Friday, October 25, 2013

“ባድሜ የኤርትራ ነው:: ” አቶ በረከት ስምኦን

dd
የድሪምላየን ሆቴል ባለአክሲዮን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን በኤርትራውያን የፓልቶክ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው መንግስታቸው ባድሜ የኤርትራ ህዝቡም እርትራዊ ነው ሲሉ መስክረዋል::ይህም በሕወሓት ኢሕኣዴግ ውስጥም የሚታመንበት እንደሆነ የተናገሩት አቶ በረከት ከኢትዮጵያ የድንበር ከተሞች አብዛኛዎቹ የኤርትራ ስለሆኑ ሊመለሱ ይገባል ፌዴራል መንግስታችን ደሞ ይህን ያምናል ብለዋል::

የትግራይ ህዝብ በተለይም የመከላከያ ሰራዊቱ ጥያቄ ማንሳቱን ተከትሎ የሄግ ውሳኔን በተግባር ለማዋል ያልቻሉት የወያኔ ባለስልጣናት ባድሜን አሳልፈው ለመስጠት መቸገራቸውንም አቶ በረከት ለኤርትራውያኑ በፓልቶክ መድረኩ አልሽሸሸጉም:: በተለያዩ ጊዜያት ከሕግዴፍ ሰዎች ጋ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ያወሱት አቶ በረከት በአፋጣኝ ባድሜን እና ሌሎች ኤርትራ የጠየቀቻቸውን የድንበር ከተሞችን ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አምነዋል::አቶ ኢሳያስን ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካም ያሉት አቶ በረከት ለኤርትራ እና ለኤርትራውያን መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ በአጽንዎት ተናግረዋል::
ከካፒቴኑ ጋር የድሪምላየን ሆቴል ባለድርሻ የሆኑት አቶ በረከት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ማሴር አይሆንም የሚል ጠንካራ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለማድበስበስ ሞክረዋል::የባድሜን መሬት ለእርትራውያን ካስረከቡ በኋላ የትግራይ ህዝብ ስሜት ምን ይሆናል? ባድመን ነጻ ለማውጣት የተሰዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መቃብር ስፍራ በሻእቢያ ተቆፍሮ ሲወጣ እና ሲጣል ኢትዮጵያውያን ስሜታቸው ምን ይሆን? የትግራይ ህዝቦች አንጡራዊ ሃብት የሆነው የባድመ ወርቅ ስፍራ በሻእቢያ እየተቆፈረ ወደ አስመራ ሲጋዝ የትግራይ ህዝብ ስሜት ምን ይሆናል? አቶ በረከት ሳይመልሱ አድበስብሰው ያለፉት ጥያቄ::
minilik salsawi

No comments:

Post a Comment