Saturday, July 11, 2015

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የተናገሩት

‘’ንቅናቄያችን በአንድ ሰው ላይ፤ በሁለት ሰው ላይ፤ በአስር ሰዎች ላይ ብቻ የቆመ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የነፃነትና የዲሞክራሲ ስሜት መገለጫ የሆነ፤ ለዛ እስከመጨረሻው ድረስ ለመሄድ ዝግጁ የሆነ፤ በጣም ብዙ የተማሩ፤ ያውቁና የበቁ ብዙ የተሻለ ኑሮ መኖር ሲችሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን ብለው የቆረጡ ሃይሎች ያሉበትና የተሰባሰቡበት ድርጅት ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ ሹማምንት ለሚያደርጉት ማንኛውም የስነ ልቦና ትግል ጆሮ ሳይስጥ በጣም እየፈጠነ ያለውንና በጣም እየተራመደ ያለውን የነፃነት ትግል አካል ሆነን፤ ንቅናቄው የሚጠራቸውን የትግል ሂደቶች እየተቀላቀልን ወደ ነፃነታችን የምናደርገውን ጉዞ እናፋጥን። ይሄ ደግሞ በፍፁም የሚቀር ነገር አይደለም። የወያኔ ሹማምንትን እንደዚህ የሚያንገበግባቸውና የሚያቃጥላቸው መምጣቱን እያዩት ያለ ነገር ነው። እኔ ወያኔዎች በአሁኑ ጊዜ ያሉበት ሁኔታ የሚመስለኝ አንድ በፍጥነት እየመጣ ያለ ባቡር ሲመጣ እያዩት ሊያቆሙት ያልቻሉት ነገር፤ ምን እናድርገው ብለው እየተራወጡ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለ የሚመስለኝ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ለማይቀረው ትግል ተዘጋጅ፤ እየመጣን ነው!! ይሄ ትግል ደግሞ ዳር ለመድረሱ ቅንጣት ታክል አትጠራጠር!'

No comments:

Post a Comment