Sunday, July 26, 2015

ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተለው የሃገሬ ሰው ደስ የሚለኝ

ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተለው የሃገሬ ሰው ደስ የሚለኝ አንድ ባህሪው በብሶቱ የሚያላግጡ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነን ባዮችንና ያልሆኑትን ለፕሬስ ነፃነት የማሆነው የለም ባይ ጋዜጠኞችን እንደሞተ ሰው የሚረሳው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ አቶ ልደቱን ቀብሮ እንደገባ እርስት አድርጎ ያን “አቴንሽን” ፈላጊ ፍጥረት ቀዝቀዝ ያለ የጨዋ በቀል ተበቅሎታል፡፡ ልታይ ልታይ ባዩ ልደቱ ከምንሰድበው ይልቅ ስንረሳው ያቃጠለንን ያህል የተቃጠለ ይመስለኛል፡፡ “ሶስተኛ አማራጭ ነኝ ፤የማርያም መንገድነኝ" ቢልም ጆሮ የሚያውሰው አላገኘምናየፖለቲካ ሞቱን ተቀብሎ እየሞታት ነው! የምንሰድበው ጊዜማ ‘የኢትዮጵያ ህዛብ ሁሉ አሉባተኛ ነው፣ የኔ ምጡቅ አስተሳሰብ ከአስር አመት በፊት የሚገባውም አይመስለኝ እናም ይህ ትውልድ ካተቀየረ የኔ ምቱቅነት ሊታወቅ አይችልም’ እያለ ሲመፃደቅ ነበር፡፡ አሁን ግን የማይወደውን መረሳት ተቀብሎ ከፖለቲካ ድንዛዜው ጋር ቀርቷል፡፡ 

ከልደቱ በኋላ ብዙዎች ተረስተዋል ፡፡ ‘ለስድብም አይመጥኑም’ ሲል የሃገሬ ሰው ትቷቸዋል፡፡ እነ ሰለሞን ተካልኝ፣እነ ንዋይ ደበበ፣እነ አየለ ጫሚሶ ወዘተ .... ፡፡ ደዊት ከበደ ደግሞ የሰሞኑ ባለተራ ነው፡፡ ይህ ሰው ከዕለታት አንዴ ብቅ እያለ የሚናገረውን ነገር ስመለከት አከራካሪ፣አነጋጋሪ መሆን የፈለገ ይመስለኛል፡፡ እኛ ስለሱ ስናወራ ደግሞ ስዕለቱ ሰመረ ማለት ነው፡፡ ‘ዳዊት ወዳጀ ነው በእርሱም ደስ ይለኛል’ የምትሉም ሆነ በዳዊት ዘባሪኮም የምትናደዱ ወዳጆች ቻል አድርጋችሁት ብታድሩ ደግ ይመስለኛል፡፡ እመኑኝ ስለዳዊት ከምናወራ ዝም ብንል እንጠቀማለን፡፡ ግራ ገብቶት ግራ ስለሚያጋባ ሰው ከዚህ በላይ ማውራት የሚፈልገውን ትኩረት መስጠት ይመስለኛል፤ እናም ጊዜያችንን ረብ ባለው የፖለቲካ ጉዳይ ላይ አውለን ስለሱ ብናወራ ተሻይ ነው እላለሁ !

No comments:

Post a Comment