Saturday, October 26, 2013

የሳውዲ የምህረት አዋጅ መገባደድና የኢትዮጵያውያን ስጋት

ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ገልጿል። የሳውዲ መንግስት ሕገ ወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣውን መስፈርት ለሚያሟሉ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት የሰጠው የተራዘመ የምህረት አዋጅ፤በቀጣዩ ሳምንት ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓም ተግባራዊ ይደረጋል።
በርካታእድሉን መጠቀም የሚችሉ ሕገወጥየነበሩ ነዋሪዎችን ጨምሮ፤ ሕጋዊ ቪዛ ይዘው ከአሰሪያቸው ውጭ በነጻነት ይሰሩ የነበሩ ጉዳያቸዉን ለማሳካት ላይ ታችቢሉም እስካሁን ብዙዎች እንዳላጠናቀቁ ይነገራል። ከደላሎች እስከ ሃገራቸው ቆንስልና ኤምባሲ ተወካዮች፣ ከግል ቪዛሻጭ ሳውዲ አሰሪዎች፣
 ከፊል ተወካዮች እስከ ሳውዲ መንግስት መሥሪያ ቤቶች በተወሳሰበ አሠራር ውስጥ 
ተዘፍቀውጉዳያቸው ከዳር ያልደረሰዉም ቁጥር ቀላል ነው አይባልም። የተራዘመዉ
 የጊዜ ገደብ እየተገባደደ ባለበት በዚህ ወቅትየሳውዲ መንግስት አስፈላጊዉን አከናዉነዉ ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ ያልተቀበሉትንም ሆነ ያስጠጓቸዉን እንደሚቀጣእያስጠነቀቀ ነዉ። ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ በዘገባዉ ገልጿል።
ነብዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሂሩት መለሠ

AUDIO http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_

17181945_mediaId_17181939

No comments:

Post a Comment