
የኬንያ ፖሊስ ከጥቃቱ ፈፃሚዎች አንደኛውን አቁስሎ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተዘግቧል። ሆኖም የጥቃቱ ፈፃሚዎች በትክክል ከየትኛው ቡድን እንደሆኑ እስካሁን ፖሊስ የሰጠው መግለጫ የለም። የሀገሪቱ መንግሥት ጥቃቱ «ከሽብርተኞች» የተቃጣ ነው ሲል ገልጿል። ኬንያ ከሁለት ዓመታት በፊት በሶማሊያ የሚገኙ እስልምና አክራሪ ታጣቂዎችን ለመውጋት ጦሯን በላከችበት ወቅት የሶማሊያው ኧል ሸባብ ታጣቂ ቡድን በኬንያ ምድር የሽብር ጥቃት በመፈፀም መበቀሉ እንደማይቀር ዝቶ እንደነበር ይታወሳል። በዛሬው ዕለት የእእስራኤል ልዮ የኮማንዶ ሀይል በአሸባሪዎች የታገቱትን ዜጎችና ቁስለኞችን ለማስለቀቅ ከአሸባሪዎች ጋር እየተዋጋ እንደሆነና አንዲት ሴት ቁስለኛ እንዳስለቀቁ የእስራኤል የዜና ምንጮች ዘጉአርዲያንና ሲ ኤን ኤንን ምንጭ አድረገው እየዘገቡ ነው።
No comments:
Post a Comment