Thursday, September 26, 2013

ምን ነካን?!

ገረመው ዘመኑ
ወያኔ ደርግን ፋሺስት ይበል እንጅ ደርግ የሠራውን አንዱንም ትክክል አይደለም ብሎ ለመለወጥ ወይም ለማረም ሲሞክር ማናችንም አላየንም። እንዲያውም የሕልውናው መሠረት እይደረገው እንጂ።
ለምሣሌ መሬትን ለሕዝብ ያደረገውን አዋጅ ወያኔ አንድም ቃል ሣይለውጥ እንዳለ ገልብጦ በከፍተኛ ደረጃ በገንዘብ ማምረቻነትና በፖለቲካ መሣሪያነት እየተገለገለበት እንደሆነ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሥጢር አይደለም። ይህ ብቻም አይደለም። ወያኔ ሕዝብን እጅግ በጣም በመናቁ ደግሞ፣ ለፈረንጅ፣ ለሕንድና ለዓረብ መሬቱን፣ ደኑንና ውሃውን በሣንቲም ሲሸጥ የመሬቱ ባለቤት ለሆነው ኢትዮጵያዊ የሚሸጠው ግን መሬት ለንደን፣ ኒውዮርክና ዋሽንግተን ከሚሸጥበት በበለጠ ዋጋ ነው።

ለዚህ የወያኔ አገር ሺያጭ ዘመቻ ወገኖች ወርቃቸውን ተሸክመው ወገባቸው እስኪንቀጠቀጥ በየኤምባሲውና በየቀበሌው ቆመው መዋል – ማደራቸው ነው። የራሣቻውን መሬት ለመግዛት¡ [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment