አግባብ በሚልየኖች የሚቆጠር ብር በአየር ላይ ባክኖ ቀርቱዋል፡፡ በዚህም  ከ98 በላይ ቤተሰብ አሰተዳዳሪ ሰራተኛች ያለ የስራ ዋስትና ተብትነዋል፡፡
በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው ሞራቴ እርሻ ልማት ያለበቂ ተመን ከተሸጡት ድርጅት መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ በስጦታ እንደ ተላለፈ የሚቆጠረው ይህ  የኮሪያ ባለሃብቶች የልማት ፕሮጀክት ወደ ግለሰቦች ሲዛወር ከህግ እና አሰራር ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ነው በማለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ለልማቱ የተገዙትን መኪናዎች ጨምሮ  ከመሳሪያዎች ጋር ከ32 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ባለበት ሁኔታ፣ ከገበያ ዋጋ በታች በሆነ ሁኔታ ለሺያጭ ውሎዋል፡፡
ኤጅንሲው የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መቆጣጠር በአግባቡ የመስራት አቅሙን ያዳከመው የኢህአዴግ መንግስት ፣  ሸበሌ ትራንስፖርት  ኮምቦልቻ ፤ ወይራን የመሳሰሉ ድርጅቶች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፈው እንዲሰጡ  ከባለስልጣናት በቃል በተላለፈ ትእዛዝ ያለማንም መስረጃ ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው ተሰጥተዋል።
የሸበሌ ማዴአዎች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፉ ከ 397 በላይ ተቀጣሪዎች ያለ ስራ ካሳ ወይም ምትክ የስራ ዋስትና ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
የየረር የዱቄት ፋብሪካ ተዘግቶ 41 ሰራተኛች ተፈናቅለው የስራ ዋስትና አጥተዋል፡፡ የሰራተኞች መብት እና ጥቅም እንዲሁም ውለታቸውን ባላከበረ ሁኔታ ተላልፈው ተሺጠዋል፡፡ የመንግስት ሃብቶች ወደ ግል ሲዛወሩ የሰራተኞችን መብት ባከበረ እና የስራ ዋስትናቸውን በተጠበቀ መካሄድ አለበት ቢልም ህጉ  ሳይተገበር ቀርቱዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች  በቁሳዊ እና የማህበራዊ ኪሳራ እንዲኖሩ መገደዳቸውን እና ልጆቻቸውን ለማስተማር እና  በልቶ ለማደር አቅም እንዳጠራቸው ለዘጋቢያችን ግልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኤጀንሲው ወደ ግል እንዲዛወሩ በ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ግብርና ሜካናይዜሽንና ግዮን ሆቴል ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ከሁለት ወራት በፊት በወጣው ጨረታ ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ሌሎች ሦስት የመንግስት የልማት ድርጅቶችም የባሌና የአርሲ እርሻ ልማት ድርጅቶች፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎችና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለሽያጭ መቅረባቸው ይታወቃል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታቸውን አየር ላይ እንዳለ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሦስቱ ድርጅቶች እንዳይሸጡ በመወሰኑ ከጨረታ ሒደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ሁለቱ ማለትም ባሌና አርሲ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽንና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡
በ2004/5 በጀት አመት ጊዮን ሆቴል፣ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ፣ ቡና ቴክኖሎጂና ምህንድስና እንዲሁም የኢትዮጵያ ማእድን አክሲዮን ማህበር ወደ ግል የዛወራሉ ቢባልም ሳይሸጡ ቀርተዋል።
ቢሊቶ እርሻ ልማት፣ ሀማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበርና አርባ ጉጉ እርሻ ልማት በአዲስ ለጨረታ ከሚቀርቡ ድርጅቶች ውስጥ ሲካተቱ ፥ በሰኔ ወር መጨረሻ ለጨረታ ከቀረቡት ውስጥ የባቱ ኮንስትራክሽን ጨረታ ተሰርዞ በሌላ የመንግስት ድርጅት ስር እንዲተዳደር በቦርዱ መወሰኑን በኤጀንሲው የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ይናገራሉ።
ወደ ግል ሳይዛወሩ በመንግሥት እጅ ይቆያሉ የተባሉትና ኤጀንሲው ስትራቴጂክ ካላቸው ተቋማት መካከል የጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ)፣  ሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ድርጅት (ኢትፍሩት) ይገኙበታል፡፡
የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በእጁ ላይ 287 ኢንተርፕይዞች ነበሩት፡፡ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ 236 ኢንተርፕራይዞችን ለግል ካዛወረ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የቀሩት 51 የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ሃያዎቹን በ2005 ዓ.ም. ወደ ግል ለማዛወር  አውጥቷል፡፡ ኤጀንሲው የመንግሥትን ኢንተርፕራይዞች በሽያጭ ወደ ግል ማስተላለፍ በጀመረበት በ1987 ዓ.ም. አምስት ኢንተርፕራይዞችን ብቻ ነበር ወደ ግል ያዛወረው፡፡ በቀጣዩ ዓመት እስከዛሬ ድረስ ክብረወሰን ሆነው የተመዘገቡትን 127 ኢንተርፕራይዞች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡
ከፍተኛ ሙስና እንደተፈጸመባቸው በተነገረው በዚህ ሽያጭ፣ ግብር ከፋዩ ክብረተሰብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለዘረፋ ተጋልጧል።
ESAT

No comments:

Post a Comment