Thursday, September 26, 2013

ፖለቲካዊ ብዙህነት እና ኣብዮታዊ ዴሞክራቱ ኢህአዴግ (በብርሃኑ በርሀ/ መቐለ)

1- መግቢያ
ብዙሕነት በኣንድ ኣጠቃላይ ህልውና ጥላ ስር በሃሳብ፤ ኣደረጃጀት፤ በባህልና ፤በዘር፤በቋንቋ፤ወዘተ የተለያየ ህልውና መኖርን እና መታወቀንና መከበረን  የሚገልፅ ፅንስ ሃሳብ ሆኖ የተለያየ ህልውና፣ ባህሪና ማንነት በኣንድ ኣጠቃላይ ህልውና መጣመርን የሚገልፅ ነው። የብዙህነት ፅንስ ሃሳብ ዋናው ኣምር በኣንድ ኣጠቃላይ ህልውና ስር ልዩ ነፃ ህልውና የመኖር ጉዳይ ነው። ብዙሕነታችን እንደመወያያ ነጥብ ታሳቢ ኣድርገን ስንቃኘው ልዩነታችን በነፃነት ጠብቆ ከመኖር ኣንፃር ነው። የብዙህነታችን ፅንስ ሃሳብ ዋናው ኣንኳር መገለጫው የተለየ ፍላጓትን የሚገልፅ የፖለቲካ ኣቋም መያዝና ይህንኑ ኣቋም በነፃነት ማራመድ መቻልን የፍላጎት ተመሣሣይነት ያላቸው ዜጎች በነፃነት ተደራጅተው እንደ ፓርቲ የፖለቲካ ነፃነታቸው ተጠብቆ  በነፃነት መሥራት መቻልን ነው።ብዙህነት በሃሳብና በአማራጭ ተወዳዳሪ ማሕበራዊ ሃይል መኖርንና በነፃነት ለመወዳደር የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር መኖርን ነው።

     የፓለቲካ ምህዳር የሚባለው ነፃና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ፣ ነፃ ሚድያ፣ ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ኣስተዳደር፣ ነፃና ገለልተኛ የፀጥታ ሃይል፣ ከፓለቲካ ወገንተኛነት የፀዳ የሲቪል ሰርቪስ ኣስተዳደር፣ ብሎም የመንግስት ፓለቲካዊ ገለልተኛነት ነፃና ገለልተኛ ሲቪል ማሕበራት – - – -ወዘተ መኖርን የሚመለከት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ባልተJላበት የሚካሄድ ምርጫ የይምሰል ከመሆን ኣይልፍም፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የፓለቲካ ነፃነት የተነፈጋቸው በመሆናቸው የሕብረ ፓርቲ ስርዓት መገለጫና የብዙህነት ማሳያ ሊሆኑ ኣይችሉም፡፡ የለውጥ ኣጀንዳ ኣንግበው በህዝብ ፍላጎት ተመርጠው ለውጥ ለማምጣት የፓለቲካ ምህዳሩ እንዲስታካከል ቀዳሚ ኣጀንዳ ኣድርገው ህዝቡን ከጎናቸው ማንቀሳቀስ ኣለባቸው፡፡
2- ፖለቲካዊ ብዙህነት በሶሻሊስትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ እይታ
B.TOPORNIN አና E. MACHLSKY “ሶሻሊዝም እና ዴሞክራሲ”-ምላሽ ለኣድርባዮች በተባለው መፅሓፋቸው ሶሻሊስት ዲሜክራሲ የላቀ የዲሚክራሲ ገፅታ/highest form of democracy) መሆኑን ለማሣመን የጣሩ የሶሻሊስት ዲሞክራሲ ኣቀንቃኞች ሲሆኑ ብዙህነት በሶሻሊስት ዲሞክራሲ ምን እንደሚመስል የተነተኑበት” Socalism and Tthe Multiparty System” በሚል ርእስ ስር የኮሚኒስት ፓርቲው ግንባር ቀድሞ መሪነት ሚና ኣጥር ሳይሻገሩ የሠረተኛው ወዳጅ ወይም ታማኝ (friendly to the workers) የሆኑ መደቦችን የሚወክሉ ፓርቲዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንደሚከተለው ይገልፁታል።
The communists do not deny that when the communist party plays the leading role in socialist society other parties representing classes and social sectors that all friendly to the workers can exist in the political system,
ይህ በሳሻሊስት ዲሞክራሲ የብዙሃን ፓርቲ እና የብቸኛ ፓርቲ ስርዓት መኖር ጉዳይ ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም ለመሸጋገር በሚኖረው ሂደት ልዩ ሁኔታዎች (result from specific conditions) ውጤት እንጂ የግድ መኖር ያለበት ቀኖናዊ ኣቋም ሊሆን እንደማይችል እንዲህ በማለት ይገልፁታል ።
The multiparty and the one party system do not depend on a dogmatic scheme; they result from a specific condition under which the transition from capitalism to socialism is made and a developed socialism is built in aunties where the multiparty system has proved to be necessary, it  consolidates the alliance between the workers, and peasants, intelligentsia and other non-proletarian sections of the population and rallies the people round the guiding force of society, the communist (workers’) party.(p.165)
በሶሻሊስት ዴሞክራሲ የብዙህነት ስርዓት ፓርቲ መኖር ብዙሕነትን በከፈል በቃል ኣምኖ በተግባር ብዙህነትን ትርጉም በሚያሣጡ ቅድመ ሁኔታዎች የተተበተበ ሲሆን እነሱም ፤
(1)          የኮሚኒስት ፓርቲው ግንባር ቀድሞ መሪነት ሚና መቀበልን የግድ ይላል፡፡
(2)          ከግንባር ቀደሙ ኮሚኒስት ፓርቲ በተለይ የሚኖሩ ፓርቲዎች ውክልናቸው የወዝኣደሩ መደብ ወዳጅ መደቦች ብቻ መሆን እንዳለበት ከዚህ ውጭ በጠላትነት የተፈረጁት መደቦች ጥቅም ወካይ ከተባለ እንደ ፓርቲ መቆም እንደማይፈቀድ፡፡
(3)          እነዚህ ከግንባር ቀደሙ ፓርቲ የተለዩ ፓርቲዎች ስራቸው የወዝኣደሩ የገበሬውና፤የሙሁሩ እና የወዝኣደር ያልሆኑ ክፍሎች ከግንባር ቀደሙ ፓርቲ የትግል ኣጋርነት ማጠናከርና
(4)          የሚንቀሳቀሱትም የሚወክሉትን የሕብረተሰብ ክፍል በየሕብረተሰቡ ግንባር ቀደም መሪ ሃይል የሆነው የኮሙኒስት ፓርቲ’ውን በመደገፍ እንዲተጉ ማድረግ መሆኑን፡፡
(5)          ይህም ሆኖ ስለ ኮሙኒስት ፓርቲው የተለያዩ ፓርቲዎች መኖር የመርህ ጥያቂ ሳይሆን ልዩ ሁኔታዎች የግድ ሲሉ ብቻ የሚፈቀድ መሆኑን ነው
(6)          ከኮሙኒስት ፓርቲው የተለዩ የሚባሉ ፓርቲዎች ኮሙኒስት ፓርቲው ውጤታማ ሆኖ ሊሰራው የማይችለውን አጋሩ በመሆን እንደ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛ የሚያገለግሉ እንጂ ተወዳድረውት የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ የሚከጅሉ አይደሉም ።
የሶሻሊስት ዲሞክራሲ ብዙህነትን ያስተናግዳል የሚል ክርክር ይህንኑ የሚመሰል ሆኖ ከዚህ መረዳት የሚቻለው በልዩ ሁኔታም ቢሆን የተለያዩ ፓርቲዎች ህልውና የሚፈቅደው ኮሚኒስት ያልሆኑ ፓርቲዎቹ የኮሚኖስት ፓርቲው ኣጋር እሰከሆኑ ድረስ ብቻ ነው።
የሶሻሊስት ዲሚክራሲ ተንታኝ የሆኑት B.TOPORNTN እና E.MUCHULSKY ‘’ሶሻሊስት ዲሞክራሲ ከሁሉም ዲሞክራሲ የላቀ ዲሚክራሲ እና የብዙህነት ፓርቲ ስርዓት ይቀበላል፣ ኣድረባዮች ለፕሮፓጋንዳ ጠቀሜታ ሲሉ ሶሻሊስቶች የብዙህነት ፓርቲ ስርዓት ኣይቀበሉም በማለት ይወቅሳሉ እንጂ ከእውነት የራቀ ነው ’’ በማለት ወቀሳውን የማይቀበሉ ቢሆንም በዛው መፅሓፍ የብዙህነት ኣምር በሶሻሊስት ዴሞክራሲ የማይስተናገድና ሊስተናገድ የማይገባው መሆኑ እንደሚከተለው ይገልፁታል፡፡
 The socialist society has no place for parties which defend and express the interests of the landowner and big bourgeoisie, there Is no reason why these parties should be kept after the proletarian revolution and the subsequent transformation of the social system, historical experience shows without exposing right wing parties both politically and ideologically early, and defeating them organizationally.(P,170)
ከዚህ መረዳት የሚቻለው በሶሻሊስት ዲሞክራሲ ተወዳዳሪ ፓርቲ የሚሸከም ትእግስት ያለመኖር መርህ ሆኖ ከተወዳደርሪ ፓርቲ የሚኖረው ግንኝነት የውደድራና ኣብሮው የመሥራት ሳይሆን  የመጠፋፋት ፖለቲካ ግንኝነት ነው።  የጥላቻ ፓለቲካ ነው፡፡ ይህም እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲን በፖለቲካና የርእየተ ዓለም ማጋለጥና  የተደራጀ ህልውና እንዳይኖር በማድረግ (Defeating them organizationally) የሚፈፀም መሆኑነ ነው።የርእዮተ ዓለም ማጋለጥ ስራ ባልከፋ ድርጅታዊ ህልውና እንዳይኖረው ማድረግ ግን ሰላማዊ ያልሆነ የትግል ስልት በመሆኑ የአፈናና የጭቆና ስርዓት ያደርገዋል።
3- ፖለቲካዊ ብዙሕነት በአብዮታዊ ዴሞክራቱ ኢህአዴግ እይታ
 የኣብየቱ ተቀናቃኞች በፖለቲካ በርእዮተዓለምና በድርጅት እንዲሸነፍና ካልተደረጉ የኣብዮቱ ፍሬ መጠበቅ ኣይቻልም የሚለው የሶሻሊስት ዲሚክራሲ መርሕ-አህአደግ ከግንቦት 7 ቀን1997ዓ/ም ምርጫ በኋላም ዴሞክራሲና ዴሚክራሲያዊ ኣንድነት በኢትዮጵያ (ሰኔ 1ቀን 1997 ዓ/ም ገፅ 65-66 )ላይ
“እፍኝ የማይሞሉት ጥገኞች እና  ፀረ-ዴሞክራሲ ሃይሎች ኣደገኛ የሚሆኑት ሁሉም የዲሞክራሲ ሃይሎች በተለያየ ደረጃ ለፀረ- ዲሚክራሲያዊ የጥገኛነት ኣስተሳሰባቸው የተጋለጡና ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ በመሆናቸው ነው። ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ እጅግ ሰፊ በሆነ መሰረት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ታዳጊ ከመሆኑ የሚመነጩ ድክመቶች ሰላሉት፤ሰፊው መሠረቱ ለጥገኛ ኣስተሳሰብ የሚጋለጥ በመሆኑ በማይቋረጥ ትግል ውሱንነቶቹን መቅረፍ ካልቻለና በህዝቡ ውስጥ ያሉ ጥገኛ ኣስተሳሰቦች ካልተገሩ በጥገኛ ፀረ-ዴሞክራሲ ሊሸነፍ ይችላል። ይህ ኣደጋ በንደፈ ሃሳብ ደረጃ የሚቀመጥ ብቻ ሳይሆን በሶስተኛው ኣገራዊና ክልላዊ ምርጫ እንዲታየው ህያው የሆነ ኣደጋ ነው።”
ከዚህ ጥቅስ መረዳት የሚቻለው የኢህኣደግ የብዙህነት ፓርቲ ስርዓት የማይቀበል ርእዮተ ዓለማዊና ፖለቲካዊ መስመር ማራመዱና ይህ ባህሪ በሶሻሊስት ዴሞክራሲ ክለብ የሚቀላቅለው መሆኑን ነው።ይህም
(1)          እፍኝ የማይሞላ ጥገኛ ፀረ-ዴሞክራሲ ኣላማቸው ኣደገኛ ነው የኣብዮቱን ፍሬ ተመልሰው ሊወሰዱት ስለሚችሉ እነሱን መጨቆን ኣስፈላጊ ነው የሚለው ሃሳብ ይጋራል።  ኢህኣዴግ በፓርቲ የመደራጀት መብት እውቅና ሰጥቶ በተግባር የመስራት ነፃነት  የሚከለክለው ወይም በይምሰል ምርጫ የስልጣን እድሜው የሚያራዝመው…… ካለው ዓለም ኣቀፋዊና ሃገራዊ ፓለቲካዊ ሁኔታ ኣgሜን ሳልስት በሁኔታው የሚስማማ ስልት ብሎ ነው፡፡
(2)          ኢህኣደግ እንደ 1997 ምርጫ በነፃና ፍትሓዊ የምርጫ ቢሸነፍ የህዝብ ፍላጎት መገለጫና የህዝቡ ሉኣላዊነት መረጋገጡ ሳይሆን የኣብዮት መቀልበስ ኣድርጎ የሚያስብ መሆኑን፣ የኣብዮታዊ/ ሰሻሊስት ዴሞክራሲ ዲሲፕሊን መሪው ፓርቲ እራሱን ከህዝቡ በላይ ኣድርጎ ህዝቡ በእሱ መስመር እንዲገባ እንጂ ፓርቲው በህዝቡ ፍላጎት እንዲገዛ ኣይፈቅድም ይህ ሲሆን ፓርቲው የህዝብ ጭራ ሆንኩኝ በማለት በድክመቱ የሚያየው ነው፡፡  በህዝብ ፍላጎት መገዛት የብቁ ኣመራር መለያ ሳይሆን የተሸነፈ ኣሰራር ኣድርጎ ነው የሚያስበው፣ ስለሆነም የህዝቡ ፍላጎትና ምርጫ ከፓርቲው ፍላጎት ከወጣ ኣብዮት ተቀልብሳል ብሎ እሪ  ማለት የተለመደ ነው፡፡
(3)          ኢህኣዴግ በራሱ ድክመት በተሸነፈ ቁጥር እንኳን የራሱን እውነተኛ ድክመቶች የሚታየው ሳይሆን የተሸነፍኩት ህዝቡ የጥገኛ ፀረ-ዴሞክራሲ አመለካከት—–ወዘተ ሰለባ በመሆኑ ነው ብሎ ህዝብን ከመክሰስ ወደ ኋላ የማይል የግንባር ቀደም ፓርቲ ኣመራር ፍፁምነት በሽታ የተጠናወተው መሆኑ ነው።  ይህ ዓይነቱ የፓለቲካ ዝንባሌ የፓለቲካ ፍፁምነት (Poletical correctness) የሚባል ሆኖ የኢ-ዴሞክራሲያዊ ኣምባገነን መሪዎች መለያ ነው፡፡  በኢህኣዴግ ኣንደበት ‘’ፍፁሞ ዴሞክራሲያዊ’’ እንከን የለሽ፣ የተዋጣለት መስመር’’ የሚሉት የዚህ የፓለቲካ ፍፁምነት ኣስታሳሰብ ኣባዜ የወለዳቸው ናቸው፡፡  ይህ በመሆኑ ከህዝብም ሆነ ከተቃዋሚዎች ለሚመጣ ገንቢ ትችቶች የሚሰማ ጆሮ የላቸውም። በኢህኣዴግ እድሜ ፍፁም ዴሞክራስያዊ፣ የጠራ ዲሞክራሲ፣ እንከን የለሽ መስመር ወዘተ ሲባል ቆይቶ ትችት የሚነሳበት በኢህኣዴግ የውስጥ ሹኩቻ ኣሸናፊው ሃይል ድክመትን ኣንስቶ መተቸት የፓለቲካ ትርፍ ኣገኝበታለሁ ሲል ብቻ ነው፡፡
     ኢህኣዴግ ሕብረ ፓርቲ ስርዓት ኣሞርሮ የሚቃወምበት ሃገራዊ ዓለም ኣቀፋዊ የፖለቲካ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያሰገቡ ዜዴዎች በመጠቀም ቀዝቃዛው ጦርነት ከነበረው ሁኔታ ለየት ያለና እንደ መንግስት በሕብረተሰቡ ጫና የማሳደር ኣቅሙን  ግምት ውስጥ በማስገባት ቀስበቀስ ወደ ቅድመ የስግግር መንግስት የነበረበት ሁኔታ የመመለስ ኣዝማሚያ የተከተለ ነው።   ኢህኣዴግ  ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሚለው መስመር ተጠብቆ ኣልላቀቅ ያለውም ቀስ በቀስ ሁኔታዎች ኣስገድደውት የተቀበላቸው የካፒታሊዝም መርሆዎች ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት ለመመለስ ካለው ፍላጎቱ ስለሚጣጣም ነው፡፡  የኣብዮታዊ ዴሞክራሲ መመርያ ሃገራዊና ዓለም ኣቀፋዊ ሁኔታ በሚፈቅደው በተግባር እየፈፀምን መሆናችን እንጂ የተነሳንበት ዓለማ ኣልሳትንም የሚለው ኣባባል ከቁንጮ መሪዎች የሚደመጥ ነው፡፡
     የኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መለያ እምነቶችን (ነሓሴ1989ዓ.ም) የሚለው የኢህኣደግ የፖለቲካ መስመር የሚገልፀው ሰነድ ስናይ ከደርግ መደምሰስ በኋላ እየተገነባ ያለው ስርዓት ሕብረ-ፖርቲያዊ ዴሞክራሲ እንደሆነ በመግለፅ ይህም፤
“የሁለም ዜጎች ሰብኣዊና ዴሚክራሲያዊ መብት ተጠብቆ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚወክሉ ልዩ ልዩ ፓርቲዎች በነፃ የሚንቀሳቀሱበት እና ህዝብ ጥቅሜን ይወክለሉ የሚላቸውን ከመካከላቸው መርጦ ሃላፊነት ላይ የሚያስቀምጥበት ስርዓት ነው። ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉትና በሰላማዊና በዲሞክራስያዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ሁሉ የሚያገለግል ቢጋር ወይም ኣጠቃላይ ሁኔታ ነው” ይላል።
በዚህ ሰነድ ኢህኣዴግን ሕብረ-ፓርቲ ስርዓት መቀበሉን የሚያሳይ ቢመስልም ለሕብረ ፓርቲ ሰርዓት ጠንቅ የሆኑ ኣቋሞች ኣሉበት። በተለይ የኣብዮታዊ ዴሞክራሲ የኣስተሳሰብ ልዕልና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተብለው መላው መዋቅርና መድረክ መጠቀም ( ማሕበራት፤ ኢህኣደግን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋዘሪ መንገድ የያዛቸው ጋዜጦች፤መፅሔቶች እንዲሁም ሬድዮ ጣብያዎች) የመንግስት ሚድያ፥ሕገ-መንግስቱ፤ትምህርት ቤቶችና የታሪክና የስነ-ዜጋ ትምህርቶች፤ኣስመልክቶ የሠፈሩት ዝርዝር ኣቋሞች መንግስትን የፖርቲው ተቀጥላ የሚያደርጉ በመሆናቸው  ለ ሕብረ ፓርቲ ስርዓት ኣፍራሽ ኣቋሞች መሆናቸው ማስተዋል ይቻላል። ይህ ሰነድ የሚያረጋግጠው ኢህኣዴግ መንግስትን የፓለቲካ ፓርቲው ተቀጥላ ኣድርጎ በመንግስት ሃብትና ንብረት የፓለቲካ ርእዮተ ዓለሙን ሄጂሞኒ ለመገንባት የያዘው ኣgም ሲሆን ኢህኣዴግን ኢ- ዴሞክራስያዊ ፓርቲ የሚሰኙት ባህሪ የሚያለብሰው መሆኑንም ነው፡፡
 ለሕብረ ፓርቲ ስርዓት ተፃራሪ ግልፅና የተጠናከረ ኣቋም ሊባል የሚችለው ግን ኢህኣዴግ ተሃደሶ ኣመጣሁ ባለበት ጊዜ”መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቂዎች በኢትዮጵያ ነሓሴ 1992ዓ/ም በተባለው በትግርኛ የተፃፈ ሰነድ ገፅ 49 “ላይ የሠፈረው፣
“……ካብ’ቲ ወያናይ ዴሞክራሲያዊ መስመር ወፃኢ ኣብ ሃገርና ዴሞክራሲያዊ ይኹን ልምዓት ክረጋገፅ ኣይኽእልን። ኣብ ካልእ ኩነታት ዴሞክራሲ ርእሰማላዊ ምዕባለ ዘረጋገፀ ሊበራል ዴሞክራሲ እውን እንትኾነ ኣብ ሃገርና ንፀረ ዴሞክራሲን ፅግዕተኛታት ጉልባብ ካብ ምኳን ዝሓለፈ ተራ ክህልዎ ኣይኽእልን። ፀረ ዴሚክራሲ ማለት ድማ ኣብ ኢትዮጵያ ቀፃሊ ቅልውልውን ኣብ መወዳእትኡ ምብትታንንማለት እዩ።ስለዝኮነ’ውን አዞም ተቓወምቲ ፓርቲታት ኣብዚ ዘለናሉ መድረኽ ንታሪኽን ንሕ/ሰብ ኢትዮጵያ ንቕድሚት ዘስጉም ባህሪን ተራ ኣይብሎምን….. ወይ ካብ’ቲ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት ወፃኢ ኮይንካ ብዓመፅን ብሓይልን ንወያናይ ዴሞክራሲ ንምስዓር ምፍታን እዩ። ወይ ድማ ሓውሲ ሕጋዊ ብዝኾነ ኣግባብ ወያናይ ዴሞክራሲ ኣብ ሃገርና ሱር ከይሰድድ ብዝከኣሎም ምፅዓር እዩ። (ገፅ, 49)
በኢህኣደግ እምነት ከጉዳት በቀር ምንም ጥቅም የሌላቸው ተቃዋሚ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ፓርቲዎች እንዲኖሩ መፍቀድ ተፈላጊ የሚሆነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች “የሻገተ ኋላ ቀር “ ኣስተሳሰባቸው ወደ መድረክ ካልወጣ ህዝቡ በኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ኣስተሳሰብ ማነፅ ስለማይቻል የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ኣስተሳሰብ የሚታገላቸው ሳይኖር ውስጥ ውስጡን እንዲጎለብቱ እድል መስጠት ሰለሚሆን ነው ይላል።(ገፅ:50) ይህ አቋሙ ለኢህአዴግ ሕብረ ፓርቲ ስርኣት የስልት እንጂ የመርህ ጉዳይ ያለመሆኑን በሚገባ ግልፅ ያደርጋል ።
     ዓለም በየጊዜው ወደ ሕብረ ፓርቲ ስርዓት እየገባ ያለው የተለያዩ እምነቶች ኣማራጮች በነፃነት ወደ ህዝቡ ቀርበው ተቀባይነታቸው በነፃና ፍትሓዊ ምርጫ በህዝብ ድምፅ ሲዳኙ እንጂ ኢህኣዴግ እንደሚለው ኣንድ ህዝብ በኣንድ ኣgም ለመግራት፣ ‘’የሻገተ =ላ ቀር’’ እንደተባለው የፕሮፓጋንዳ ቅመም ካልተገኘ ህዝብ የፈለገ ትምህርት ቢሰጠው ስለማይገባው ተብሎ ኣይደለም፡፡  ‘’የሻገተና =ላ ቀር ’’ የሚለው ኣናጋገር ራሱ በሕብረ ፓርቲ ስርዓት ከ የፓለቲካ ፓርቲዎች የስነ ምግባር ደንብ  ያፈነገጠ የማናለብኝንትና የጥላቻ ኣነጋገር በመሆኑ ተቀባይነት የሚቸረው ኣይደለም፡፡  መላው ኣለም ያመነበት በሕብረ ፓርቲ ስርዓት ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ይረጋገጣል የሚል ሲሆን  በኢህኣዴግ ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖር በኢትዮáያ የኣመፅና ከፊል ሕጋዊነት ሆኖ እድገትን ማጥፋትና ብሎም ሃገር መበታተን ነው የሚል ነው፡፡
ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሚና በኣመፅ፣ በከፊል ሕጋዊነትና ከሕገ-መንግሰቱ ባፈናገጠ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲን ለማፍረስ እንደሆነ የሚያትተው ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ የውድድር ስርኣት በመረጡት ፓርቲዎች በኣመፅና በሕገ- ወጥነት በሃሰት ወንጀል በመጥለፍ ማወድምን የሚደግፍ ፓለተካዊ መሰረት ለመጣል የሚከጅል ስልት ሲሆን  በይዘቱ ግን ሕብር ፓርቲ ስርዓትን ከመቃወምና ከልብ ካለመቀበል የሚመነጭ ነው፡፡
     ኢህኣዴግ ተቃዋሚዎች ኣውንታዊ ሚና የላቸውም ብሎ ርእዮተ ዓለማዊ ትንታና ያባጀው ኣመፅ፣ ሕገ- መንግስትና ሕገ- ምንግስታዊ ስርዓት እያለ በማሳበብ በሕግ በመቅጣት ለመጨቆን ምክንያት ይሆነኛል ብሎ የቀመረው የሃሰት ፓለቲካዊ ድርስት ስለመሆኑ ቀጣይ እርምጃዎቹ በሚገባ ኣሳይተዋል፡፡ይህ ድረሳነ ተሃደሶ ከቅድመ “ተሃድሶ” ጊዜም ቢሆን ሁለት፣ሦስት እርምጃ ወደ ኋላ ሲሆን እየቀጠለ የታየውም ቢሆን የኋሊት ጉዞው የሚያጠናክር እንጂ ያሳየው መሻሻል የለም። በተለይ ከምርጫ 1997 ዓ/ም በኋላ ኣዝማሚያው ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሆነው። የዲሞክራሲ ስርኣት ግንባታ ትግልና ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ መጋቢት 1995ዓ/ም የታተመው የኢህኣደግ ሰነድ ገፅ 77 ላይ የሕብረ ፓርቲ  ስርዓት ኣስመልክቶ።
“የሌበራል ዴሞክራሲ ስር በሰደደበትና የበላይነት ባረጋገጠበት ኣገር በመሠረታዊ ባህሪያት ሊበራል የሆኑ በርካታ ፓርቲዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በተግባር ተረጋግጦአል። በተመሳሳይ መልኩ መሰረታዊ ይዘታቸው ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሆኖ ከዚህ በመለስ በሉ ጉዳዮች የሚለያዩ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች የመኖራቸው ዕድል ቢያንስ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ዝግ የሚያድርግ ኣይደለም ይላል።“ገፅ 77)
በመቀጠል በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ስርዓት የግንባር ቀደሙ አብዮታዊ ግንባር ቀደም መሪነት የተቀበሉ አጋር ፓርቲዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና ኢህአዴግ አብሮ መስራት የሚፈቅደው ከነዚህ ልብሳቸው በልኩ ቀዶ ያሰፋላቸው ፓርቲዎች ብቻ መሆኑን ይገልፃል።
“በኣካባቢያቸው ለኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ማህበራዊ መሰረት የሌላቸው በመሆን የተሟላ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ባህሪ መያዝ ባለመቻላቸው የግንባሩ ኣባላት ባይሆኑም በኣሠላለፋቸው በኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ከምፕ ውስጥ የሆኑ ኣጋር ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል ። እነዚህ ሃይሎች በኣገር ኣቀፍ ፊልሚያ ጥቅማቸው የሚጠበቀው በኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ካምፕ መሆኑን በመገንዘባቸው በውስጣቸው አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ኣቋም ያላቸው ግለሰቦች ስላሉዋቸው ጠንካራ ኣጋሮችና የኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ካሞፕ ሃይሎች ናቸው።(ገፅ 78)
ከላይ የቀረቡት ሁለት ጥቅሶች ኣጠቃልለን ስናያቻው
(1)          በሊበራል ዴሞክራሲያ ሊበራል ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ማናቸውም ከሙኒስት ፓርቲም ቢሆን ሊኖሩና ነፃ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚኖራቸው ይሸሸጋል።
(2)          በሊበራል ዴሞክራሲ የተለያዩ ሊበራል ፓርቲዎች እንደሚኖሩ መነሻ በማድረግ በኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ብዙ ኣብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ብቻ ሊኖሩ እንደሚችሉ እንድሞታ በመስጠት መኖር ያለባቸው ብዙ ኣብዮታዊ ዴሞክራቶች ብቻ እንደሆኑ እንጂ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባለበት ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መኖር እንደማይቻል እንደሞታ ይሰጣል፡፡የዚህ ሴራ ይዘት በሊበራል ዴሞክራሲ መኖር የሚችለው ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ስለሆኑ በአብዮታዊ ዴሞክራሲም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ብቻ ነው መኖር የሚገባቸው ከዛ ውጭ ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ቦታ ባይሰጣቸውም ተገቢ ነው የሚል እንድምታ ያለው ክርክር ነው።

(3)          የኢህኣደግ የብዙህነት ፓርቲ ስርዓት ፅንስ ሃሳብ መሥመር ግንባር ቀደም መሪ ኣብዮታዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲና ግንባር ቀዳምነትቱ የተቀበሉ ኣብዮታዊ ዴሞክራት(Non revolutionary democratic) ፓርቲዎች መኖር የሚል መሆኑን ነው ሲጠቁም ይህም ከላይ ብዙህነት በሳሻሊስት ዴሞክራሲ ኣስመልክተው ከፃፉት ሶሻሊስቶች መቶ በመቶ ይጋጠማል፡፡
አሁን ኢህአዴግ ና ህወሓትን ጨምሮ ሁሉም አባል ፓርቲዎቹ በፅናት የሚተገብሩትና የስራቸው ውጤታማነት መለኪያ አድርገው የሚወስዱት አማራጭ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን መጨቆንና  ማዳከምን ነው።  አብዮታዊ ዴሞክራቶች በተወዳዳሪዎቻቸው ላይ የተቀናጀ ጭቆና መፈፀም የአመርቂ ህልውናቸው መሳያ አድርገውም ያስባሉ ። አንጋፋው የህወሓት መሪ የተከበሩ አቦይ ስብሃት ነጋ በዚህ ጉዳይ ያላቸው አመለካከትና አቋም ግልፅ ነው ፣የህወሓት ህልውናም የሚያዩት ከመጨቆን ብቃቱ ነው። ውራይና ለተባለው የትግርኛ መፅሄት በሰኔ ወር 2005 ዓ/ም እትሙ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ሲሉ ይገልፁታል ።
ናይ ህወሓት ፖለቲካዊ ፕሮግራም መሰረታት /ደርቢታት ሓረስታይ ፣ሸቃላይ ፣ሙሁርን ንኡሽተይ ወናኒ ሃብትን እዮም ። ነዚኦም እናንቀሐ እናወደበ በቢስረሖም እናዋፈረዶ ኩነታት ይልውጥ አሎ ? ፖለቲካዊ ፕሮግራምና ልምዓታዊ በዓል ሃብቲ አጋር/ማሓዛ ስለዝኾነ ፣ዝተዋደደ ሓገዝ /Coordinated Suport / ክግበረሉ አለዎ ይብል።ብአንፃሩ ፅግዕተኛ በዓል ሃብቲ ተፃባኢ ናይቲ ስርዓት ስለዝኾነ ዝተዋደደ ፀቕጢ ክግበረሉ አለዎ ይብል ። ነቲ ድጋፍ ፣ነቲ ኻልእ ድማ ፀቕጢ’ዶ ይግበረሉ አሎ ዝብሉ ሕቶታት ምስተመለሱ ሓደ መፍለጢ ህልዊ ኩነታት ህወሓት ይመስለኒ።ገፀ 20
—- ፈታውን ፀላእን ፈልዩ ነቶም ፈተውቲ ደርቢታት አሰሊፉ ነቶም ፀላእቲ ፀቒጡ ኩነታት እናለወጠ እንትኸድ’ዩ ህወሓት ካብ ትግራይ ሓሊፉ ንሃገር’ውን ዝተርፎ።
ወደ አማርኛ ሲመለስ አጭር ይዘቱ የህወሓት ብቃት መለኪያው ወዳጆቹን መደቦች በመጥቀምና ተፃራሪ ጠላቶቹን የሆኑት መደቦች ጨቁኖ በመያዝ ሁኔታዎችን እየለወጠ ሲሄድና ከትግራይ አልፎ ለሃገር የሚበቃውም በዚሀ መንገድ ብቻ መሆኑን ነው። አንዱን መደገፍና ሌላውን መጨቆን የህወሓት ህልውና ሁኔታ ማወቅያ መሆናቸውን አሰምረውበታል ።
4- ህወሓት/ኢህአዴግ  ጠላቶቼ የሚላቸውን የሚጨቁንበት መንገድስ ምን ይመስላል ?
የጭቆናው መልክ የተቀናጀ እንደሆነ ከላይ በክቡር አቦይ ስብሓት ነጋ ተገልፆአል። የተቀናጀ ሲባል ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ፣ባህላዊና አስተዳደራዊ ብሎም በህግ ማእቀፍ የሚደገፍ እነደሆነ መረዳት ይቻላል። በስመ ልማታዊነት አጨብጫቢና ሙሰኛ ባለሃብቶችን የገበያው የውድድር ስርዓት ከሚፈቅደው ሕግጋት ባፈነገጠ የጥቅም ተካፋይ ማድረግ ፣ ንፁሃን ታታሪ ባለሃብቶችን ብሰራ ፈቃድ አወጣጥ፣ በግብር ክፍያ ፣ጨረታ ሂደት ፣በመሬት አሰጣጥ ፣— አድልዎና በደል በመፈፀም ማሸበርና የኢኮኖሚ ዓቅማቸው ማዳከም — ወዘተ ሲያካትት በባለ ሃብትነት ሊገለፁ በማችሉ ድሃ ዜጎች ድግሞ የስራ እድልን ከፓርቲ አባልነት በማቆራኘት የህሊና ቅጣት መፈፀም ፣ በመንግስት ስራ የሚገኙትም የስራ አፈፃፀማቸው ፖለቲካዊ በማድረግ በእድገት ፣ በስልጠና እድል ፣–ሁሉ ይጨቆናሉ ።
አማራጭ ፖሊሲ የሚያፈልቁ፣በአማራጭ ፓርቲነት የሚደራጁ እና ደጋፊዎቻቸውም በተመሳሳይ ይጨቆናሉ ። ብስራ ፣ በግብር አወሳሰን ይደፈጠጣሉ ፣በመናገር ነፃነት ይገደባሉ ፣ማህበራዊ መገለል ፣ ዛቻና ማስፈራራት ይፈፀምባቸዋል። ይህንኑ እውነታ በሁሉም አማራጭ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተደቀነ ችግር ቢሆንም ለአብነት ያክል ህወሓት በዓረና ትግራይ ፓርቲ ላይ የሚፈፅመውን ከብዙ በጥቂቱ እንሆ ፣ህወሓት “ተቃዋሚዎች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አጭር የስራ እቅድና አቅጣጫ” ( ሕዳር 11/2000 ዓ/ም ) በሚል ዓረና ትግራይ ፓርቲን አንጃ በማለት “  ከሌሎች የትምክህትና ጠባብ ፀረ ህዝብ ሃይሎች የማይለይ “ ነው በማለት በጠላትነት ከፈረጀ በኋላ ፣እያንዳንዱ አባል አንጃ ሆነ ሌሎች ፀረ ልማትና ፀረ ዴሞክራሲ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መከታተል የዘወትር ተግባሩ ማድረግ እንዳለበት አስምሮ በተለይ ዓረና ትግራይ ፓርቲን አስመልክቶ በሰነዱ ገፅ 11 ላይ ፣
“1- አንጃ እንታይ ይዛረቡ አበይ ይዛረቡ ንመን ይረ¦ቡ ንኸመይ ዝበሉ ይረ¦ቡ ኩሉ ክከታተል አብ መንበሪኡ ከባቢ አብ መስርሒኡ ከባቢ ብጥብቂ ተኸታቲሉ ደጋፊ ንአባል አባል ንዋህዩኡ ጠርናፊ ዋህዮ ጠርኒፉ ንመ/ውዳበ ጠርናፊ መሰረታዊ ውዳበ ን ወረዳ ንዞባን ክልልን ብዝቐልጠፈ ብእዋኑ ሪፖርት ይገብር ፣
2- አንጃ አባላቱን ደገፍቱን በዓል መን ምðኑ እንታይ ይሰርሑ አበይ ይሰርሑ ብኸመይ ይውደቡ ይራኸቡ ብስልኪ ብፅሑፍ ብአካል በቢኸባቢኡ ፅንዓት ገይሩ ብሰንሰለቱ ብቁልጡፍ ሪፖርት ክገብር አለዎ።”
ትርጉሙ
1-  አንጃ ምን እንደሚናገሩ የት እንደ ሚናገሩ ለማን እንደሚያገኙ እንዴት ያሉትን እንደሚያገኙ በመኖርያ እና በስራ ቦታ ሁሉም እንዲከታተልና ደጋፊ ለአባል አባል ለአስኳሉ የአስðል አስተባባሪ መረጃው አሰባስቦ  ለመሰረታዊ ድርጅት አስተባባሪ መሰረታዊ ድርጅት ለወረዳ ዞንና ክልል በተፋጠነ ጊዜ ሪፖርት ያደርጋል፣
2-  የአንጃ አባላትና ደጋፊዎቹ እነማን መሆናቸው ፣ምን እና የት እንደሚሠሩ እንዴት እንደሚገናኙና እንደሚደራጁ በስልክ በፅሑፍ በአካል በየአከባቢው የተደረገው ጥናት ደረጃው በጠበቀ በፍጥነት ሪፖርት መደረግ አለበት ።

ህወሓት መላ መዋቅሩን ከየፖለቲካ ፓርቲ ማንነት አውጥቶ ወደ የተደራጀ የስላላ ድርጅትነት መቀየሩን  ይፋ ያደረገ እውነታ ሆኖ ከዛ ባለፈ ወደ ተራ የማፍያነትና የቦዘኔነት ተግባር ለመሸጋገር መቁረጡንም በዛው ሰነድ ይፋ አድርጎአል። ህወሓት አባላቱን እንዴት ዓረና ትግራይን ማወክ እንዳለባቸው ሲመክር

“1- አብ አንጃ ባዕሉ ዝፀወዖ ዕላዊ አኼባታት አባልናን ደጋፊናን ከይቀሪ የግዳስ ተወደቡ ተዳልዩ አትዩ ነቲ ዝብልዎ ብንቕሓት ተኸታቲሉ ክቃለሶምን ከፈሽሎምን አለዎ።”

ይላል ትርጉሙ “ ዓረና ትግራይ በጠራው ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባ የህወሓት ደጋፊና አባል ተገኝቶ ተደራጅቶ ማኮላሸት አለበት ነው።” ( ገፅ 11) ህወሓት ይህ ብቻ አልበቃውም የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት አስመልክቶ ነሓሴ 2004 ዓ/ም ባወጣው ድርጅታዊ መግለጫው በተለመደው ዓረና ትግራይ ፓርቲን ኳኺቶ በማለት የተለመደ አባባሉ በመጠቀም “ ሕዚ እውን እንተኾነ ሓፋሽ ህዝብና አባልና ኳኺቶ እናግለሰ ብፅንዓት ከምዝምርሽ አይንጠራጠርን ።” / አሁንም ቢሆን ሰፊው ህዝብና አባላችን /ዓረናን / በማስወገድ በፅናት እንደሚረማመድ አንጠራጠርም / በማለት አውጆአል ።

5- ህወሓት/ኢህአዴግ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ አማራጭ የሌለው የህልውና ጥያቄ ነው ማለቱ ! ?
ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ከሌለ እንደ ሃገር ትበታተናለች ይለናል ። ሆኖም  ከላይ በዝርዝር ለማሳየት እንደተሞከረው ኢህአዴግ ኢ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና አገዛዙም ሙስናን ወደ ስርዓትነት የተቀየረበት ብልሹ አገዛዙ ጣራ የነካበት ሆኖም እያለ ሀገራችን እንደ የኢህአዴግ ትንቢት ያለመበታተንዋ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲ ቢነፈጉም አብረው በመታገል ያመጡታል እንጂ መበታተን ምርጫቸው እንደማይሆን ነው። ሊበራል ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ የሀገራዊ ምስቅልቅልና እንደ ሃገር መበታተን አጀንዳነው ፣ ሊበራል ዴሞክራሲን አማራጫቸው ያደረጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ለሃገር የሚበጅ አጀንዳ የላቸውም ብሎናል። ሶሻል ዴሞክራሲንም በአሁኑ ወቅት ከሊበራል ዴሞክራሲ የራቀ መርህ የለውም በሂደት በስም ካልሆነ በይዘት አንድ ሆነዋል በማለት ያሰምርበታል ። ከዚህ የኢህአዴግ አቋም ተነስቶ ሊደረስ የሚችል ማጠቃለያ በኢትዮጵያ ብቸኛው አማራጭ የለውጥ አጀንዳ አብዮታዊ ዴሞክራሲና አብዮታዊ ዴሞክሲያዊ ፓርቲ ብቻ ነው የሚል ነው። ይህም ማለት አማራጭ ፖሊሲና አጀንዳ አይሰራም የኢትዮጵያ ብቸኛው አማራጭ አብዮታዊ ዴሞክረሲና አህአዴግ ብቻ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ ማማተር በሀገር ህልውና መፍረድ ነው የሚል ነው። ተወደደም ተጠላም በኢህአዴግ መገዛት ወይም የሀገር መበታተን በፀጋ መቀበል ነው እያለን ያለው ። ለትንግርት አማራጭ የሌለው ምርጫ !! ነፃነት ወይስ ባርነት ከሚለው የኤርትራ ሬፈረንደም የባሰ ጉድ !!!
አማራጭ የሚነፍግ የፖለቲካ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሆን አይቻለውም ። አማራጭ ሃሳብ ፣ አማራጭ ፖሊሲንና አማራጭ ፓርቲን እንደ ጦር የሚፈራ ፓርቲ የ 87 ብሄር ብሄረሰብ እና ህዝቦች ባህላዊ አልባሳት ፣ዘፈኖች ፣ —- ቢያስተናግድ ፣ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብሎ የባህል ድግስ ቢያስተናግድ ብሄር ብሄረሰብ ቢፈልጉ በክልል ደረጃ ሊቋቋሙ ይችላሉ ብሎ ቢደነግግ  ጠቅላይ ፓርቲ እንጂ ፖለቲካዊ ብዙህነት የተቀበለ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊሆን አይችልም ። ሊሆን የሚችለውና እየሆነም ያለው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጠበቃ በመምሰል ከማንኛቸውም ለሚመጣበት የመብት ማስከበር ጥያቄ በዘር ፖለቲካ በመቃኘት ከፋፍሎ የመግዛት መርሆውን መፈፀም ብቻ ነው።
መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ/ም
መቐለ

No comments:

Post a Comment