Wednesday, October 23, 2013

‘‘መላኩ ፈንታ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሶስት ልጆች እናትን ከትዳሯ አፋተው አግብተዋል’’

ጋዜጣው ሪፖርተር
 
የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል።
ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል።
ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በክስ መዝገቡ ያትታል።
በዚህም መሠረት ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል የሙስና ክስ መስርቷል።
ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ዝርዝር ውስጥ በተጨማሪነትም ተከሳሽ በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ ተዝናንታለች ሲል፤ የተፈፀመው ወንጀል መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ያለአግባብ የመጠቀም ሙስና ሰርቷል ይላል። (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ እነሆ)
 
ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አዲስ አበባ
 
የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/መ/ቁ.     
የዐ/ህ/መ/ቁ.       
የከ/ፍ/ቤ/ወ/መ/ቁ/ 141352
ከሣሽ ………….. የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮማሽን ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች ……… 1ኛ/ አቶ መላኩ ፈንታ ቻይ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር
2ኛ. አቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር
3ኛ. አቶ በላቸው በየነ ገ/ጊዮርጊስ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4ኛ. አቶ ማርክነህ አለማየሁ ወዴቦ
ሥራ፡- ም/ዋና ዐ/ሕግ
5ኛ. አቶ እሸቱ ግረፍ አስታክል
ሥራ፡- ገ/ጉ/ባለሥልጣን አ.አ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ
6ኛ. አቶ አስፋው ስዩም ተፈራ
ሥራ፡- ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ
7ኛ. አቶ ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ሥራ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅ/ፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ
8ኛ. አቶ አስመላሽ ወ/ማርያም ገብሬ
ሥራ- የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ የነበረ
9ኛ. አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ደበበ
ሥራ፡- ነጋዴ
10ኛ. አቶ ከተማ ከበደ አስገልጥ
ሥራ፡- የግል ባለሀብት
11ኛ. አቶ ስማቸው ከበደ ካሳ
ሥራ፡- ነጋዴ
12ኛ. ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ወርዶፋ
ሥራ፡- ሐኪም
13ኛ. ኮ/ል ኃይማኖት ተስፋዬ ገ/ስላሴ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ
14ኛ. አቶ ዳንኤል ገ/ኪዳን (ያልተያዘ)
ሥራ፡- የግብር አውሳሰንና ምርመራ ኦዲተር
15ኛ. አቶ አውግቸው ክብረት
ሥራ፡- ዐቃቤ ሕግ
16ኛ. አቶ ጌቱ ገለቴ (ያልተያዘ)
      ሥራ፡- ነጋዴ
17ኛ. አቶ ገ/ስላሴ ገብረ ኃ/ማርያም
ሥራ፡- ነጋዴ
18ኛ. ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ሥራ፡- ጄ.ኤች.ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
19ኛ. ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
20ኛ. ነፃ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
21ኛ. ጌታስ ኃ/የተ/የግ ማኅበር
22ኛ. ኮሜት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
23ኛ. አቶ ፍፁም ገብረመድህን አብርሃ
ሥራ፡- ነጋዴ
24ኛ. አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ
 ቀጣዩን ለማንበብ ይሄን ይጫኑ http://ferewabebe.blogspot.no/2013/10/132006.html?spref=fb

No comments:

Post a Comment