ከዮና ብር
ባለራእዩ ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ በመጨረሻ ዘመናቸው (ምን እንደታያቸው አይታወቅም) ከበድ ያለ የጡረታ ፓኬጅ ለራሳቸው አሳውጀው ነበር። መቼም ለራሳቸው ብቻ አረጉት ብሎ ሰው እንዳያማቸው <ሼም> ፈርተው ነው መሰለኝ ለፕሬዘዳንቱ፤ ለምክትል ጠ/ሚንስትሩ እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት እንደየደረጃው ጡረታ ፈቅደውላቸው ነበር። ምን ያረጋል ሳይበሉት አለፉ እንጂ።
በአዋጁ መሰረት የመጀመሪያው ተጧሪ ….. አዛውንቱ ጋሽ ግርማ ሆነዋል። የጡረታ ቤቱ ክራይም በየወሩ ከ400 ሺ ብር በላይ እንደሆነ የሰሙ ሰዎች <<ፕሬዘዳንት ግርማ ተቀመጠው አበባ ለማስቀመጥ ይህን ያህል ብር ካስወጡን ቆመው ቢሆንማ ኖሮ በሚሊዮን ብርም አይለቁንም ነበር>> ሲሉ ተደምጠዋል። በብሩ መብዛት ብዙ ሰው ቅር ቢለውም አከራዮቹ እና ክራይ ሰብሳቢ ባለስልጣኖቹ ግን <<400 ሺ ብር ምን አላት ቀንሰንላቹ ነው እንጂ መጀመሪያ ያሰብነውማ 560 ሺ ነበር>> እያሉ ነው። በተጨማሪም ይህ ቤት የዋና ገንዳ ያለው ሲሆን ይህም የሚጠቅመው <<ፕሬዘዳንት ግርማ ከቻሉ እንዲዋኙበት ጤናቸው ካልፈቀደም እያዩት በሃሳብ ባህር እንዲዋኙበት ነው>> ሲሉ እነዚህ ክራይ ወዳይ ባለስልጣናት ይገልጽሉ።

በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ይህ ወጪ ለድሃ አገር ተገቢ አይደለም እያሉ ይከራክራሉ።
እኛ ደግሞ እንጠይቃለን
1. ጡረታ የወጡት ፕሬዘዳንት ግርማ ሳይሆኑ ጠ/ሚ መለስ (በህይወት ኖረው ) ቢሆኑ ኖሮ ገንዘቡ በዝቶዋል ምናምን የሚል ግርግር ይፈጠር ነበር ወይ? ሰለ ቤቱስ መረጃ ይወጣ ነበር ወይ?
2. በዚህ ያክል ገንዘብ ከመክራየት ይልቅ ለጡረተኞች እና ለሌላ የዲፕሎማት ስራ የሚያገለግሉ ጥቂት ቤቶችን መገንባት አይሻልም ነበር ወይ? ወይስ ክራይ ሰብሳቢዎችን (Rent Seekers) ስለሚጎዳ ነው?
3. መንግስታችን ጡረታ የወጡትን ፕሬዘዳንት እንዲህ በፎቅና በዋና መጦርን ካወቀ ምናለበት ከጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከ1% ለሚያንሱት ጧሪ እና ቀባሪ ለሌላቸው አረጋውያን መጦሪያ የሚሆን የማህበራዊ ዋስትና ነገር ቢያበጅላቸው? መቼም ከ1 ሚሊዮን በላይ ለማኞች ባሉባት ሃገር የዋና ገንዳ ያለው ጡረታ ቤት የሚያኮራ አይሆንም።
በመጨረሻ ለተሰናባቹ ፕሬዘዳንት መልካም የጡረታ ዘመን እየተመኘን ለሚቀጥለው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በዋና ወክለው እንደምናያቸው ተስፋ እናረጋለን።
No comments:
Post a Comment