Sunday, September 22, 2013

አሁንስ በዛ …. ገለማኝም! ከሥርጉተ ሥላሴ

በጣም ብዙ ታገስኩኝ። በጣም ብዙ ብእሬን ኮረኮምኳት። የሚባለውን አነባለሁ። እያደንኩ አያለሁ። ዝም ያልኩት ግን መማር ይቻል እንደሆን ብዬ ነበር። ከዚህም ሌላ በድርጀቱ በአባልነት ሆነ በአካልነት ያሉ ወንድምና እህቶቼም ብዕራቸውን ሊያነሱ ይችላሉ ብዬም ጠበቅሁ። አሁን ግን እኔ ነፃ ሴት ስለሆንኩ ውስጤ የቆሰለበትን ነፃ አስተሳሰቤን ላጋራችሁ ወደድኩ።
ለማን እንደሚጠቅም አላውቅም። ለማን ይመቸው ተብሎ እንደሚደረግም አይገባኝም። ለነገሩ እንዲገባኝም አልፈልግም። ጠናና ዕይታና ቅንነት የነጠፈበት የምቀኝነት ቋሳ —-፤ ሽፍታው ድርጅት ወያኔ የሚፈጥረው መጠራቅቅ  አልበቃ ብሎ የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ከሆኑት ስህተቶች እዬተፈለጉ፤ ስንጥርና ስንጥቅ እዬተፈተሽ በግንቦት ሰባት ላይ ጦር የሚመዘዝበት ነገር አይገባኝም።

No comments:

Post a Comment