Thursday, July 9, 2015

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን �ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::


.........አንድ ጊዜ ላይ እንዲህ ሆነ::
ሀና የምትገኝበት ወታደራዊ ክፍል ግዳጅ ይሰጠዋል:: እስከ 30 የሚጠጋ አርበኛ የሚገኝበት ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት በአንድ የህወሀት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የመመለስ ግዳጅ ተሰጥቶት ይሰማራል:: ሀና መትረየሷን ታጥቃለች:: ጠዋት ከመነሻቸው ወደ ኢላማ ቦታው ገሰገሱ:: እንደታቀደው ድንገተ�ኛ ጥቃቱ ተሰንዝሮ የታሰበውን ጉዳት አድርሰው ወደ ካምፓቸው ሊመለሱ እያለ ድንገት በህወሀት ሰራዊት ይከበባሉ:: ምን ይደረግ? ብዙ ቁጥር ያለውንና እስከአፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ሰራዊት መክቶ ወደ ካምፕ መመለስ ከባድ ሆነ:: የዚህን ጊዜ ነበር አንድ ጀግና ታሪክ የሰራችው:: ....ሀና::
መትረየሷን መተረች:: ገዢ መሬት ያዘች:: ቦታዋን አስተካከለች:: ....እሷ መስዋዕት ሆና የትግል ጓዶቿን ልታስመልጥ ወሰነች:: ምሽት እየመጣ ነው:: ጓዶቿ ተ�ስናበቷት:: ዳግም በህይወት እንደማያገ�ኟት ታወቃቸው:: ...እሷ መትረየሷን ወደ ህወሀት ሰራዊት ለቀቀችው:: ለጓዶቿ ሽፋን በሚሰጥ ስልት አስካካችው:: ...ፍልሚያው በአንዲት ሀና እና በህወሀት ሰራዊት መሃል ሆነ:: የሀና መትረየስ ያስካካል:: ጓዶች በዚያ ሽፋን ወደ ጦር ካምፓቸው እየተመለሱ ነው:: የሀና የመትረየስ ድምጽ እየራቃቸው ነው:: እነሱ ይተርፉ ዘንድ አንድ አርበኛ መስዋዕት መሆን ግድ አለ:: በተሰጣቸው ግዳጅ ውጤታማነት እየተደሰቱ የሃናን መስዋዕትነት እያወደሱ ከካምፓቸው ምሽት ላይ ደረሱ:: በአርበ�ኞች መንደር ህይወት እንዲህ ናት:: ታጋይ ይሰዋል:: ትግል ይቀጥላል::
...እኩለ ሌሊት ከመድረሱ በፊት ነው:: ጭው ካለው የኤርትራ በረሃ አንድ ሰው ወደ አርበኞቹ መንደር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅጣጫ ይገሰግሳል:: በርቀት የተመለከቱት የሌሊት የካምፕ ተረኛ ዋርዲያዎች(ጠባቂዎች) መሳሪያቸውን አስተካክለው ጣት ከቃታ አገናኝተው ወደ ካምፑ እየገሰገሰ ያለውን ሰው ይጠብቃሉ:: ውድቅት ሌሊት ስለነበር ማንነት መለየት አልተቻለም:: የሚገሰግሰው ሰው እየቀረበ ሲመጣ ዋርዲያዎቹም ኢላማቸውን አስተካክለው እርምጃ ለመውሰድ ተ�ዘጋጁ:: ....ሰውዬው ቀረበ:: ሴት ናት::ሃና:: ዋርዲያዎቹ አላመኑም:: የዕለቱን የይለፍ ቃል ጠየቋት:: መለሰችላቸው:: ደክሟታል:: ተአምር የሚያሰ�ኘው ከዚይ የህወሀት ሰራዊት ከበባ ማምለጧ አይደለም:: ሁለት የጦር መሳሪያዎችንም ማርካ ተሸክማለች:: ከሷ መትረየስ ጋር ሶስት:: ዋርዲያዎቹ በሚያዩት ነገር ተደንቀዋል:: በአርበኞች መንደር ስለ ሃና እርም ወጥቷል:: ጉድ ተባለ::
....ሃናን በአካል ሳገኛት በጣም ቁጥብ ነበረች:: ብዙ አትናገርም:: ታሪኳን እንድታጫውተኝ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም:: ሲበ�ዛ ዝምተኛ ናት:: ጀግና አይናገርም::
...ሃና ከሰሞኑ ውጊያዎች በአንዱ እንደተሰለፈች እገምታለሁ:: ልብን በኩራት በሚያሞቀው ጀግንነቷ ሁሌም አስታውሳታለሁ:: የጣይቱ ልጅ!!!!!

No comments:

Post a Comment