Sunday, September 29, 2013

ኢሕአዴግ የሕዝቡን ልብ ያውቃል፤ ይፈራዋልም!

በፍቃዱ ዘ ሀይሉ
የዛሬውን ሰልፍ ለመታደም ስወስን ብዙ ሰው እንደሚገኝ ገምቼ ነበር። አልተሳሳትኩም፣ የዞን ዘጠኝ ጓደኞቼን ጨምሮ ሌሎችም በፌስቡክና ከፌስቡክ ውጪ የማውቃቸው አራማጅ/ተራማጆች ሁሉ በጠዋቱ ተሰባስበዋልተያይዘን ስንሄድ፤ ቀበና ያለወትሮዋ በእሁድ ምድር ደምቃለች።
ሰልፉ ገና ከመነሻው መድመቁ መንገዱን ካልዘጉት በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ሰው እንደሚታደም እርግጠኛ ሆንኩ።ሰልፈኛው ቁጥሩ እየገፋ ቢመጣም የትራፊክ ፖሊሶቹ መኪና ማገድ የፈለጉ አይመስልም። ፖሊስ በቀበና ዞረን ወደ ጃንሜዳ እንድንሄድ ግፊት ማድረጉን ቀጠለ። የፖሊስ አባላት አጥር ሰርተው በመቆም ሰው እንዳያልፍ ጣሩ። ኃላፊዎች ጃንሜዳ ሰልፍ ማድረግ ሕገወጥ ነው ተብለው ዘጠኝ አማራጭ ቢሰጣቸውም አሻፈረኝ አሉ። ሕዝቡ ገፍቶ መንገዱን ሲጀምር ትራፊክ ቢቋረጥም ፖሊሶችም መንገዱን አጥረው ያዙት። በየመንገዱ ዳር ተኮልኩለው የሚጠብቁትን ሰዎችም የመንግሥት ኃይሎች ይበትኗቸው ነበር። ሰልፉን ለመቀላቀል ከኋላ ካልሆነ በቀር ከፊት ትንሽ ድፍረትም፣ ትግልም ይጠይቅ ነበር። 

ረዥም ሰዓታት ፖሊስን የሚያወድሱ መፈክሮች ቢደረጉም ለአለቆቻቸው ታዛዥ የሆኑት ፖሊሶች ልብ ሊራራ አልቻለም። ሰልፉን በሌላ አቅጣጫ አስጉዞ፣ በስድስት ኪሎ አዙሮ ለመመለስ የተደረገው ሙከራም እንዲሁ አልተሳካም። በዚህ ሁሉ መሐል ሰልፈኞቹም፣ የሰልፉ አዘጋጆችም ለሰልፉ ሰላማዊነት እስከመጨረሻው ድረስ ደክመዋል፣ ተሳክቶላቸዋልም።

ኢሕአዴግ ለምን ሰልፎቹን ማፈን ፈለገ?

ከዚህ በፊትኢሕአዴግ ሕዝብ የሚወደው ይመስለዋል" የሚል አባባል ነበረን። እውነታው ግን ኢሕአዴግ ሕዝቡ ልቡን እንደነፈገው ማወቁ ላይ ነው። ሰልፉንና ቅስቀሳውን ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ቢፈቅድላቸውሕዝብ ሁሉ አደባባይ ወጥቶ ያዋርደኛል፤ ስለዚህ ሠላማዊ ሰልፍ አገደ ተብዬ ብዋረድ ይቀለኛል" በሚል ቀላሉን ውርደት ነው የመረጠው።

እኔ ከሚያዝያ 30/1997 ወዲህ ሕዝብ!’ ብሎ የሚወጣበት ሰልፍ ይመጣል ብዬ አልገምትም ነበር። አሁን ግን የማይቀር መሆኑ ገብቶኛል። በዚህ ሁሉ አፈና እና የመረጃ ግደባ መሐል ይሄ ሁሉ ሰው መገኘቱ የማይቀረው እየመጣ መሆኑን ማመላለሻ ነው። ኢሕአዴግ በጉልበት የማይወጣው ጣጣ ውስጥ ከሚገባ ይህ አጋጣሚ ፍርሐቱንም እውነቱንም ተጋፍጦ ለሕዝብ የለውጥ እና የመሻሽል ጥያቄዎች እውነተኛ መልስ ለመስጠት መልካም ዕድል ነው።


No comments:

Post a Comment