Monday, September 30, 2013

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው።

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው። በፖለቲካ ዘርፍ የአዲስ አበባው ቡድን ጥሩ እየተጫወተ ነው። አብዛኞቹ የመቐለ ቡድን አቀንቃኞች (ግን አዲስ አበባ አከባቢ የሚኖሩ) በሙስና ሰበብ እየታሰሩ (ሌሎችም እየደነገጡ) ከጨዋታ ውጭ እየሆኑ ሲሆን ለአዲስ አበባው ቡድን ደግሞ ዓቅም እያስገኙ ነው።

ግን የአዲስ አበባ ቡድን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ይችላል የሚል ግምት የለኝም። ምክንያቱም የመቐለው ቡድን የትግራይ ክልል መንግስታዊ መዋቅር ለግል ፍላጎቱ በማዋል አብዛኞቹ የህወሓት አባላት በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየመከረ ነው።
በትግራይ ክልል ቢሮ የሚሰራ የህወሓት አባል ለአዲስ አበባው ቡድን ለመደገፍ ይቸገራል። ምክንያቱም ለአዲስ አበባው ቡድን የደገፈ የትግራይ ባለስልጣን ከሓላፊነቱ ይባረራል። ስለዚህ አይሸናነፉም።
ይህ በንዲህ እንዳለ የህወሓት ሊቀመንብርና የትግራይ ክልል ፕረዚደንት የሆኑ አቶ አባይ ወልዱ ባለቤታቸው የሆኑት (ወይ የነበሩ) ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም የህወሓት ፅሕፈትቤት ሓላፊና የፖለቲካ አማካሪ አድርገው ሽሟቸዋል። ይህ ስልጣን ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ቀጥሎ በህወሓት ቁልፍ የሚባል ስልጣን ሲሆን የአቶ ቴድሮስ ሓጎስ የነበረ ነው።
እንዲህ ነው መተካካት። ባልና ሚስት ሁለቱም ቁልፍ ስልጣኖች ሲቆጣጠሩ። ‘ራእይን ማስቀጠል’ ካልቀረ እንዲህ ነው፤ የራስ ሚስት በቁልፍ ቦታ መሾም።
ህወሓት የፖለቲካ አማካሪዋን ይዛ ወደፊት። ጥሩ ነው፤ ትርፉ ኪዳነማርያም የህወሓት የፖለቲካ አማካሪ የምትሆንበት ዘመን። ህወሓቶች እንኳን ደስ አላቹ።
አሜን። 
It is so!!! Abraha Desta

No comments:

Post a Comment