Wednesday, September 25, 2013

ሰበር ዜና፤ ዶ/ር ነጋሶ ተለቀቁ፤ የጨነቀው ፖሊስ መኪኖችን ማሰር ጀመረ – ፍኖተ ነጻነት

የከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በሁለት ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በስተመጨረሻ በሃላፊዎቹ ጣብያውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው በአሁኑ ወቅት ወደ ቢሯቸው እየተመለሱ ነው፡፡
የቀድሞውን ፕሬዘዳንት አስረው የነበሩት ፖሊሶች ፋታ በማይሰጥ ሁኔታ የስልክ ልውውጥ በማድረግ ነጋሶን ለቅቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና የጨነቀው ፖሊስ መኪኖችን ማሰር የጀመረ መሆኑ ተገለጸ፤ በጃንሜዳና ቄራ ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው የዋሉት የአንድነት አባላት አመሻሹ ላይ (በቄራ ፖሊስ ጣብያ ዋስ እንዲጠሩ ተደርገው)ተለቀዋል፡፡በቅስቀሳ ስራ ተሰማርተው የነበሩት ቢለቀቁም ፖሊስ ለቅስቀሳ የተሰማሩ ሁለት መኪኖችን አልለቅም በማለት ምሽቱን መኪኖቹ በጣብያ እንዲያሳልፉ ፈርዶባቸዋል፡፡


cc
#millionsofvoicesforfreedom #udj

No comments:

Post a Comment